TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BahirDar : በባሕር ዳር በአንድ ግለሰብ ቤት ከ3 ሺህ በላይ ጥይትና ሌሎች የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ፥ በግሸ አባይ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ3 ሺህ በላይ ጥይትና ሌሎች የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ፖሊስ ጥቆማው የደረሰው ከማኅበረሰቡ መሆኑን
አመልክቷል።

በጥቆማው መሰረት ተጠርጣሪው ቤት ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ፍተሻ በማካሄድ በግለሰቡ መኖሪያ ውስጥ 2 ክላሽ ፣ ከ3 ሺህ በላይ የክላሽ እና የብሬን ጥይት፣ አንድ ኤፍዋን ቦንብ እና አንድ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ ተገልጿጻ።

የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነት በአግባቡ በማጣራት አድራሻቸውን ለፖሊስ እንዲያሳውቁም ጥሪ ቀርቧል።

Credit : AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ በኤርትራ ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለች። የአሜሪካ ግምጃ ቤት በድረገጹ እንዳስታወቀው በሁለት የኤርትራ ባለስለጣናት እና በ4 ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጥሏል። አሜሪካ ኤርትራ ላይ አዲስ ማዕቀብ የጣለችው በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ መሆኑን አሳውቃለች። እንደ አሜሪካ ግምጃ ቤት መረጃ ማዕቀቡ የተጣለባቸው ግለሰቦች አብርሃ ካሳ ነማርያም የኤርትራ ብሄራዊ ደህንነነት ቢሮ ሀላፊ እና የኤርትራ…
ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አወገዘች።

አሜሪካ በትናንትናው ዕለት በኤርትራ መንግስት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ኢትዮጵያ አውግዛለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ የሚታወቁ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነበር ብሏል።

የአሜሪካ መንግስት የሚከተሉትን እውነታዎች ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ መንግስት ጠይቋል፦

1. ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረሰውን ያልተጠበቀ ጥቃት ተከትሎ ሉዓላዊት ሀገር በሆነችው ኤርትራ ላይ ሮኬቶችን ተኩሷል።

2. የኤርትራ መንግስት በግዛቱ አንድነት እና ደህንነት ላይ ለተቋጣው ጥቃት ምላሽ የመስጠት ሉዓላዊ መብት አለው።

3. የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ጦር ግዛቱን አልፎ መገኘቱን አስመልክቶ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቅሬታ አለማቅረቡንም መግለጫው አስታውሷል።

እንዲህ ዓይነት ቅሬታ የማቅረብ መብት ያለው ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ እንጂ ሌላ አካል አይደለም።

4. የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀውን የተናጥል የሰብአዊ መብት ተኩስ አቁም ተከትሎ ወታደራዊ ሀይሉን ከኢትዮጵያ ማስወጣቱም ይታወቃል።

5. የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዳይሰፍን የኤርትራ መንግስት እንቅፋት ነው ብሎ አያምንም። በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው የሰላም ስጋት የህወሓት ጠብ አጫሪነት እና ወረራ ነው።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህወሓትን የማተራመስ ሚና አጥብቆ ለማውገዝ አለመፈለጉም የሽብር ቡድኑን አበረታቶታል ብሎ መንግስት ያምናል።

ያንብቡ : telegra.ph/ETHIOPIA-11-13 #ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አወገዘች። አሜሪካ በትናንትናው ዕለት በኤርትራ መንግስት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ኢትዮጵያ አውግዛለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ የሚታወቁ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነበር ብሏል። የአሜሪካ መንግስት የሚከተሉትን እውነታዎች ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ መንግስት ጠይቋል፦ 1. ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት…
" አሜሪካ ማዕቀብ ስትጥል ይህ አዲስ አይደለም ፤ ማዕቀቡ ከዓለም አቀፍ ህግ እና ከሉዓላዊነት አንጻር ትክክል ያልሆነ እና ህገወጥ ነው " - ኤርትራ

ኤርትራ በትናንትናው ዕለት በአሜሪካ በተጣለባት አዲስ ማዕቀብ ዙሪያ በሀገሪቱ የማስታወዊያ ሚኒስቴር በኩል መግለጫ አውጥታለች።

ኤርትራ የተጣለባት አዲስ ማዕቀብ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ እና በኤርትራ ላይ የምትከተለው የተሳሳተ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ውጤት መሆኑን ገልጻለች።

አሜሪካ ማዕቀብ ስትጥል ይህ አዲስ አይደለም ያለቸው ኤርትራ፤ ማዕቀቡ ከዓለም አቀፍ ህግ እና ከሉዓላዊነት አንጻር ትክክል ያልሆነ እና ህገወጥ ነው ብላለች።

በተጨማሪ ማዕቀቡ አሜሪካ እንዳለችው በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ከማምጣት ይልቅ አፍሪካ በተለይም ምስራቅ አፍሪካ ሁሌም ወደ አለመረጋጋት እንዲመጣ ያደርጋል ብላለች።

አሜሪካ ይሄንን ህገወጥ ማዕቀብ በኤርትራ ላይ ለመጣል ስትልም በማይታመኑት ብዙሃን መገናኛ ጣቢያዎች የተሳሳቱ ዘገባዎችን እና ተከፋይ የአይን ምስክሮችን መጠቀሟንም ኤርትራ ገልፃለች።

የአሜሪካ ማዕቀብ ዋና አላማ ኤርትራዊያንን ለማስራብ እና በአካባቢው የፖለቲካ አለመረጋጋት በመፍጠር የራሷን ጥቅም ለማግኘት ስትል የተደረገ እንደሆነ ኤርትራ በመግለጫዋ አሳውቃለች።

Credit : Al Ain News / Shabiat

@tikvahethiopia
የደ/ሱዳን ፕሬዚዳንት 2 ከፍተኛ የሀገሪቱን ባለስልጣናት ከስልጣን አስነሱ።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሀገሪቱን የገንዘብ ሚኒስትር እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ከስልጣን አስነስተዋቸዋል።

ባለስልጣናቱ ለምን ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ፕሬዜዳንቱ የሰጡት ምክንያት የለም።

ፕሬዝዳንት ኪር ፥ አትያን ዲንግ አቲያንን ከፋይናንስ ሚኒስትርነት በማንሳት በአጋክ አቹል ሉአል የተኩ ሲሆን ፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፖል ማዮም አኬክ በማህሙድ ሰለሞን አጎክ ተክተዋል።

የኪር የፕሬስ ሴክሬታሪ አቴኒ ዌክ አቴኒ ፥ የተደረገው ለውጥ የመንግስትን ተግባር አይጎዳውም ብለዋል።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 12 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,424 የላብራቶሪ ምርመራ 300 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 292 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
" ኢትዮጵያ የአገሪቱን መረጋጋትና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም ግለሰብ አትታገስም " - ቢልለኔ ስዩም

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ፅ/ቤት የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ስለዋሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ሰራተኞች ጉዳይ ለCGTN አፍሪካ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ቢልለኔ ፥ “ተመድ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ውክልና ትክክለኛ የአገሪቱን ህግ አክበረው የሚሰሩ እንዳሉ ሁሉ የተሰጣቸውን ሃላፊነትና መብት ላልተገባ ተግባር በማዋል ለአሸባሪ እገዛ የሚያደርጉ አሉ” ብለዋል፡፡

ቢልለኔ ፥ "ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአሸባሪው ህወሃት እገዛ እንደሚያደርጉ የሚጠረጠሩትን በመያዝ ምርመራ ይደረጋል " ያሉ ሲሆን እነዚህ ተጠርጣሪዎች ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቢልለኔ ፥ “ኢትዮጵያ የአገሪቱን መረጋጋት እና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም ግለሰብ አትታገስም” ያሉ ሲሆን " ሁሉም ከህግ በታች ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

Credit : #CGTN #ENA

@tikvahethiopia
#OlusegunObasanjo

ኢትዮጵያ 🇪🇹 " ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ " ለሚለው መርህ ባላት እምነት እና ቁርጠኝነት የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ለሚያደርገው ጥረት አክብሮት እንዳላት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናገሩ፡፡

ቢልለኔ ይህን ያሉቱ ከCGTN አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ተገኝተው ሰላምን ስለማምጣት የተወያዩት የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጉን አባሳንጆ በአፍሪካ ህብረት የተወከሉ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ ችግሮችን ለመፍታት ስላለው ውሳኔ ኢትዮጵያ አክብሮት እንዳላት ገልፀው፤ ኦባሳንጆ በትልቅነታቸው፣ በአገር መሪነታቸውና የተለያዩ ወገኖችን ወደ ሰላም ለማምጣት በሚያደርጉት ጥረት ትክክለኛ ውክልናና ጥረታቸውም እንደሚሳክ እናምናለን ብለዋል፡፡

Credit : #CGTN #ENA

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ አዲስ የተዘረጋው የፀጥታ አደረጃጀት ምን ይመስላል ?

የአዲስ አበባን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ ታልሞ የህልውና ዘመቻ ወቅትን ያገናዘበ አዲስ የፀጥታ አደረጃጀት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ እየተዘረጋ መሆኑን የአ/አ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለፀ።

ቢሮው ፥ አደረጃጀቱ ከመንደር ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ ደረጃ የተዋቀረ ነው ብሏል።

የቢሮው የሰላም እሴት ግንባት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አደረጃጀቱ በተመለከተ ለአዲስ ቲቪ በሰጡት ቃል ፥ " አደረጃጀቱ ከመንደር በጓድ ይጀምራል፤ በቀጠና በመቶ አለቃ ይደራጃል፣ በብሎክ በሻምበል ይደራጃል ፣ በወረዳ ደረጃ በሻለቃ ይደራጃል እንዲሁም በክ/ከተማ ደግሞ በብርጌድ ይደራጃል " ብለዋል።

የየአካባቢው ነዋሪዎችንም በአባልነት የሚያቅፍ መሆኑ ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ ጠቁመዋል።

ይህ አዲስ አደረጃጀት በሁሉም ክ/ከተማ የሚኖር ማንኛውም የሰላም እና የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ ደጀን የሚሆን ህብረተሰቡ እራሱ ሰላሙን የሚጠብቅበት እንደሆነም ተገልጿል።

በአጠቃላይ በአደረጃጀቱ ከ121 ሺ በላይ ነዋሪዎች በአባልነት የታቀፉ ሲሆን ወቅቱ የሚጠይቀውን የፀጥታ ስጋት ለመቀልበስ ያለመ መሆኑ የአ/አ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" በመማሪያ ቁሳቁስ ዕጥረት ምክንያት መደበኛ ትምህርታቸውን ለመከታተል ተቸግረናል " - የግልገል በለስ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች

በመተከል ዞን የግልገል በለስ ከተማ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በተቋሙ ከፍተኛ የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት በመኖሩ ትምህርታቸውን ለመከታተል መቸገራቸውን አሳውቀዋል።

ተማሪዎቹ በምን ሁኔታ እየተማሩ እንደሆነ ከላይ በፎቶ ተያይዟል።

ተማሪዎቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቁ ሆነው ለመማር እንቅፋት የሆኑ ፦

• የመማሪያ ክፍል ዕጥረት፣
• የመጽሐፍ ዕጥረት፣
• በቂ የመጸዳጃ ቤት አለመኖርና እና የቤተ ሙከራ ቤቶች ዕጥረት በሰፊው የሚስተዋሉ ችግሮች በመሆናቸው የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸው ተማሪዎቹ ጠይቀዋል።

የተቋሙን ከፍተኛ ችግር ለመቅረፍ የወላጅ መምህራን ህብረት፣ከፍተኛ አመራሮችና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ በመጎብኘት ለወደፊት ጊዜያዊ መፍትሄ ለማበጀት ውይይት አካሂደዋል።

የመተከል ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ጸሃይ ጉዮ ፤በተቋሙ ላይ የተጋረጠው ችግር በዘላቂነት ምላሽ እስኪያገኝ አስቸኳይ ጊዜያዊ መፍትሄ በመስጠት ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንዳለበት አሳስበዋል።

ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ተቋማትን፣ ባለሃብቶችን እና ግለሰቦችን በማስተባበርና ከፍተቶችን በመሙላት ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል።

ችግሮችን ለመቅረፍ በአጎራባች ትምህርት ቤቶች የመጽሃፍ ድጋፍ ማፈላለግ፣ጊዜያዊ የመቀመጫ ወንበሮችን ማሟላትና የፈረሱ መማሪያ ክፍሎችን ለመጠገን የህብረተሰብ ንቅናቄ በመፍጠር ለመስራት በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Gelgelbeles-11-14

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA : በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ህጻናት የወደፊት ህልማቸውን ያጋራሉ።

በጥቅምት 24 ቀን 2013 በትግራይ ግጭት ተቀስቅሶ ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች ከተስፋፋ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች ተጎድተዋል / ወድመዋል፤ ሌሎች በርካታ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ተፈናቃዮችን አስጠልለዋል።

በአጠቃላይ በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልል ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ወንድ እና ሴት ልጆች የመማር እድል እንዳመለጣቸው ይገመታል።

አስያ አህመድ (እድሜ 11 አመት - ከአፋር ክልል) ፦


በግጭት ሳቢያ ተፈናቅላ አሁን በአፋር ክልል ጭፍራ ከተማ ነው የምትገኘው።

አስያ ፥ "ሰላም ለኔ ትምህርት ቤት መሄድ፣ ከጓደኞች ጋር መሆን እና መጫወት ነው” ትላለች።

“የተኩስ ድምጽ ስሰማ በጣም ፈርቼ ነበር” የምትለው አስያ ፥ “በአካባቢው ያሉ ሰዎችም እየሸሹ ነበር…አስኩማ ወደሚባል ቦታ ሄድን። ከዚያም አንድ ቀን እዚያ አሳልፈን በማግስቱ ጭፍራ ደረስን" ስትል በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ታስታውሳለች።

አስያ እና ቤተሰቧ በጭፍራ ከተማ ትንሽ ቦታ ተከራይተው ነው የሚገኙት።

አስያ አህመድ መቼ ወደ ቤቷ እንደምትመለስ እርግጠኛ አይደለችም።

አስያ ወደፊት ህመም ያለባቸውን ሰዎች ለማከም ዶክተር ለመሆን ተስፋ አድርጋለች።

ተመስገን ኃይለ (እድሜ 11 ዓመት - ከትግራይ ክልል) ፦

ተመስገን ኃይለ የትግራይ ክልል ነዋሪ ሲሆን እድሜው 11 ዓመቱ ነው። ተመስገን እጅግ በጣም ባለብሩህ እእምሮ ያለውና ጎበዝ ልጅ ነው።

ሳይንቲስት መሆን የሚፈልገው ተመስገን "የትምህርት ቆይታዬን ሳስብ እንደ ህልም ነው" ይላል። ጦርነት ባመጣው መዘዝ ተፈናቅሎ አሁን የሚኖረው በመቐለ ሀወልቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ባለች አንድ ክፍል ነው።

መሰረት ተኳር (እድሜ 16 ዓመት - ከአማራ ክልል) ፦

በአካባቢዋ (ቆቦ) ጦርነቱ ሲጀምር ከ2 ወንድሞቿ ጋር ሆና ከእናታቸው ተነጥላ ነው ጦርነት ሽሽት ደሴ የገባችው።

“ግጭቱ ሲጀመር እኛ ቤት ላይ ጥይት ሲዘንብ ነበር። በአካባቢው አንድ ሰውም ተገድሏል። ከአያቶቻችን ጋር ነበርን በኃላም ለደህንነታችን ስንል ሸሸን" ትላለች መሰረት።

"ስለ እናቴ አስባለሁ" የምትለው መሰረት ፥ " እዚያ (ቆቦ) ሰዎች ተገድለዋል የሚሉ ብዙ ወሬዎችን እንሰማለን። ያ በጣም ያሳስበኛል” ስትል ተናግራለች።

መሰረት ትምህርቷን ስትከታተል የነበረው 7ኛ ክፍል ቢሆንም ደሴም ሆነ ሌላ ቦታ ትምህርቷን መቀጠል ትችል እንደሆነ እርግጠኛ አይደለችም። 

የ16 ዓመቷ መሰረት ፥ “ሰላም ለእኔ ከቤተሰብ፣ ከጓደኞችና ከማውቃቸው ሰዎች ጋር መሆን ነው። ሰላም ማለት ትምህርት ቤት ገብቶ ከአስተማሪዎችና ከጓደኞቼ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ማለት ነው” ብላለች።

ሙሉውን ያንብቡ 👉https://telegra.ph/UNICEF-11-05
#SUDAN

ትላንት ሱዳን ውስጥ በነበረ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስትኑን በሚቃወም ከፍተኛ የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የፀጥታ ኃይሎች 4 ሰልፈኞችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል።

የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ (CCSD) ባወጣው ሪፖርት ትላንት በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ 4 ሰዎች በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን ገልጿል።

ሟቾችን በተመለከተ ፦ አንድ በሮያል ኬር ሆስፒታል ውስጥ የነበረ ወንድ ህይወቱ አልፏል፤ የ18 ዓመት ወንድ በምስራቅ ናይል ሆስፒታል ህይወቱ አልፏል ፤ የ35 ወንድ በፊውቸር ሆስፒታል፣ እና የ19 ወንድ ወንድ በአልአርባኢን ሆስፒታል ህይወታቸው አልፏል።

በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ካውንስል ፀጥታ ሃይሎች የተገደሉት የንፁሀን ዜጎች ቁጥር ወደ 5 ከፍ ማለቱንም የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ አሳውቋል።

ሱዳን ውስጥ በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ እየደረሰ ያለው አሰቃቂ ጥቃት በቀጠለበት ወቅት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳቶች ደርሰዋል።

በተጨማሪም የወታደራዊ ጁንታው ሃይሎች የቆሰሉ ንፁሀንን ወደ ሆስፒታሎች ለማጓጓዝ እንቅፋት እየፈጠሩ እንደነበረም ኮሚቴው ሪፖርት አድርጓል።

የወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ካውንስል ፀጥታ ኃይሎች አል አርባን ሆስፒታልን ወረው በስራ ላይ ያሉ ዶክተሮች ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ፣ ሲቪሎችን፣ ቤተሰቦቻቸውን ማቁሰላቸው እና አንዳንዶቹንም እንዳሰሩ ተመላክቷል።

CCSD ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በጁንታው እና ታጣቂዎቹ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ በሚተገብሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየፈፀሙት ላለው ወንጀል ትኩረት እንዲሰጡ ተማጽኗል።

@tikvahethiopia