TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Uganda

ባለፉት 24 ሰዓት በዩጋንዳ የ398 ሰዎች ናሙና ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከኮሮና ቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን የዩጋንዳ ጤና ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UGANDA

በዩጋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት 231 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ተግኝተዋል። በአሁን ሰዓት በዩጋንዳ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተያዙ ሰዎች ቁጥር 52 ነው።

ምንጭ፦ ዩጋንዳ ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UGANDA

በዩጋንዳ ለሁለተኛ ቀን አዲስ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝ እንዳልተመዘገበ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ባለፉት 24 ሰዓት 150 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ትላንት የ231 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ነፃ ሆነው መገኘታቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UGANDA

ባለፉት 24 ሰዓት በዩጋንዳ ሁለት መቶ አስራ አራት (214) የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መያዙ ተረጋግጧል። በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የታዙ ሰዎችም 53 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UGANDA

11 የጭነት መኪና ሹፌሮች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ዩጋንዳ በአንድ ቀን ተጨማሪ 11 የኮቪድ-19 ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች። ቫይረሱ እንደተግኘባቸው የተረጋገጡት ሁሉም የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ናቸው።

ከአስራ አንዱ (11) ስድስቱ (6) ታንዛኒያውያን የጭነት መኪና ሹፌሮች ሲሆኑ በሙቱኩላ በኩል የገቡ ናቸው።

አምስቱ (5) ኬንያውያን የጭነት መኪና ሹፌሮች ሲሆኑ ሶስቱ (3) በማላባ ፤ ሁለቱ (2) ደግሞ በቡሲያ በኩል ነው የተገቡት።

በአሁን ሰዓት በዩጋንዳ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 74 ደርሷል። 46 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ሀገሪቱ በተለይ በደንበር አካባቢዎች ፤ በጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥታ ጥብቅ ቁጥጥር ብታደርግም ከቫይረሱ ልታመልጥ አልቻለችም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UGANDA : የኡጋንዳ የፀረ ሙስና መ/ቤት በሀገሪቱ ያለውን ሙስና ለመቆጣጠር ልጆችን በመጠቀም አዲስ ዘዴ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አሳወቀ።

መ/ቤቱ ኃላፊ ቤቲ ካምያ ለአውሮፓ ሕብረት የዲፕሎማቶች ቡድን ሲናገሩ እንደተሰማው ፤ ወላጆችን በልጆቻቸው በኩል በመከታተል አዲስ የሙስና መቆጣጠሪያ መንገድ እንዳለ አመለክተዋል።

ይኸው ዘዴ ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲከታተሉ የሚደረግበት እንደሆነና ወጪ ቆጣቢ መሆኑንም ነው ያመለከቱት።

አዲሱ ሙስናን የመከታተያ መንገድ ትኩረቱን በተማሪ ልጆች ላይ ያደረገ ሲሆን በተለይ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያሉ ልጆች ሕገወጥ ገንዘብ ምን እንደሆነ እንዲያውቁና "ወላጆቻቸው ያላቸው ቅንጡ ቤትና መኪና እንዲሁም ሌሎች ወጪዎች በሚያገኙት ደሞዝ የሚሸፈኑ መሆናቸውን እንዲጠይቁ እንፈልጋልን" ቤቲ ካምያ ተናግረዋል።

በተጨማሪ ከፍተኛ ገንዘብ በሚከፈልባቸው ትምህርት ቤቶች ያሉ መምህራን 10 ዓመት ለሆናቸው ተማሪዎች የአባታቸውን ስም፣ የት እንደሚሰራ፣ የሥራው ኃላፊነት፣ የሚያሽከረክረው መኪና ዋጋ እና የቤታቸውን ፎቶ የሚያሳይ የቤት ሥራ እንዲሰጡ በማድረግ የሙስና ክትትል ለማድረግ እንዳቀዱ ኃላፊዋ ተናግረዋል።

ነገር ግን አንድ ተማሪ ከታዘዘው የቤት ሥራ ላይ የሚገኝን መረጃ ለፀረ ሙስና ባለሥልጣን አሳልፎ መስጠት ይቻላል ወይ የሚለው ጥያቄ ግልጽ መልስ አልተሰጠበትም።

ባለሥልጣኗ መሥሪያ ቤታቸው ከአገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ሙስናን በሚመለከት ውይይት እንዲያደርጉ ይበረታታሉ ማለታቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Uganda: ዛሬ በኡጋንዳ በደረሱ 2 የሽብር አደጋዎች 3 ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ቆሰሉ፡፡

ካምፓላ ሁለት ቦታዎች በደረሱ የአጥፍቶ ጠፊዎች የሽብር ጥቃት ይ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ፖሊስ አስታቋል፡፡

በአደጋው ከቆሰሉት 33 ሰዎች ውስጥ አምስቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተገልጿል፡፡ የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል፡፡

በካምፓላ ሁለት የገበያ ማዕከላት ላይ ደረሰ የተባለው ይህ የዛሬ ረፋድ የሽብር ጥቃት በአገሪቱ ፓርላማ መግቢያ አካባቢ ነው የተፈጸመው፡፡

የአገሪቱ ፖሊስ በበኩሉ አደጋው በሁለት የአገር ውስጥ የሽብር ቡድን አባላት አማካኝነት በተመሳሳይ ሰዓት በተለያዩ ቦታዎች ፍንዳታው መድረሱን ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ይሁንና እስካሁን በሽብር ድርጊቱ ዙሪያ ሃላፊነት የወሰደ አካል እንደሌለ የተገለጸ ሲሆን የአገሪቱ ፖሊስ ድርጊቱን እየመረመርኩ ነው ብሏል፡፡

ከ1 ወር በፊት በካምፓላ ከተማ ባለ አንድ ሬስቶራንት ውስጥ በደረሰ ተመሳሳይ የሽብር አደጋ ሁለት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ሀላፊነቱን አይኤስ አይ ኤስ ለድርጊቱ ሃላፊነት ወስዶ ነበር፡፡

በዚሁ ዓመት መስከረም ወር መጨረሻ ቀናት ላይ አንድ አጥፍቶ ጠፊ የሽብር ቡድን በፈጸመው ጥቃት እራሱን ገድሎ በርካቶችን ማቁሰሉ አይነጋም

Credit : Al AIN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Uganda: ዛሬ በኡጋንዳ በደረሱ 2 የሽብር አደጋዎች 3 ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ቆሰሉ፡፡ ካምፓላ ሁለት ቦታዎች በደረሱ የአጥፍቶ ጠፊዎች የሽብር ጥቃት ይ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ፖሊስ አስታቋል፡፡ በአደጋው ከቆሰሉት 33 ሰዎች ውስጥ አምስቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተገልጿል፡፡ የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል፡፡…
#UGANDA

የኢትዮጵያ መንግስት በዩጋንዳ መዲና ካማፓላ ከተማ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዘ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ በትናንትናው ዕለት በካምፓላ ሁለት ቦታዎች ላይ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት በንጹሃን ዜጎችና ፖሊስ ባልደረቦች ላይ በደረሰው የሞትና የአካል ጉዳት ማዘኑን ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት በጥብቅ እንደምታወግዝም ነው በመግለጫው የተመላከተው።

ኢትዮጵያና ዩጋንዳ በጋራ ሽብርተኝነትን የመዋጋት ልምድ እንዳላቸው በመጥቀስ ጥቃቱ ዩጋንዳም ሆነ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ሽብርተኝነትን የበለጠ በቁርጠኝነት ከመዋጋት እንደማያግዳቸው የኢትዮጵያ መንግስት ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለኡጋንዳ ህዝብና መንግስት እንዲሁም ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ/ የውጭ ጉዳዩ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia