TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የክልል እና የዞን ጥያቄዎችን በተመለከተ‼️

በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የዞንና የክልል ጥያቄዎችን በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ #ለመመለስ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ተናገሩ።

በአሁኑ ወቅት በርካታ የማንነት ጥያቄዎች እየቀረቡ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን በህጋዊ መንገድ ማቅረብና መደመጥ መቻል በራሱ የዴሞክራሲ መብት አካል መሆኑን አስገንዝበዋል።

ይሁን እንጂ ዞን ወይም ክልል የሚለው ጥያቄ ከመመለሱ በፊት የጥያቄዎቹ ዋና ዓላማ፤ እንዲሁም ጥቅምና ጉዳቱን መታየት አለበት ብለዋል።

የአንድ አካባቢ የዞን ወይም የክልል ጥያቄ ሲመለስ በአካባቢው ካሉ ጎረቤት ክልሎች ጋር በሰላም፣ በኢኮኖሚና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማይኖረው መረጋገጥም ይኖርበታል ብለዋል።

ይሁን እንጂ የክልልና የዞን ጥያቄዎች በህጋዊ መንገድ መቅረብ እንዳለባቸው፤ የጥያቄው አግባብነት እስከሚታይ #መታገስ እንጂ በህገ-ወጥ መንገድ ይመለሳል ብሎ መንቀሳቀስ #አዋጭነት_የለውም ብለዋል።

መንግስት ይህንኑ ጉዳይ የሚከታተል ኮሚሽን አዋቅሮ እየሰራ መሆኑንና በቀጣይ ጥናት ላይ ተመስርቶ በህጋዊ መንገድ ለመፍታት የምናየው ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ።

“የሚወሰነው ውሳኔም የሚያዋድደን፣ አንድ የሚያደርገን እንጂ የሚያጣላን መሆን የለበትም” ሲሉም ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም ጫፍ ከሌላው ጋር ተሳስሮና ተደጋግፎ መሄድ ካልቻለ #መቀጠል አይችልም፣ ህይወታችን በራሱ #ተደጋግፈን እንድንቀጥል ያደርገናል” ሲሉም ነው መልዕክት ያስተላለፉት።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia