TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የ14 ዐመቷ ታዳጊ ህይወቷ አለፈ⬆️

አንዲት የ14 አመት ታዳጊ ከተደፍረች በኋላ በተደፋባት #አሲድ መሰል ንጥረ ነገር ሕይወቷ አለፈ።

#ጫልቱ_አብዲ የተባለችውና ከምስራቅ ሐረርጌ በደኖ ወደ ሐረር መጥታ የቤት ሰራተኛ የነበረችው ይህች ታዳጊ የተደፈረችውና ሕይወቷ ያለፈው #በአሰሪዋ እንደሆነም ተመልክቷል።

ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ ግለሰብ ታዳጊዋን ከደፈራት በኋላ የአሲድ ጥቃት እንደፈጸመባትም ተመልክቷል።

ከጥቃቱም በኋላ በስቃይ ውስጥ እያለች በቤት ተደብቃ እንድትቀመጥ ማድረጉም ታውቋል። ታዳጊዋ ከመሞቷ በፊት ለፖሊስ በሰጠችው መግለጫ እንዳመለከተችው ሰውነቷ መሽተት ሲጀምር ወደ ሆስፒታል ሊወስዳት ተገዷል።

በአዲስ አበባ የካቲት 12 ሆስፒታል በሕክምና ላይ እያለች ሕይወቷ ላለፈው የ14 አመቷ ታዳጊ ጫልቱ አብዲ ትላንት በየካቲት 12 ሆስፒታል #የሻማ ማብራት ስነስርአት ተካሂዶላታል።

ታዳጊዋን #በመድፈርና በማቃጠል የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለ ቢሆንም እስካሁን ግን ፍርድ ቤት አለመቅረቡ ታውቋል።

©ኢሳት
ፎቶ፦ ናቲ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፍትህ_ለጫልቱ!!
#JUSTICE_FOR_CHALTU!

ሴት ሰው ናት!
ሴት ሀገር ናት!
ሴትን #መድፈር ሀገርን መድፈር ነውና በሞት ይቀጡልን!

"እኛም ሴቶች ዜጋ ነን!"

መንግስት የአሲድ መድፋት ወንጀልን ያስቁምልን!

📌 #የአሲድ ጥቃት አስመልክቶ ህግ ይውጣ።
📌 #አሲድ በቀላሉ እንዳይገኝ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሚላት⬆️

"....ካሚላት ናት። "ስለወደድኳት ረጨኋት" ያለ #አሲድ ደፊ ወንጀለኛ የልጅነት ገጿን፣ ቀለሟን፣ ውበቷን ገፏታል።የህዝብ ርብርብ ሆኖ እንጂ ህይወቷ ንም ሊነጥቅ የሚችል ጥቃት ነበር። ዛሬ በዚህ ምስል እንደሚታየው በሀገሯ መሪ እቅፍ ውስጥ ፈገግታዋ ብቻ ነው የሚታየኝ። በጥንካሬዋ የተቀዳጀችው ውበት ነው ያበራብኝ። ዓብይ በደረሱበት አሻራና ድካ ይተዋሉ። ወጣት ኢትዮጵያውያን በብሩህ መንፈስ ይከተሉታል። መልካም ነገር ፅናት ይጠይቃል፤ ዳርቻ የሌለው ትዕግስት ግድ ይላል። ዐብይ ካሚላን አቋጥረው በማቀፍ ሁላችንንም #አቅፈውናል። እናመሰግናለን። መልካም ጉብኝት ይሁንልዎ! ካሚላም መልዕክታችን ይድረስሽ፦ከዚህ ሁሉ በኋላ ለህይወት ያለሽ ጉጉትና ህይወትሽን እየመራሽበት ያለው ውበት በርካታ ብስጩ ተስፋቆራጭ፣ ተጨናቂና ተካዦችን አንገታቸውን ቀና እንደዲያደርጉና ለህይወታቸው ትርጉም እንዲፈልጉ ያተጋል።"

©ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የገዛ ባለቤቱ ላይ #አሲድ እንዲደፋባት ያደረገዉ ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ። 👉https://telegra.ph/DA-07-11
ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ላይ የተፈፀመው ምንድነው ?

ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ነዋሪነቷ በምስራቅ ሀረጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ ቀበሌ 02 ነው።

በ2008 ዓ/ም ነው ከባለቤቷ አቶ አሪፍ አልዬ ጋር በጋብቻ የተሳሰረችው።

ላለፉት 8 ዓመታት በትዳር ስትቆይ 2 ወንድ ልጆችን አፍርተዋል።

ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ፍፁም ባልጠበቀችው ሁኔታ በገዛ ባለቤቷ እና የልጆቿ አባት ዘግናኝ በሆነ መንገድ በአሲድ ተቃጥላለች። አንድ አይኗንም አጥታለች።

ከባለቤቷ ጋር በተደጋጋሚ አለመግባባቶች ቢፈጠሩም ይህን ያደርግብኛል ብላ በፍፁም አልጠበቀችም።

ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ፦

" በዕለቱ (ጥር 15  ቀን 2016) ቀን ስራ ውዬ ልጆቼን ከቤተሰቦቼ ጋር ይዤ ወደ ቤት ገባሁ።

ማታ ተሰብስበን እራታችንን በላን እጅግ ደክሞኝ ስለነበር ልጆቼን በግራ እና በቀኝ አስተኝቼ እኔም ተኛው።

በዛ ቀን ምን ክፉ ደግ አልተነገርንም። ከለሊቱ 9 ሰዓት ተኩል አካባቢ #አሲድ በማስታጠቢያ አድርጎ በተኛሁበት በጭንቅላቴ አፈሰሰብኝ።

ወይኔ ጭንቅላቴን ተቃጠልኩ ! ብዬ ከተኛሁበት ተነስቼ እጁን ልይዘው ስሞክር ' ገና መቼ ተቃጠልሽ ' ብሎ አሲዱን አይኔ ውስጥ ጨመረው።

ያኔ አንዱ አይኔን ለማትረፍ በእጄ ሸፍኜ በሩን ለመክፈት ስሞክር የተረፈውን አሲድ ጀርባዬ ላይ ረጨብኝ።

ለረጅም ጊዜ #በቅናት ምክንያት ያስቸግረኝ ነበር። ከዛሬ ነገ ይሻለዋል እያልኩኝ አብሬው ቆየሁ። በዚህ ውስጥ ነው 2 ልጆች የወለድነው።

በተደጋጋሚ ይዝትብኝ የነበረ ቢሆንም እንዲህ ይጨክናል ብዬ አላሰብኩም። "

እንደ ሀረማያ የሕይወት ፋና ሆስፒታል መረጃ ከሆነ በወ/ሮ አያንቱ ላይ የደረሰው ቃጠሎ 3ኛ ደረጃ የሚባለው ነው። የአሲድ ጥቃቱ በአይኗ፣ በጭንቅላቷ፣ ፊቷ ላይ ፣ ደረቷ ፊት ፣ እጇ ላይ ጉዳት ደርሷል።

የቀኝ አይኗ ላይ በአሲድ ቃጠሎው ምክንያት የብሌን ጉዳት ስላጋጠመ ማየት አትችልም። የግራውን ግን በህክምና ማትረፍ ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረጃው ባለቤት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ታደሰ) እውቅና ይሰጣል።

@tikvahethiopia