TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አንቶኒ ብሊንከን ዛሬ ናይሮቢ ይገባሉ።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከዛሬ ጀምሮ ሦስት የአፍሪካ አገራትን ይጎበኛሉ።

ሚኒስትሩ ኬንያ፣ ናይጄሪያና ሴኔጋልን ነው በይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው የሚጎበኙት።

ብሊንከን ጉብኝታቸው የ6 ቀናት ሲሆን ጉብኝታቸው ከናይሮቢ የሚጀምሩ ሲሆን ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመገናኘት በኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ እና በሱዳን ያሉ ጉዳዮችን ጨምሮ በሌሎች ርዕሶች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኬንያው ፕሬዜዳንት ትላንት ኢትዮጵያ ነበሩ።

የኬንያ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ጉብኝቱን በማስመልከት ኡሁሩ ኬንያታ ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር መወያየታቸውን ገልጿል።

ኬንያታ እሁድ ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ ለሰዓታት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው ማምሻውን ወደ ናይሮቢ መመለሳቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#ይከተቡ

ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት እድሜያቸው 12 ዓመትና ከዚያን በላይ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ-19 ክትባት በዘመቻ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አሰታወቀ።

ከዛሬ ሰኞ ህዳር 6 እስከ ህዳር 15 ጀምሮ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ እድሜው ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ በአቅራቢያቸው በሚገኝ ጤና ጣቢያ በመሄድ ክትባቱን መውሰድ እንደሚችሉ የቢሮ ሃላፊው ዶክተር ዮሃነስ ጫላ አስታውቀዋል።

ከጤና ጣቢያዎች በተጨማሪም የክትባቱን ተደራሽነት ለማስፋት በትላልቅ የገበያ ቦታዎች ፣ ሞሎች ፣ በባንኮች ፤ በትራንሰፖርት መናህሪያዎች ፤ በኢንዱስትሪ ፓርክ እና በሌሎች በተመረጡ ቦታዎች ይሰጣል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ እስከአሁን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች የኮቪድ 19 ክትባት የተሰጠ ሲሆን ለ10 ቀናት በሚካሄደው የክትበት ዘመቻ ከ1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ::

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የክትባት ቡድኖች መደራጀታቸውን ዶክተር ዮሃንስ ጫላ ገልጸዋል፡:

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
#Legetafo : በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ከተጠርጣሪ ወንጀለኞች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ዘግቧል።

የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ክላሽንኮቭ ፣ ሽጉጥ፣ ቦንብ፣ የተለያዩ ጥይቶችና የሠራዊት ዩኒፎርም ከተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዉ ፖሊስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#DireDawa

በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ እና ገጠር የሚኖር ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኝ የጦር መሳሪያ በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ እና ገጠር በሚገኙ በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር ቀርቦ ማስመዝገብ እንዳለበት የድሬዳዋ ፖሊስ ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ዜጎች እጃቸው ላይ የሚገኝ ጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ የተቀመጠው ቀነ ገደብ ዛሬ ህዳር 6 ቀን 2014 ዓ/ም ይጠናቀቃል።

@tikvahethiopi
" ጅቡቲ በጎረቤት ሀገር ላይ ለሚፈጸም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት መጠቀሚያ ሆና አታገለግልም " - ማህሙድ አሊ ዩሱፍ

የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ሀገራቸው ጅቡቲ በጎረቤቶቿ ላይ ለሚፈጸም ጣልቃ ገብነት ግዛቷ መጠቀሚያ እንደማይሆን አሳውቀዋል።

ሚኒስትሩ ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ይህንን ያለቱ ትላንት በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ነው።

ሚኒስትሩ ሀገራቸው ጅቡቲ " በጎረቤት አገር ላይ ለሚፈጸም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት መጠቀሚያ ሆና አታገለግልም " ብለዋል።

ይህ የሚኒስትሩ አስተያየት የመጣው አንድ ጂቡቲ ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ከፍተኛ ወታደራዊ ጄነራል ዊሊያም ዛና ለቢቢሲ በኢትዮጵያ ቀውስ የሚከሰት ከሆነ የአሜሪካ ወታደሮች "ከእዚህ ምላሽ ይሰጣሉ" በማለት ከተናግሩ በኃላ ነው።

የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ "አንዳንዶች የጂቡቲ ግዛት በጎረቤት አገራት ላይ ለሚፈጸም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል" በማለት የጄነራሉን ንግግር ተከትሎ የተፈጠረውን ስሜት የጠቀሱ ሲሆን ይህ ግን እንደማይሆን አስረግጠው ተናግረዋል።

ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ፥ "ጅቡቲ ከጎረቤቶቹ ጋር ትስስር ያለው የጂቡቲ መንግሥት ይህ እንዲሆን አይፈቅድም" ገልፀዋል።

ለቀይ ባሕር ስልታዊ መተላለፊያ በሆነችው ጂቡቲ ውስጥ የጦር ሰፈርና ወታደሮች ካሏቸው አገራት መካከል አንዷ የሆነችው አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ ቀውስ የሚፈጠር ከሆነ ወታደሮቿ ምላሽ እንደሚሰጡ ጅቢቲ ባሉት ጄነራሏ አማካኝነት ስንትናገር ነበር።

Credit - Mahmoud Ali Yossouf Twitter Page-BBC

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ 🇪🇹 ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ A350-900 በዱባይ ኤር ሾው 2021 ለእይታ ቀርቧል።

የዱባይ ኤር ሾው ከ1 ሺህ 200 በላይ ኤግዚቢሽን አቅራቢዎችና ከ148 በላይ ሀገራት ተወካዮች የሚሳተፉበት ትልቅ የአየር ትዕይንት ነው።

Credit : የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
ፎቶ : አየር ኃይል በኤር ፓሊስ ኮማንዶ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመርቋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በመጀመሪያ ዙር በኤር ፓሊስ ኮማንዶ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመርቋል።

ፎቶ ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#UN

UN በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ጦርነቱ እየተባባሰ ባለበት አካባቢዎች የነብስ አድን የሰብአዊ ዕርዳታ የሚውል 40 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ ገንዘብ ድጋፍ መመደቡን አስታውቋል።

የUN የርዳታ ሃላፊ ማርቲን ግሪፍትስ ፥ የገንዘብ ድጋፉ ትግራይ ክልልን ጨምሮ በጦርነቱ በተጎዱ የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል እና ድርቅ ለተከሰተበት ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል አስቀድሞ ምላሽ ለመስጠት ታስቦ የተለገሰ መሆኑን ተናግረዋል።

ነገርግን በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ለመደገፍ የሚያስፈልገውን የ350 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ ለሚከናወኑ የሰብአዊ ድጋፍ ተግባራት የ1.3 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ክፍተት እንዳጋጠማቸው ኃላፊው በመግለጫቸው አሳስበዋል።

ግሪፊትስ ፥ " በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብአዊ ቀውሱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሄዶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሕይወታቸው አደገኛ ጠርዝ ላይ ይገኛሉ " ብለዋል። በመላ ሀገሪቱ መሰረታዊ ፍላጎቶች እየጨመረ መምጣቱንም ገልጸዋል።

ለአስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቱ የተመደበው ገንዘብ 25 ሚሊዮን ዶላሩ አዲስ ጥሬ ገንዘብ ከUN ማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ፈንድ የተገኘ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን የቀረው 15 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ተቀማጭነቱን ሀገር ውስጥ ካደረገ የሰብአዊ ረድኤት ገንዘብ አቅራቢ የተገኘ መሆኑን ተናግረዋል።

ገንዘቡ በትግራይ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖች ከለላ እና የነብስ አድን ድጋፍ ይውላል ተብሏል።

የገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ በድርቅ በተጎዱት የደቡባዊ ሶማሌና የኦሮሚያ ክልሎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ጨምሮ እንደ ኮሌራ ያሉ የውሃ ወለድ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ለእንስሳት መኖ አቅርቦትና እንክብካቤ ስራዎች እንደሚውል መገለፁን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ጊዜያዊ_መታወቂያ !

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ መመሪያ ፥ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት መመሪያ አውጥቷል፡፡

* መመሪያው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia