TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ጥያቄ ምንድነው ? ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ምላሽስ ?

• " እንደዚህ ዓይት ውሳኔ ላይ የተደረሰው አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ኃላፊዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው " - የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ፍቅረስላሴ አካሉ (ለአዲስ ስታንዳርድ)

• " ማህበራችን የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አላቀረበም " - ዶ/ር በፍቃዱ ዘለቀ (ለዶቼ ቨለ)

• " መምህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችን ህጋዊ ከሆነው #የኢትዮጵያ_መምህራን_ማህበር ጋር ብቻ በመነጋገር የሚፈታ ነው " - ወይዘሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል (ከትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየሰሩ ያሉ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ከህዳር 26 ቀን 2015 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የስራ ማቆም አድማ እንደሚመቱ የሚገልፅ ፅሁፍ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ከሰሞኑን ተሰራጭቷል።

መምህራኑና ቴክኒካል ረዳቶቹ አድማ እንደሚያደርጉ የተገላፀበት ይኸው ፅሁፍ ለትምህርት ሚንስቴር እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፃፉን የሚገልፅ ሲሆን " ያቀረብነው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም " በሚል ምክንያትነው አድማው ይደረጋል የሚለው።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቃላቸውን ለ " አዲስ ስታንዳርድ " ሚዲያ የሰጡ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ተከታዩን ብለዋል ፦

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ፍቅረስላሴ አካሉ ፦

" እንደዚህ ዓይት ውሳኔ ላይ የተደረሰው አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ኃላፊዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው።

ስራ የማቆሙ ሃሳብ ሁሉም መምህራን የሚጋሩት ነው። በቀጣይ የዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር መግለጫ ያወጣል። "

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህር ጥላሁን ረጋ ፦

" የመምህራን ደሞዝ አነስተኛ በመሆኑ በአገሪቱ ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም አልተቻለም።

በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ላሉ መምህራን የሚደርሳቸው የተጣራ ደሞዝ  8 ሺህ 5 መቶ ብር ብቻ ነው። ይህ እንዲሻሻልልን የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን ድረስ አልተመለሰልንም።

መንግስት የመምህራንን ጥያቄ ባለመመለሱና ችላ  በማለቱ በትምህርት ጥራቱ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረሰ ነው። ከምስራቅ አፍሪካ በኢኮኖሚ ትልቅ ሆና ለመምህራን ዝቅተኛ ደሞዝ የምትከፍል ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት።

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሙሉ ስራ ለማቆም ዝግጁ ናቸው። "

አንድ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህር ፦

" የመምህራን ማህበር #ለጥያቄዎቻችን ትኩረት መስጠት ባለመቻሉ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ መምህራን ተመካክረንበት ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች በኩል መግለጫችንን ይፋ አድርገናል።

መምህራን ወር በደረሰ ቁጥር የቤት ኪራይ ምን እከፍላለሁ ልጆቼን ምን አበላለሁ እያለ በመጨናነቅ ለማስተማር በቂ ዝግጀት ስለማያደርግ የትምርት ጥራቱ ላይ ተፅኖ እያደረሰ ነው። "

(መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ የሚገልፀው ፅሁፍ በዚህ የተያያዘ ነው ፦ https://telegra.ph/University-11-29

የኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲዎች መምህራን እና ቴክኒክ ረዳቶች ማኅበር ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጠው ቃል  በዩኒቨርሲቲዎች መምህራን የፊታችን ሰኞ ኅዳር 26 ቀን/2015 ይደረጋል የተባለውን የሥራ ማቆም አድማ
እኔ አልጠራሁትም ሲል አስታውቋል።

ፕሬዜዳንቱ ዶክተር በፍቃዱ ዘለቀ ፤ የመምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አላቀረበም ብለዋል። ተናግረዋል።

ዶክተር በፍቃዱ ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ ሲሆን የሚመሩት ማኅበር ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረቡት 14 ጥያቄዎች በእርግጥም ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች መሆናቸውን ቢያረጋግጡም የሥራ ማቆም አድማ ግን አልጠራንም ሲሉ ገልጸዋል።

ማኅበሩ ይህንን ያደረጉት " የማናውቃቸው የተደራጁ አካላት ናቸው " ብሏል። ይህን ያደረጉ ያላቸውንም አካላት እንደሚከስ ለዶቼቫለ ሬድዮ አሳውቋል።  

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ " መምህራን የሚያነሷቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ለመፍታት ከመምህራን ማህበር ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑን " ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ትላንት ለህ/ተ/ም/ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተናግረዋል።

መምህራኑ ባነሱት ጉዳይ አስተያያታቸውን ለቲክቫህ  የሰጡት የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል በበኩላቸው ፤ መመህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችን ህጋዊ ከሆነው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጋር ብቻ በመነጋገር የሚፈታ መሆኑን አመልክተዋል።

@tikvahethiopia