TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አብዲ ኢሌ⬇️

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ባቀረቡት #የዋስትና ጥያቄ ላይ ለመወሰን #ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዛሬው እለት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመርን ጨምሮ፥ ወይዘሮ ራሃማ መሐመድ፣ አቶ አብድራዛቅ ሰህኒ እና አቶ ሱልጣን መሐመድ፥ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ተረኛ የወንጀል ችሎት መቅረባቸው ይታወቃል።

በዚህ ወቅትም የተለያየ የጤና እክል እንዳለባቸው በመጥቀስ፥ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ የዋስትና ጥያቄ ይፈቀድልን ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ የዋስትና ጥያቄውን በመቃወም በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለሚያካሂደው ምርመራ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም አቶ #አብዲ_መሐመድ_ዑመር በቀረበው የዋስትና ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ #ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

©EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አብዲ ኢሌ⬇️

ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አብዲ_መሐመድ_ዑመር ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሰጠ።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ነው አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ 3 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን #የዋስትና ጥያቄ #ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የፈቀደው።

በዚህም መሰረት የፖሊስን የምርመራ ውጤት ለመስማት ለመስከረንም 4/ 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አብዲ ኢሌ⬇️

ፖሊስ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር #አብዲ_መሐመድ ጨምሮ በሌሎች ተከሳሾች ላይ የጠየቀው ተጨማሪ 14 ቀን የምርምራ ጊዜ በፍርድ ቤቱ ተፈቀደለት።

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሐመድ ጨምሮ የሌሎች ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ እየተመለከተ ያለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት 19ኛ ተረኛ ምድብ ችሎት በተጠርጣሪዎች የቀረቡትን አቤቱታ ሰምቷል።

ተጠርጣሪዎቹ ቤተሰብ እይጠየቀን አይደለም ምግብና ህክምናም በአግባቡ እያገኘን አይደለም የሚል #ቅሬታ በጠበቆቻቸው በኩል እቅርበዋል።

መዝገቡ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች በአንድ የያዘ ነው እንደኃላፊነታችን መጠን ሊለያይ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል። የዋስትና መብታቸውም እንዲከበር እንዲሁ። ፍርድቤቱ የቀረቡት ጉዳዮችን በተመለከተ ፖሊስ ተገቢውን ማስተካከያ እንዲያደረግ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የተጠረጠሩበት ወንጀል የዋስትና መብት ስለማየሰጣቸው ይህን ጥያቄ #ውድቅ በማድርግ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። በመሆኑም ቀጣይ የቀጠሮ ጊዜ መስከረም 18 እንደሚሆን ፍርድቤቱ ወስኗል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አብዲ ኢሌ ከእስር ለማምለጥ ሞክረው ነበር‼️

የሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ከእስር ቤት #መስኮት ሰብረው ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ሲል ፖሊስ ገለጸ።

አቶ #አብዲ_መሐመድ ከሐምሌ 26 ቀን እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ፥ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሳቢያ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

አቶ አብዲ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀጠሮ ችሎት በቀረቡበት ወቅት፥ ለደህንነታቸውና ለጤናቸው ሲባል የፖሊስ ቢሮ ውስጥ ታስረው መቆየታቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ይሁንና አቶ አብዲ የታሰሩበትን ቢሮ መስታወት በመስበርና አንድ የጥበቃ አባልን ጉሮሮ በማነቅ ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ብሏል ፖሊስ በማብራሪያው።

አቶ አብዲ መሐመድ በበኩላቸው ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን በመጥቀስ፥ ሆን ተብሎ ስሜን ለማጥፋትና እኔን ለመምታት የተደረገ ሴራ ነው ብለዋል።

ድርጊቱን ፈጽመዋል መባሉ ውሸት መሆኑንና በእርሳቸው ላይም ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው እንደሆነም ተናግረዋል።

ምቹ ባልሆነ እስር ቤት መታሰራቸውን፣ የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ ታሳሪ የታሰሩበትን ክፍል በር ገንጥሎ በመግባት ሁለት ቀን ጉዳት ሊያደርስባቸው እንደሞከረና ይህም በደህንነታቸው ላይ ስጋት እንደፈጠረባቸውም ገልጸዋል።

በአንድ አጋጣሚም አንድ እስረኛ የሽንት ቤት በር ገንጥሎ እሳቸው ላይ በመጣል ጉዳት ሊያደርስ መሞከሩንም ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

የታሰሩበት እስር ቤትም የማይመችና በጤናቸው ላይ እክል እንደፈጠረባቸውም ነው አቶ አብዲ የተናገሩት።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ አቶ አብዲ መሐመድ ማንኛውም እስረኛ በሚቆይበት እስር ቤት እንደታሰሩ ጠቅሶ፥ በእርሳቸው ላይ ምንም አይነት ጫና አለመደረጉን ገልጿል።

በተጨማሪም ፖሊስ ከእርሳቸው ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ለግጭቱ መቀስቀስ ተጠያቂ መሆናቸውንና በዚህም ተጸጽተው ይቅርታ መጠየቃቸውንም አስረድቷል።

ፖሊስ በአብዲ መሐመድ የክስ መዝገብ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ የ10 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም ምርመራውን እያካሄደ ያለው ፖሊስ የምርመራውን ውጤት ለጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ.ም ይዞ እንዲቀርብ በማሳሰብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅምላ መቃብር ተገኘ‼️

በሶማሌና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢ 200 ሰዎች የተቀበሩበት የጅምላ #መቃብር መገኘቱ ተሰማ።

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አብዲ_መሐመድ_ኡመር ላይ ፖሊስ እያካሄደ ካለው ምርመራ ጋር ተያይዞ ነው የጅምላ መቃብሩ የተገኘው፡፡

በጅምላ መቃብሩ አፅማቸው የተገኘው ሰዎችን #ማንነት ለመለየት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

በትናንትናው ዕለት፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ ሙሀመድ ኡመር ላይ ለሚያደርገው ምርመራ ፖሊስ የጠየቀው #ተጨማሪ 14 ቀናት እንደተፈቀደለትና ፍርድ ቤቱ ለህዳር 13 2011 ቀጠሮ መስጠቱን ይታወቃል።

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዲ ኢሌ‼️

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምደብ 4ኛ የወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው ለአቃቤ ህግ የሶማሌ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር በእነ አቶ #አብዲ_መሐመድ ላይ የ13 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቀደ።

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድን ጨምሮ በአራት ተጠርጣሪዎች ላይ ከሃምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማና አካባቢው ብሄርን መሰረት በማድረግ በተፈጸመው የግድያ፣ የአካል ማጉደልና ንብረት ማውደም ተግባር በመጠንሰስና በመሳተፍ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲደረግባቸው መቆየቱ ይታወሳል፡፡

መርመሪ ፖሊስ በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ፣ በወይዘሮ ራሕማ መሐመድና ፈርሃን ጣሂር ላይ ላይ ሲያደርግ የነበረውን የምርመራ መዝግብ አጠናቆ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎችን አደራጅቶ ለጠቅላይ አቃቤ ህግ ማስረከቡን ለችሎቱ አስረድቷል።

የምርመራ መዝገቡን የተረከበው ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተገቢውን ክስ ለማቅረብ ተጠርጣሪዎቹ ከተጠረጠሩበት ድርጊትና ከደረሰው ጉዳት አንፃር አይቶ ክስ አስከሚመሰረትባቸው ድረስ ተጠርጣዎቹ በእስር እንዲቆና የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ እንዲፈቀድለት ለችሎቱ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡

መዝገቡ ላይ ከቀረቡ በርካታ ማስረጃዎች አንፃር በአጭር ጊዜ መዝገቡን መርምሮ ለመደበኛ ፍርድ ቤት ክሱን ለማቅረብ የጊዜ እጥረት እንደሚገጥመውም አስረድቷል፡፡

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው አቃቤ ህግ ከሁለት ወር ጀምሮ እስካሁን ድረስ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየ ሲሆን ÷ አሁን ላይ የጠየቀው 15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ተገቢ አይደለም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡
ክስ ለመመስረትም አስር ቀን በቂ መሆኑን የተጠርጣሪ ጠበቆች ገልጸዋል፡፡

የግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበት ጉዳይ ከባድና ውስብስብ ስለሆነ ሌሎች አቃቤ ህጎች እንዲሳተፉበት ለማድረግና የምርመራ መዝገቡ በጥራት ታይቶ ክስ መመስረቱ ተገቢ በመሆኑ ለአቃቢ ህግ የ13 ቀናት የክስ መመሥረቻ ጊዜ ፈቅዶ ለጥር 24 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዲ ኢሌ‼️

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ #አብዲ_መሐመድ የቀረበባቸው ክስ “የተቀነባበረ ውሸት ነው” አሉ። አቶ አብዲ ይህን ያሉት ጉዳያቸውን እየተመለከተ ላለው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ነው።

ችሎቱ ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ የነበረው አቶ አብዲን ጨምሮ በ47 ተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበባቸውን ክስ በንባብ ለማሰማት ነበር። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በይፋ ክስ የመሰረተው ባለፈው ረቡዕ ጥር 22 የነበረ ቢሆንም የተከሳሽ ጠበቆች በችሎት ባለመገኘታቸው የክስ ንባቡ ለዛሬ ተላልፏል። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ በሐምሌ 2010 ዓ. ም. በሶማሌ ክልል 59 ሰዎች እንዲገደሉ እና 412 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገዋል በሚል ነው ክሱን ያቀረበው።

በዛሬው የችሎት ውሎ ክሳቸውን ያደመጡት አቶ አብዲ ክሱን ተረድተውት እንደሆነ በመሐል ዳኛው ሲጠየቁ “ሆን ተብሎ የተቀነባበረ #ውሸት መሆኑ ገብቶኛል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። የእርሳቸውን ምላሽ ተከትሎ ችሎቱን ሞልተው የነበሩ ታዳሚዎች በሹክሹክታ ሲጠያየቁ እንደነበር በስፍራው የተገኘው የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ ታዝቧል። ፍርድ ቤቱ ከአቶ አብዲ ውጭ የሌሎችን ተከሳሾች ምላሽ ያላደመጠ ሲሆን ከክስ መቃወሚያ ጋር ደርቦ ለመስማት ለመጪው የካቲት 20 ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው የተከሳሽ ጠበቆች በክሱ ላይ ያቀረቡትን አቤቱታም አድምጧል። በክሱ ውስጥ የምስክሮች ዝርዝር አለመካተቱን ያነሱት የተከሳሽ ጠበቆች በተገቢው ሁኔታ “እንድንከላከል አያስችለንም” ሲሉ ተቃውመዋል። አቃቤ ህግ ምላሹን በጽህፈት ቤት በኩል እንዲያስገባ ያዘዘው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ለየካቲት 6 ቀጥሯል።

በዛሬው ችሎት አብዛኞቹ ተከሳሾች በአካል አለመቅረባቸውን ዘጋቢያችን ተመልክቷል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው ሳምንት ባስቻለው ችሎት ፖሊስ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዲያውል የአምስት ቀናት ጊዜ ፈቅዶ ሰጥቶ ነበር። የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ለፖሊስ የደረሰው ከትላንት በስቲያ መሆኑን አቃቤ ህግ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል። “ከቦታው ርቀት አንጻር በቂ ጊዜ ይሰጠን” ሲልም በዛሬው ችሎት አመልክቷል።

ምንጭ:- የጀርመን ድምፅ ራዲዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia