TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ?

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፤ በውስጡ ባለው #ሙስና እና ብለሹ አሰራሮች ምክንያት እጅግ በርካቶች ይማረሩበታል፤ በተደጋጋሚ ጊዜ የዚህ መስሪያ ቤት ጉዳይ ቢነገርም ችግሩ ግን ዛሬም ድረስ ሊቆም አልቻለም።

ዜጎች #በህጋዊ መንገድ ማግኘት ያለባቸውን አገልግሎት በሙስና ሰንሰለት በተጣመሩ አካላት ምክንያት ከፍተኛ ክፍያ እንዲከፍሉና ከሌሎች በፊታ ያለ አንዳች ወረፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል።

በዚህ መስሪያ  ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ የሚማረሩ፣ የሚበሳጩ እና እንግልት የደረሰባቸው በርካቶች ናቸው።

ከሰሞኑን ደግሞ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣብያ (ኢቲቪ) አንድ የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራ ሰርቶ አየር ላይ አውሎ ነበር።

በዚህ የምርመራ ስራም በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ውስጥ ፦

-   በፓስፖርት እድሳት እና ከአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ዜጎች ለሕገ-ወጥ አሠራር ተጋላጭ ሆነዋል።

- በሕጋዊ መንገድ ከ6 ሺህ 500 ብር በታች በሆነ ወጪ መጨረስ የሚቻለውን ፓስፖርት እስከ 40 ሺህ ብር በመክፈል አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ተረጋግጧል።

- ዜጎች መብታቸው ለሆነው አገልግሎት ሕገ-ወጥ ክፍያ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ ፤ ተቋሙ ባለበት አካባቢ እስከ ውስጥ ድረስ የተያያዘ የሙስና ሰንሰለት አለ።

ለመሆኑ ይህ ተቋም ይህን ሁሉ ችግሮች ለመቅረፍ ምን እያደረገ ነው ?

ቃላቸው ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የሰጡት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳሬክተር አቶ ብሩህተስፋ ሙሉጌታ  ፦

" ከ33 በላይ የተቋሙ ሠራተኞች ላይ የሥነ -ምግባር እርምጃ ቢወስድም ዛሬም ግን በሙስና እና በብልሹ አሠራር እየተፈተንን ነው።

ዜጎች በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ቅሬታ ካላቸው ከቅሬታ ሰሚ ዴስክ አንሥቶ እስከ ተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ድረስ በመገናኘት ቅሬታቸውን ቢያሰሙ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን። 

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም 95 በመቶ የሚሆነው ከፓስፖርት ሕትመት ጋር ተያይዞ ያሉ ግብዓቶች ጭምር በሀገር ውስጥ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ሥራዎች ተጠናቀዋል።

አገልግሎቱ እንዲጓደል የሚያደርጉ የተቋሙ ሠራተኞች በቅርብ በሚካሄድ የአደረጃጀት ሪፎርም ላይ ይጋለጣሉ እርምጃም ይወሰድባቸዋል። " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Afar

" ከጨው ፓለቲካ ጋር በተያያዘ ከ1,700 በላይ ሰዎች ታስረዋል " - የዶቢ ጨው አምራቾች ማኅበር

" ከጨው ፓለቲካ ጋር በተያያዘ ከ1,700 በላይ ሰዎች ታስረዋል" ሲል በአፋር ክልል የሚገኘው የዶቢ ጨው አምራቾች ኃላ/የተ/የግል/ሕብረት ሽርክና ማኅበር ገለጸ።

ሰዎቹ የታሰሩት የት ማረማያ ቤትና ለምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበለት ጥያቄ ማኅበሩ፣ " የታሰሩት በሰመራ ማረሚያ ቤት ነው፣ የታሰሩበት ምክንያት ደግሞ ጨው ለማምረት በመከልከላቸው ቅሬታ ሲያቀርቡ ነው " ብሏል።

ማኅበሩ እንዳስረዳው ፤ 409 አባላቱ ጨው እንዳያመርቱ በመንግሥት መታገዳቸውን፣ የታገዱበት ምክንያትም እንዳልተነገራቸው ነው።

የሚኅበሩ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሁሴን አሊ የማኅበሩ አባላት በችግር ላይ መሆናቸውን ገልጸው፣ በክልሉ ብዙ #ሙስና እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ፤ በጨው ማምረት ሥራ የተሰማሩት በክልሉ የሚገኙ አመራሮች ብቻ ናቸው ብለዋል።

የማኅበሩ አባላት በተናጠልና በጋራ እንደገለጹት ፣ ክልከላው እንዲነሳ  ለሚመለከታቸውን የክልሉ የመንግሥት አካላት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም አጥጋቢ ምላሽ አላገኙም።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ በማኅበርና በየፊናቸው በሰጡት ገለጻ፣ በዚህ ሳቢያ በአፋር ክልል ግጭት ከመፈጠሩ በፊት የፌደራል መንግሥት አፋጣኝ መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ጠይቀዋል።

ከዚህም ባሻገር ጨው አምራቾች ምርታቸው የሸጡበት የስድስት ወራት ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ፣ የማኅበሩ አባላት በየፊናቸውና በማኅበር በሰጡት ገለጻ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፤ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ " ተርበናል " ብለው የሚጠይቁ ሰዎች በፓሊስ እየታሰሩ መሆኑን ማኅበሩ አስታውቋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ሰዎች በርሃብ እየሞቱ ነው ብለው፣ ለአብነትም በአፍዴራ ሰሞኑን ሁለት ሰዎች ሞተዋል ብለዋል።

ዶቢ የጨው አምራች ማኅበር ኃላ/የተ/የግል/ሕብረት ሽርክና ማኅበር በአፋር ክልል በ1992 ዓ.ም በባህላዊ የምርት አሰራር የተመሰረተና በሂደት ወደ ዘመናዊነት የተሸጋገረ 409 አምራች አባላት ያሉት ማኅበር ነው።

መረጃውን የአዲስ አበባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው ያዘጋጀው።

@tikvahethiopia
#ሙስና📈

" ዛሬ እኮ አገልግሎት ተፈልጎ ክፍለ ከተማ ቢኬድ በግልፅ የሚጠየቅበት (ጉቦ) ሁኔታ ላይ ደርሰናል። ከዚህ በፊት እንደውም በካኪ ታሽጎ ፣ ተደብቆ ነው ሲሰጥ የነበረው "

በኢትዮጵያ ውስጥ #ሙስና ከመቀነስ ይልቅ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ፣ የሚፈፀምበትም መንገድ እየተራቀቀ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፤ የትራንስፖርት ፣ የመሬት፣ የካርታ፣ የግንባታ ፍቃድ ፣ የመታወቂያ ... ሌሎችም አገልግሎት ለማግኘት ሲኬድ ከእጅ መንሻ ጋር እንደሆነ መረዳቱን ገልጿል።

✦ የተቋሙ ዋና እምባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ምን አሉ ?

- በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ሙስና እንደሚፈፀም ተገልጋዮች ተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርባሉ።

- ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት የሚጠየቁት ጉቦ በድብቅ ሳይሆን በግልፅ ነው።

- ለሙስና ተጋላጭ ናቸው የተባሉ ተቋማት ተለይተዋል እየተባለ ቁጥጥሩ ለምን እንደላላ ግራ የሚያጋባ ነው።

- " ዛሬ አገልግሎት ፈልገህ ክፍለ ከተማ ብትሄድ እኮ በግልፅ የሚጠየቅበት (ጉቦ) ሁኔታ ላይ ደርሰናል። ከዚህ በፊት እንደውም በካኪ ታሽጎ ምናምን ነው ሲሰጥ የነበረው፤ ዛሬ በካኪ ታሽጎ የሚሰጠውን ገንዘብ እዛው ፊትለፊት ላይ የሚቀዱ የመንግሥት ሰራተኞች ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው ፤ ምንም እንኳን የየስራ ባህሪያቸው ቢለይም። "

- የስርዓት ለውጥ ነው የሚያስፈልገው፤ ሙስናን መሸከም የማይችል፣ ሙስናን ማስተናገድ የማይችል ስርዓት ፣የህግና የተቋም ስርዓት ነው መዘርጋት ያለበት።

- የስነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተሰጠው ኃላፊነት ሙስናን ለመከላከል በቂ አይደለም። ይህ ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለአስፈፃሚው አካል ነው፤ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ መስራት የሚያስችለው አይደለም። የተቋሙ ኃላፊዎች የሚሾሙት በአስፈፃሚው አካል ነው፤ ተጠሪናታቸውም ለዛ አካል ነው እንጂ ለምክር ቤት አይደለም። ሌላው እየሰራ ያለው መከላከል ላይ ነው፤ የህግ ማስከበሩን ለፍትህ ሚኒስቴር ነው የተሰጠው አሁን ካለው ከፍተኛ የሙስና ችግር አንፃር የህግ ማስከበሩንም የመከላከሉንም ስራ መስራት የሚችል ጠንካራ ኮሚሽን ማቋቋም ያስፈልጋል።

- ጠንካራ ኮሚሽን ባልተቋቋመበት ሁኔታ ኮሚቴ እያቋቋሙ ሙስናን የመከላከል የሚቻልበት ሁኔታ የለም።

◾️የህግ ባለሙያ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ምን ይላሉ ?

- ሙሰኞች ላይ የሚወሰድ እርምጃ ጠንካራ ስላልሆነ ሙስና ከመቀነስ ይልቅ እንዲጨምር ሆኗል።

- የፖለቲካ መዋቅሩ በራሱ አጥፊዎች እንዳይጠየቁ እድል የሚሰጥ ነው። ብሄርና ትውውቅን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በአጥፊውና በጠያቂው መካከል ልዩነት እንዳይኖር ሆኗል።

- " ሰዎች ሙስና ሰርተው ሲያጠፉ በግልፅ ማስረጃ ቀርቦባቸው ጥፋተኛ መሆን ሲገባቸው እንደውም ከለላና ሽፋን ሲያገኙ ፣ ከበላበት ቦታ ወደሌላ ቦታ ዘወር ሲል ፣ ሃብትና ንብረት እንዲያገኙ ሲመቻችላቸው ይታያል። ይሄ ሁሉ የፖለቲካ ስሪቱ ነው። የፖለቲካ ስሪቱ ብሄርን መሰረት ያደረገ መሆኑነው። ይሄ ብሄርን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት የሰላ ትግል እንዳይደረግና ተጠያቂነት እንዳይመጣ ያደርጋል። "

- የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን መክሰስም ሆነ የመመርመር ስልጣን ቢሰጠው አሁን ካለው ስራ የተሻለ ማድረግ አይችልም። ለ16 ዓመታት ይሄ ኃላፊነት ተሰጥቶት የሰራው ስራ ታይቷል።

- አሁን የሚበጀው አጥፊዎች የሚጠየቁበትን ህግ ማጠናከር ነው።

- " ሰው በዚህ ሰመን በካልኩሌሽን መታሰር ጀምሯል። ለምሳሌ አንድ የሙስና ወንጀል የፈፀመ ሰው 10 ሚሊዮን ብር ቢያገኝ በቀላሉ 10 ዓመት ቢታሰር / ቢወሰንበት ምን ብሎ ያስባል ' ይሄን 10 ሚሊዮን ብር በ10 ዓመት ላፈራው አልችልም ደግሞ ማንኛውም ታራሚ አመክሮ ስላለው በ7 ዓመት / በ6 ዓመት ብወጣ ይሄን 10 ሚሊዮን ብር መብላቱ / መመዝበሩ የተሻለ ነው ፤ ምክንያቱም በ6/7 ዓመት ውስጥ ላፈራው አልችም ' ብሎ ሰው በካልኩሌሽን መታሰር የጀመረበትና የደረሰበት ዘመንና ሁኔታ ላይ ደርሰናል "

- መፍትሄው ሙስና የሚፈፅሙ አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ ህጉን ጠንካራ ማድረግ ብቻ ነው።

🔹በስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን የጥቅም ግጭት መከላከል መሪ ስራ አስፈፃሚ መስፍን በላይነህ ምን ይላሉ ?

- የሙስና ጉዳይ በጣም እየጎላ መጥቷል።

- ሁሉም ዘርፍ ከሙስና ተግባር የፀዳ አይደለም ፤ ግን ደረጃው ይለያያል።

- የእኛ ኮሚሽን ሙስናን መከላከል እንጂ ከተፈፀመ በኃላ የመመርመር፣ የመክሰስና የማገድ ኃላፊነት አልተሰጠውም። ዋናው ተልዕኮ የስነምግባር ትምህርትን ማስተማር ነው።

- በአብዛኛው ዓለም ላይ ሶስቱንም ማለትም፦
• የማስተማር፣
• የመመርመር ፣
• የመክሰስ አውድ ይዞ ነው የሚኬደው ፤ እኛ ሀገርም ተሞክሯል ከ1993 - 2008 ተሞክሯል። ከ2008 በኃላ የሙስና ወንጀል ምርመራ ብሎም ክሱ ወደሌላ አካል ተለልፋል። ቅንጅት ከተፈጠረ ይህ መሆኑ ችግር የለውም። ፖሊስ ይመረምራል፣ አቃቤ ህግ ይከሳል፣ ፍርድ ቤት ፍርድ ይሰጣል። ህብረት ያስፈልጋል። ቅንጅቱ ግን ጠንካራ አይደለም።

- ብዙ ሀገራት ላይ ይህን ዘርፍ በአንድ ተቋም ነው የሚመሩት ፤ እኛ ሀገር በተለያየ ተቋም ነው የሚሰራው ይህንን የሚመሩ አካላት እንደ አንድ ተቋም ሊሰሩ ይገባል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ / ጋዜጠኛ ያሬድ እንዳሻው ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለፀ። እንዚህ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት ፦ - ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ - ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ - ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተውጣጣ ግብረ-ኃይል ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ ከቆየ በኃላ ነው ተብሏል። ተጠርጣሪዎቹ ፤ ተገልጋዮች በመደበኛ…
#ሙስና #ICS

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ኃላፊ የነበሩት ታምሩ ግንበቶን ጨምሮ 60 የተቋሙ ባልደረቦች 15 የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው።

የተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር ከነበሩት ታምሩ ግንበቶ በተጨማሪ የውጭ ዜጎች ቁጥጥር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጅላሉ በድሩ የኬላዎች ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ቦጋለም ይገኙበታል።

በፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ዐቃቤ ሕግ በክሱ የእያንዳንዱ ተከሳሽ የወንጀል ተሳትፎን ዘርዝሯል።

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ፦

* ፎርቲን አቬጋ በተባለ ድርጅት የሚሠሩ 12 ግብፃዊያን ለቪዛ ቅጣት ይከፍሉ የነበረውን 24 ሺህ ዶላር በራሳቸው ትዕዛዝ 14 ሺህ ዶላሩን በመቀነስ በመመሪያው መሠረት ባልተገባ መንገድ የተቀነሰውን በዶላር መክፈል ሲገባቸው በኢትዮጵያ ብር እንዲከፍሉ በማድረግ መንግሥት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል።

* ሀይንፊን፣ ሀድዙ የተሰኙ የቻይና ኩባንያ ድርጅት ውስጥ የሚሠሩ ብሎም ሻሎም አስመላሽ ኪዳኔ እና ነጃት ዓሊ መሐመድ ለቪዛ ቅጣት በዶላር መክፈል ከነበረባቸው 4 ሺህ ዶላር ያህል መመሪያ በመጣስ እንዳይከፍሉ በማድረግ መንግሥት ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

* የማይገባ ጥቅምን ለማግኘት በማሰብ ተገቢ ማጣራት ሳይከናወን ነዋሪነታቸው በሶማሊ ላንድ ሐርጌሳ ለሆኑ 68 ግለሰብ የኢትዮጵያ ፓስፖርት እንዲሰጥ በማድረግ የሀገርን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት የፈፀሙ በመሆኑ ሥልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከስሰዋል።

1ኛው ተከሳሽ ታምሩ ግንበቶ እና 2ኛ ተካሽ ጅላሉ በድሩ በወንጀል ከሀገር እንዳይወጡ ትዕዛዝ ለተላለፈባቸው 6 ቻይናውያን መካከል ዙ ጂያን እና ዛንግፒንግል የተሰኙ ሁለቱ የተጣለባቸው እግድ ተነሥቶ የመውጫ ቪዛ በአስቸኳይ እንዲሰጣቸው በማድረጋቸው ዐቃቤ ሕግ ሁለቱንም ግለሰቦች በፈፀሙት ሥልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል ከሷቸዋል።

ዐቃቤ ሕግ የእያንዳንዱን ተከሳሽ የወንጀል ተሳትፎን በመጥቀስ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የሙስና ወንጀል ጉዳይ ችሎት አቅርቧል።

በተከሳሾች ስም ፦

- 14,523,647.36 ብር (14 ሚሊዮን 523 ሺህ 647 ከ36 ሣንቲም)
- አክሲዮን 383,000.00 ብር (383 ሺህ)
- 8 ቤቶች ያሉ ሲሆን በፍትሕ ሚኒስቴር በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል በኩል ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ማፍራት እንዲሁም በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅርብ ወንጀል ምርመራ እየተጣራ እና ምርመራ እየቀጠለ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

ክሱን በንባብ ለማሰማት ፍርድ ቤቱ ለሰኞ ታኅሣሥ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 " አሁን ላይ ያሉ ችግሮች ምፍትሄ እስካላገኙ  ስለ ምርጫ ማሰብ #ቀልድ ነው " - አቶ ግርማ በቀለ የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሕብር) ሊቀ መንበር አቶ ግርማ በቀለ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቆይታ አድረገዋል። Q. የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት ጥሰትን በተመለከተ ስለሚነሱ ጉዳዮች የፓርቲዎ ግምገማ ምን ይላል ?   አቶ ግርማ…
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ #እንደ_ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ ? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እያቀረበ ያለውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች በመቀጠል ጎጎት ፓርቲን አነጋግሯል።

የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጀሚል ሳኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

Q. ከዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት አንፃር የፓርቲዎን ግምገማና መፍትሄውን ቢገልጹ ?

አቶ ጀሚል ሳኒ፦

“ ሰዎች በተደጋጋሚ ሕይወታቸውን እያጡ ነው። በዋና ከተማዋ ሲይቀር ሰዎች እየታሰሩ፣ እየታገቱ ነው።

የትኛውም ዜጋ የደህንነት ስሜት እየተሰማው አይደለም። 

መንግስት #በዋነኛነት የተመሠረተበትና እንዲሰራው ኃላፊነት የተሰጠው ስራ ከየትኛውም ቅድሚያ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ የተዘነጋ የሚመስልበት ዘመን ላይ ነን።

በመወያየትና በመነጋገር ጦርነትን ማስቆም ይገባል።

ሰላምን ከማስፈን ይልቅ #ስልጣንን_የመጠበቅ ፣ የፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራት ነው አብዛኛው አቅም እየባከነ ያለው።

ከዚያ ይልቅ አገሪቱን በሚያሻግሩ ሀሳቦች ላይ አተኩሮ መስራት ያስፈልጋል።

ያለፉትን ዘመናት እንደ ቅንጦተ እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው። ”

Q. በሙስና ተዘፍቀው ስለሚገኙ ባለስልጣናት እንዲሁም በአጠቃላይ ስለብልሹ አሰራር ፓርቲዎ ምን ይላል ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ አሁን ላይ #ሀዘኔታዎች_የጠፉበት ፣ ሌላው ይቅርና የዜጎች ቤቶች ‘ሕገ ወጥ ናቸው’ ተብለው ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች ላይ ገንዘብ የሚጠየቅበት ሁኔታ ነው ያለው። 

ከኢትዮጵያ Norm ሁላ ያፈነገጠበት ወቅት ላይ ነው ያለነው። በአብዛኛዎቹ መስሪያ ቤቶች የተለመደውን አይነት አሰራር ከመስራት ይልቅ ከእግሮች እጆች እየቀደሙ ነው።

#ሙስና_በግልጽ_እየተጠየቀ ፣ ቢሮ ውስጥ ሥራ አስፈጻሚዎች #በግልጽ_ድርድር እያደረጉበት ያለበት ሂደት ነው አሁን ያለው።

አለ የተባለ የትኛውም ችግርን ለመቅረፍ ላይከብድ ይችላል ፤ ነገር ግን ከተንሰራፋ የትኛውንም ችግር ልቅረፍ ማለት የማይታሰብ ይሆናል። 

ሙስና የሀገር ተቋርቋሪነትን፣ ስሜትን ያጠፋል።

እያየነው ያለውም ይሄው ነውና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።”

Q. እንደ ፓርቲ የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ የምስረታ ጉባዔ ባደረግንበት፣ የጉባዔውን ውጤትና የምርጫ ቦርድ ኮሮጆ ጭምር ይዘን በነበረበት ሰዓት ነው እስር የተጀመረው። ክፍለ አገርም አዲስ አበባም እስሮች አሉ። 

በአባል ደረጃ አንድ የፓርቲው አባል ከ5 ወራት በላይ ያለ ክስና ዋስትና በእስር ላይ ይገኛሉ። ከአባላቶች እስራትና ተንቀሳቅሶ ከመስራት ጋር ዘተያያዘ ያለፉትን ዘመናት እንደ ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው።

ፓርቲውን የሚደግፉ አባላት #ወጣቶች_እየተላኩ ማስፈራሪያ ያደርሱባቸዋል።

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ሕገ መንግስቱን ያልከተለ በመሆኑ ምስረታው እንዲታገድ፣ ኢ - ሕገ መንግስታዊ ስራዎች በሰሩ ባለስልጣናት ላይ የመሰረትነው ክስ በቀጠሮ እየተጉላላ ነው ያለው። ”

Q. ሕዝቡ በኑሮ ውድነቱ ተማሯል። ለዚህም “ መንግስት ትኩረት አልሰጠም  ” የሚሉ ወቀሳዎች ይቀርባሉ። የፓርቲዎ ግምገማ ምንድን ነው ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ የኑሮ ውድነት በራሱ የሚፈጠር ነገር አይደለም። እስካሁን ከላይ የተነጋገርንባቸው ነገሮች ናቸው እየገፉ የሚያመጡት። 

አንዲት አገር #በጦርነት ላይ ሆና ሚሊዮን ዶላሮችም ለጦርነት እያወጣች ፣ አርሶአደር ማምረትና በሰላም ወጥቶ መግባት ባልቻለበት ፣ የመልካም አስተዳደር ፣ የአቅም ፣ የብቃት ጉዳዮች የመጨረሻ ውጤታቸው የኑሮ ውድነቱ ማምጣት ነው።

እነዚህን ችግሮች ማጥፋት፣ መቀነስ ካልተቻለ የኑሮ ውድነቱን ማረጋጋት፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ማስፈን አይቻልም። ”

Q. ስለምርጫ ያላችሁ አስተያዬት ምንድን ነው ? በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?


“ ከምርጫ ጋር በተገናኘ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራው፣ አጀንዳውም የሚያዘው ከሚደረገው #የፓርላማ እና #የክልል_ምክር_ቤቶች ጋር በተገናኘ ነው። 

ይሄ ስርዓቱን ለመቀየር የሚያስችል ብቸኛው መንገድ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ምርጫ በየአካባቢው ማድረግ ያስፈልጋል። የአካባቢ ምርጫ የተደረገው ከ8 ዓመታት በፊት ነው።

የአካባቢ ምርጫ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

አሁን ባለንበት ሁኔታ ላይ #ምርጫ ሊደረግ ይችላል ብሎ ማለት ትንሽ አዳጋች ነው። ”

◾️በቀጣዩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፓርቲ የሰጠው ቃል ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia