TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተራዘሟል በአዲስ አበባ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ  እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ። ምዝገባው ሰኔ 30 ያበቃል መባሉ ይታወሳል። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 248,469 የኪራይ ውል ምዝገባ ተከናውኗል። አሁንም ምዝገባው እንደቀጠለ ይገኛል ብሏል። ነገር ግን ፦ - በርካታ ተመዝጋቢ በመኖሩ…
#AddisAbaba

" ለሁለተኛ ዙር አይራዘምም " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፤ የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት ምዝገባ  ለሁለተኛ ጊዜ የማይራዘም መሆኑ አሳውቋል።

ቢሮው በመጀመርያው የምዝገባ ወቅት የነበረው መጨናነቅ እንዳይደገም ነዋሪዎች ከወዲሁ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት በነዋሪዎች ጥያቄ መሰረት መራዘሙን ያስታወሰው ቢሮው " ነገር ግን አሁንም መዘናጋት እንደሚታይ " ገልጿል።

ባለፍነው ሰኔ 1 ጀምሮ ሰኔ 30 ይጠናቃቀል ተብሎ በነበረው ስምምነት በመጀመርያዎቹ ምዝገባ ቀናት ከፍተኛ የሆነ መቀዛቀዝ እንደነበር  ፤ ነገር ግን በወሩ መጨረሻ አካባቢ ከፍተኛ ቁጥር የነበረው ተዋዋይ መገኘቱን አመልክቷል።

በዚህም በቀን ከ30,000 በላይ ነዋሪ ይመዘገብ እንደነበር ተጠቁሟል።

በነዋሪዎች ጥያቄ የውል ስምምነቱ እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ/ም ቢራዘምም አሁንም መዘናጋት እንደሚታይ ተጠቁሟል።

የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት ለሁለተኛ ጊዜ የማይራዘም በመሆኑና በመጀመርያው የምዝገባ ወቅት የነበረው መጨናነቅ እንዳይደገም ነዋሪዎች ከወዲሁ እንዲመዘገቡ ቢሮው ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaHousingDevelopmentandAdministrationBureau

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ጉዳይ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት ማብራሪያ ሰጥቷል።

ቢሮው እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከአውድ ውጪ በተተረጎመ መንገድ እንደሆነ ጠቁሟል።

" የ1997 የጋራ መኖርያ ቤት ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው የተሳሳተ መረጃ ትክክል ባልሆነ መልኩ  ከአውድ ውጪ ተተርጉሞ የቀረበ ነው " ብሏል።

ቢሮው በሰጠው ማብራሪያ ምን አለ ?

" ከተማ አስተዳደሩ የጋራ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ለማስተላለፍ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2011 መሰረት ክፍል 3 አንቀፅ 13 ንኡስ አንቀፅ 1 እና 2 መሰረት ብቁ እና ንቁ ማለትም ' የቤት ፈላጊዎች በገቡት ግዴታ መሰረት የቁጠባ መጠን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትክክል ተቀማጭ ማድረጋቸውን ከእጣ በፊት ያረጋግጣል ' ይላል።

ስለሆነም የ1997 ተመዝጋቢዎች በወቅቱ በመረጃ ቋት ውስጥ ንቁ እና ብቁ  የነበሩ ተመዝጋቢዎችን ከተማ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ አስተናግዶ ያጠናቀቀ ሲሆን ነገር ግን በወቅቱ ብቁ ያልነበሩትን የ1997 ተመዝጋቢዎች እና ሌሎች የ2005 እጣ ያልደረሳቸው የቤት ፈላጊዎች እየተተገበሩ ባሉ የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮች እያስተናገደ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በወቅቱ ብቁ እና ንቁ  ያልነበሩ የ1997 ተመዝጋቢዎች ከየትኛውም የቤት ልማት መርሃ ግብር ውጪ እንደተደረጉ ተደርጎ የተሰራጨው የሀሰት መረጃ ተገቢ እንዳልሆነ ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ እና ይህንን ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩትን ከተማ አስተዳደሩ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል።

ከተማ አስተዳደሩ ተመዝግበው የሚጠባበቁትን ሆነ ሌሎች የከተማችዋን የቤት ፈላጊዎች ቤት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ አዳዲስ የቤት ልማት አማራጮችን በመቀየስ እየተገበረ ይገኛል " ብሏል።


NB. ቢሮው ስለ 1997 ተመዝጋቢዎች የትኛው ሚዲያ ከአውድ ውጭ የተተረጎመ ሀሰተኛ መረጃ እንዳሰራጨ በግልጽ ያለው ነገር የለም ነገር ግን መረጃውን የሚያሰራጩትን በህግ እጠይቃለሁ የሚል ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።

#AddisAbabaHousingDevelopmentandAdministrationBureau

@tikvahethiopia