TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ItsMyDam🇪🇹

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ለግድቡ ድጋፍ ማድረጋቸው ተጠናክሮ መቀጠሉን የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ም/ቤት ፅ/ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሃይሉ አብረሃ ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፥ በቅርቡ በውጭ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለማሰባሰብ ታስቦ በተሰራው ዘመናዊ የሃብት ማሰባሰቢያ ሥርዓት (www.mygerd.com) አማካኝነት ከ132 ሺ ዶላር በላይ ተሰበብስቧል ብለዋል።

ገንዘቡ የተገኘው ከ1 ሺ 29 ለጋሾች መሆኑንም ገልፀዋል።

በድረገፁ ከሚደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ በተጨማሪም #የቴሌብር የሃብት ማስባሰቢያ ተከፍቶ እስካሁን 30 ሺ ብር መሰብሰቡን አቶ ኃይሉ አብርሃ ተናግረዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ከ15 ቢሊዮን 729 ሚሊዮን ብር በላይ ከሕዝቡ መሰብሰቡን ተጠቁሟል።

በሌላ መረጃ ፦ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ24 ሰዓት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ተሰብስቧል።

በ24 ሰዓት የተሰበሰብው 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሲሆን በጎፈንድሚ በኩል ነው። ጎፈንድሚው በድር ኢትዮጵያ በኩል ከ1 ወር በፊት የተከፈተ መሆኑን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን 1,005,060 የአሜሪካ ዶላር ተሰብስቧል።

@tikvahethiopia