TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሜሪካ የተሳተፈችባቸው ጦርነቶች ...

#Repost

በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካ በበርካታ ሀገራት ውስጥ በተደረጉ ጦርነቶች እጇን አስገብታለች።

በጥቂቱ...

#አፍጋኒስታን

አል-ቃይዳ መስከረም 11 ቀን 2001 በአሜሪካን ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ አሜሪካ ታሊባንን ከስልጣን ለማስወገድ አሜሪካ የአፍጋኒስታንን ወረራ መርታለች። 20 ዓመታት የዘለቀ እጅግ ዋጋ ያስከፈለ ጦርነት ነበር። በመጨረሻ ግን ታሊባን ወደቦታው ተመለሰ። አሜሪካም ጓዟን ጠቅልላ ወጣች።

#ኢራቅ

በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ዘመን አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ 2003 ኢራቅን በመውረር ሳዳም ሁሴን ከሥልጣን አስነስታለች። በኢራቅ ጦርነት በርካቶች አልቀዋል፣ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ኢራቅ ዛሬም አስተማማኝ ሙሉ ሰላም የላትም። ለዳግም ግንባታም ደፋ ቀና እያለች ነው።

#ሊቢያ

የአሜሪካና የአውሮፓ አጋሮች እኤአ በ 2011 በሊቢያ የአየር ዘመቻ ከፍተው ነበር ፤ ጥቃቱ ሙአመር ጋዳፊ በአረብ አብዮት ለመቃወም በተነሳሱ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ግፍ ለመከላከል በሚል ነው ፤ የእነ አሜሪካ መዘቻ ጋዳፊን አወረደ ፣ ሊቢያ ግን ወደ ትርምስና ቀውስ ገባች፤ ዛሬም እዛው ናት።

#ሶሪያ

አሜሪካ ከሌሎች አጋሮቿ ጋር ሆና በሶሪያ ጦርነት ውስጥም እጇ ያለበት ሲሆን በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ የበሽር አል አሳድ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት በምትወስደው እርምጃ የሶሪያ ከተሞች ክፉኛ አውድማለች።

#የድሮን_ጥቃቶች

አሜሪካ ሽብርን ለመዋጋት በሚል በፓኪስታን፣ የመን፣ ሱማሊያ፣ ሊቢያ የድሮን ጥቃቶችን ፈፅማለች (አሜሪካ ከፍተኛ የሰራዊት ቁጥር አላሰፈረችም)።

እነሊቢያ፣የመን፣ ሱማሊያ ጦርነት ምስቅልቅላቸውን አውጥቶት ዛሬም ማገገም ያልቻሉ ለደህንነት አስጊ ሀገራት ሆነው ቀርተዋል።

@tikvahethiopia
" ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን ገልፀውልኛል " - ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ

በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የመንግስትን እና የህወሃትን አመራሮችን ማነጋገራቸውን ካስታወቁ በኋላ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ኦባሳንጆ ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ ፍልሚያውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፡፡

ከመንግስትም ሆነ ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀው ህወሃት በኩል የሰላም ፍላጎቶች መኖራቸውን የገለጹት ከፍተኛ ተወካዩ ‘የሰላም መንገዱ ምን ይሁን’ የሚለው ግን ልዩነታቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የአፍሪካ መሪዎችና ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ሕብረቱ የጀመረውን የማሸማገል ጥረት እንዲደፉ እና ግጭቱን ሊያባብሱ ከሚችሉ ነገሮች እንዲቆጠብም ኦባሳንጆ ጥሪ አቅርበዋል።

ኦባሳንጆ፥ "ሆን ተብሎም ይሁን ባለማወቅ ግጭቱን የሚባብሱና ወደከፋ ደረጃ ከሚያደርሱ ንግግሮች መቆጠብ ያስፈልጋል" ብለዋል ።

ኦባሳንጆ፤ ውጊያው ከቆመ የንግግር ዕድል እንደሚኖር የገለጹ ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ ውጊያ እየተደረገ ግን ለመነጋጋር የሚመች እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ኦባሳንጆ ፥ የኦሮሚያ እና አማራ ክልል አመራሮችን ማግኘታቸውን በመግለጫቸው ላይ የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የአፋር ክልል አመራሮችን እንደሚያገኙ አሳውቀዋል።

ኦባሳንጂ ይህ የማሸማገል ስራ እንዲሳካ ቁርጠኛ እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን ፦
- #የኬንያ
- #ኡጋንዳ
- #ጅቡቲ
- #ደቡብ_ሱዳን
- #ሶማሊያ እና ሱዳን መሪዎችን ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አስማሚ ሁኔታ ይፈጠራል ብዬ አስባለሁ ያሉት ኦባሳንጆ ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን እንደገለጹላቸው አሳውቀዋል።

Credit : #Al_AIN
Pic : AU

@tikvahethiopia
ኡሁሩ ኬንያታ አዲስ አበባ ገቡ።

የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ " ውድ ወንድሜ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ወደ ሁለተኛው ቤትዎ እንኳን ደህና መጡ " ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
አንቶኒ ብሊንከን ዛሬ ናይሮቢ ይገባሉ።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከዛሬ ጀምሮ ሦስት የአፍሪካ አገራትን ይጎበኛሉ።

ሚኒስትሩ ኬንያ፣ ናይጄሪያና ሴኔጋልን ነው በይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው የሚጎበኙት።

ብሊንከን ጉብኝታቸው የ6 ቀናት ሲሆን ጉብኝታቸው ከናይሮቢ የሚጀምሩ ሲሆን ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመገናኘት በኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ እና በሱዳን ያሉ ጉዳዮችን ጨምሮ በሌሎች ርዕሶች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኬንያው ፕሬዜዳንት ትላንት ኢትዮጵያ ነበሩ።

የኬንያ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ጉብኝቱን በማስመልከት ኡሁሩ ኬንያታ ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር መወያየታቸውን ገልጿል።

ኬንያታ እሁድ ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ ለሰዓታት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው ማምሻውን ወደ ናይሮቢ መመለሳቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#ይከተቡ

ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት እድሜያቸው 12 ዓመትና ከዚያን በላይ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ-19 ክትባት በዘመቻ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አሰታወቀ።

ከዛሬ ሰኞ ህዳር 6 እስከ ህዳር 15 ጀምሮ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ እድሜው ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ በአቅራቢያቸው በሚገኝ ጤና ጣቢያ በመሄድ ክትባቱን መውሰድ እንደሚችሉ የቢሮ ሃላፊው ዶክተር ዮሃነስ ጫላ አስታውቀዋል።

ከጤና ጣቢያዎች በተጨማሪም የክትባቱን ተደራሽነት ለማስፋት በትላልቅ የገበያ ቦታዎች ፣ ሞሎች ፣ በባንኮች ፤ በትራንሰፖርት መናህሪያዎች ፤ በኢንዱስትሪ ፓርክ እና በሌሎች በተመረጡ ቦታዎች ይሰጣል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ እስከአሁን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች የኮቪድ 19 ክትባት የተሰጠ ሲሆን ለ10 ቀናት በሚካሄደው የክትበት ዘመቻ ከ1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ::

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የክትባት ቡድኖች መደራጀታቸውን ዶክተር ዮሃንስ ጫላ ገልጸዋል፡:

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
#Legetafo : በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ከተጠርጣሪ ወንጀለኞች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ዘግቧል።

የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ክላሽንኮቭ ፣ ሽጉጥ፣ ቦንብ፣ የተለያዩ ጥይቶችና የሠራዊት ዩኒፎርም ከተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዉ ፖሊስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#DireDawa

በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ እና ገጠር የሚኖር ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኝ የጦር መሳሪያ በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ እና ገጠር በሚገኙ በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር ቀርቦ ማስመዝገብ እንዳለበት የድሬዳዋ ፖሊስ ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ዜጎች እጃቸው ላይ የሚገኝ ጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ የተቀመጠው ቀነ ገደብ ዛሬ ህዳር 6 ቀን 2014 ዓ/ም ይጠናቀቃል።

@tikvahethiopi