TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NationalExam

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከየካቲት 29 ቀን 2013 ጀምሮ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተሳካ መልኩ እንዲጠናቀቅ ከ4 መቶ በላይ የፖሊስ ሀይል አባላት ስምሪት እንደተሰጣቸዉ ለአሃዱ ሬድዮ ኤፍ ኤም 94.3 አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ይፈጠሩ የነበሩ ችግሮች እንዳይከሰቱ የዲጅታል ደህንነት እና የአካላዊ ደህንነት መፈተሻዎች መዘጋጀታቸዉ ተገልጿል፡፡

ፈተና በሚካሄድባቸዉ ቀናት አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች ተሟልተዋል ያሉ ሲሆን ለፈታኞች እና ለተቆጣጣሪዎች ማብራሪያ የመስጠት እንዲሁም የመፈተኛ ክፍሎችን ማዘጋጀት በስፋት እየተሰራባቸዉ መሆኑን ሀገር አቅፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለሬድዮ ጣቢያው (አሃዱ FM 94.3) አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NationalExam

በአ/አ ከተማ የ12ኛ ክፍል ፈተና ያለ ምንም እንከን እንዲካሄድ ሁሉም ባለድርሻ አካል ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ።

ዛሬ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መቀጠል በሚችልበት ጉዳዮች ዙሪያ ከሁሉም ትምህርት ቤቶች ከተውጣጡ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐር ቫይዘሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኜ ገብሩ ርዕሰ መምህራን በየትምህርት ቤቱ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮችን በበላይነት መከታተል እና ከጸጥታ አካላት ጋር በጋራ መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተገናኘ ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮችን የሚከታተል የአብይ እና ቴክኒክ ኮሚቴ እንደሚዋቀር አሳውቀዋል።

ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀ ሁሉን ኃላፊነቱን ይወጣ ተብሏል።

በሌላ በኩል ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫን ተከትሎ በየትምህርት ቤቱ የጸጥታ ችግር እንዳይከሰት ከወዲሁ መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተገኘው ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትምህርት_ሚኒስቴር የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል። ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ…
#NationalExam

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ ይሰጣል።

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ፈተናው ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የፈተና ደንብ ጥሰቶች #በህግ ያስጠይቃሉም ተብሏል።

የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጀ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ከቀናት በፊት መገለፁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE " የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲሰጥ ታቅዷል " - ትምህርት ሚኒስቴር የ2ዐ14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በሁለት_ዙር እንዲሰጥ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለ42 ዩኒቨርሲቲዎች…
#NationalExam

መስከረም 30 ቀን 2015 መሰጠት የሚጀምረው የ2014 ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና " ተሰርቆ ወጥቷል " በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆነን  የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የአገልግሎተ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ ከፈተና ስርቆት ጋር በተያያዘ እተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የዘንድሮ " ነው ተብሎ የሚሰራጨው ፈተና በ2013/14 (2021) ዓ.ም የተሰጠ እንደሆነ አስረድተዋል። እየተሰራጩ ያሉት ፈተናዎች ዓመቱ ኤዲት ተደርጎ መሆኑንም አመልክተዋል።

" ተፈታኝ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰራጩ መሰል መረጃዎችን ከማመናቸው በፊት የአሰራጩን ታማኝነት እንዲያጣሩና ትክክለኛነቱን እንዲመረምሩ " መልዕክታቸውን አስተላፈዋል።

የአገር አቀፍ ፈተናን የተመለከቱ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት " ፖለቲካን ከታዳጊዎች ህይዎት ቢለዩ መልካም ነው " ሲሉ ለ " ኢትዮጵያ ቼክ " መረጃ አጣሪ ድረገፅ በሰጡት ቃል አሳስበዋል።

የ2014 ዓ/ም የሀገር አቀፍ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሁለት ዙር የሚሰጥ ይሆናል።

ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንደሰማነው ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ይገኛል ፤ ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው ተብሏል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
* ብሔራዊ ፈተና የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ካላንደራቸው ላይ ማስተካከያ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህ እየተደረገ ያለው ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ወቅት በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መገኘት ስለሌለበት ነው። በሌላ በኩል ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #ለሪፖርተር_ጋዜጣ…
#NationalExam

ለ12ኛ ክፍል የብሄራዊ ፈተና አስፈፃሚዎች ስልጠና ተሰጣቸው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ማጠናቀቂያ ፈተና አስፈጻሚዎች ሥልጠና እንደተሰጣቸው ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ የፈተና አስፈፃሚዎች ትልቅ ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን በመገንዝብ በትጋትና በታማኝነት እንዲወጡ በማሳሰብ ዝርዝር የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው ፤ የፈተና አስፈፃሚዎች በቂ ትኩረት በመስጠት ያለ ምንም አድልዎ ሙያዊ በሆነ አግባብ እንዲሁም በቁርጠኝነት የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

ዝርዝር ስልጠና በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አመራርና በዘርፉ ባለሙያዎች ተሰጥቷል።

የ2014 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከመጪው መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በሁለት ዙር ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ፎቶ : የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለፈተና ሄደው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለወለዱ ተፈታኞች በቀጣይ እንደመደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ ዕድል ይሰጣቸዋል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በእርግዝና ላይ ላሉ እና ወልደው ህጻንን ጡት እየመገቡ ላሉ ለተመዘገቡ ሴት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የእነርሱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የመፈተኛ ስርዓት በቀጣይ መዘጋጀቱን አሳውቋል። በመሆኑም ተፈታኞቹ ከመስከረም…
#NationalExam

የ2014 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከነገ መስከረም 30 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

ነገ ፈተናቸውን የሚፈተኑት በመጀመሪያ ዙር ወደ መፈተኛ ማዕከላት / ዩኒቨርሲቲ የገቡ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።

ተማሪዎቹ ስለፈተናው አጠቃላይ (ኦረንቴሽን) ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በፈተና ወቅት መከተል ስላለባቸው የስነምግባር መርሆች፣ የሰዓት አከባበርን በተመለከተ ፣ የተብራራላቸው ሲሆን የመፈተኛ ጣቢያ እና ክፍላቸውን ለይተውም እንዲያውቁ መደረጉን ሰምተናል።

ከተፈታኝ ተማሪዎች በተጨማፊ ፈታኞች፣ ለፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ ለሱፐርቫይዘሮች፣ ማየት ለተሳናቸው ተፈታኝ አንባቢዎችና ለመልስ ወረቀት ቆጣሪዎች ገለፃ (ኦረንቴሽን) ተሰጥቷቸዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከነገ ጥዋት ጀምሮ እስከ ጥቅምት 2 ድረስ ይሰጣል፤ ከጥቅምት 3 - ጥቅምት 4 ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ።

የ12ኛ መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናው ጥብቅ በሆነ ዲሲፕሊን እንደሚመራ ተገልጾልናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተፈታኞች በሙሉ መልካም ፈታናን ይመለኛል!

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ እና ነገ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማእከላት / ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ። ይህ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጥብቅ በሆነ ህግ መሰጠት ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ ፈተናቸውን ጨርሰው የወጡት " የማህበራዊ ሳይንስ " ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የተመለከቱትን እና በቀጣዩ " የተፈጥሮ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ሊስተካከለ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች በዝርዝር…
#NationalExam

የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል።

ተማሪዎች ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ሲሆን ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ (ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል።

ከጥቅምት 08 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

ከዚሁ ከሁለተኛ ዙር ፈተና ጋር በተያያዘ የባለፉት ክፍተቶች መታረም ያለባቸው ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር  ሴት ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ በቀን ሆነ በማታ ምንም አይነት ትንኮሳ እንዳይደርስ እና ፈተናውን ተረጋግተው እንዳይወስዱ የሚያደርጉ ጫናዎች እንዳይፈጠሩ እንዲሁም ምቾታቸውን ሆነ ደህንነታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል እንቅስቃሴ እንዳይኖር ጥብቅ ቁጥጥር ማደረግ ይኖርበታል።

የፀጥታ ኃይሎች የግቢ መውጫ እና መግቢያ ላይ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ዙርያ ገባው ላይ ቁጥጥራቸውን ማጠንከር እንዳለባቸው የከዚህ ቀደም ተፈታኝ ተማሪዎች ጠቁመዋል። (በአጥር የተከለከሉ ነገሮች እንዳይገቡ)

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ የ2014  የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ ሁሉንም የፈተና ህጎችን በማክበር በመረጋጋት፣ በከፍተኛ የራስ መተማመን እንዲሁም በብሩህ ተስፋ ፈተናችሁን እንድትወስዱ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ደግሞ እነዚህ ታዳጊዎች አሁን ለተተገበረው የፈተና ስርዓት/ለዩኒቨርሲቲም  አዲስ በመሆናቸው ማበረታታ እና መደገፍ እንጂ ባልተረጋገጠ መረጃ እንዲረበሹ፣ ተስፋ እንዲቆርጡ፣ በራሳቸውን እንዳይተማመኑ ማድረግ የለባችሁምና ስለምታጋሩት መልዕክት ጥንቃቄ አድርጉ እንላለን።

ተማፅኖ፦ ተፈታኝ ተማሪዎችን ወደ ፈተና ማዕከል በማጓጓዝ ላይ አሽከርካሪዎች በእርጋታ እና በጥንቃቄ ማሸከርከር እንዳትዘነጉ እንማፀናለን።

መልካም ፈተና!
Tikvah Family!

@tikvahethiopia
#NationalExam

2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ 21/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

በሁለተኛው ዙር ለፈተና የሚቀመጡ የሁሉም ክልል ተማሪዎች መለየታቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ፦

• የመጀመሪያውን ዙር ፈተና በወሊድ ወይም በእርግዝና ምክንያት መፈተን ያልቻሉ፣

• በሕግ ጥላ ስር ወይም በማረሚያ ቤት ሆነው ለመፈተን ያልቻሉ፣

• የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወይም የፌዴራል ፖሊስ ወይም የክልል ልዩ ኃይል አባል ሆነው በወቅቱ በግዳጅ ላይ በመሆናቸው ያልተፈተኑ፣

• በህመም ወይም ተቀባይነት ባገኘ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ፈተና ያልወሰዱ፣

• ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በደረሰው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ያልተፈተኑ፣

• በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አንድ ፈተና እንዲፈተኑ የተወሰነላቸው፣

• ተቀባይነት ባገኙ ችግሮች ምክንያት ፈተና እንዲወስዱ የተወሰነላቸው።

@tikvahuniversity
#NationalExam

" ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን አይፈተንም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን ነው የተገለፀው።

የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ሲሆን ተማሪዎች የምዝገባ ሂደቱን ለማካሄድ በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ይካሄዳል።

የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ሲሆን ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደማይፈተን አገልግሎቱ አሳውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ለምዝገባ ምን ያስፈልጋል / ተማሪዎች ምን ማሟላት አለባቸው ?

- መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ9 - 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም  በመማር ላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

- የማታ እና የርቀት ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ሶስት ሴሚስተር እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል የሁለት ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

- ድጋሜ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም የተፈተኑበትን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ መመዝገብ አለባቸው።

- ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናው መቼ እና የት ይሰጣል ?

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም  ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

Credit : #MoE

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#NationalExam

የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።

ተቋማቱ አጠቃላይ ያሉበትን ደረጃ እየገመገሙ ናቸው።

ፈተናው የተሳለጠ እንዲሆን ተቋማት በዚህ ሳምንት ተመራቂ ተማሪዎቻቸውን በማስመረቅ በቶሎ ይሸኟቸዋል።

ከሐምሌ 16 ጀምሮ ተቋማት ለ12ኛ ክፍል ፈተና #ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቡ አይዘነጋም።

ከትምህርት ምዘናና ፋተናዎች አገልግሎት ባገኘነው መረጃ መሰረት ፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሐምሌ 16 -17 / 2015 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ ፤ ሐምሌ 18 የፈተና ኦረንቴሽን ይሰጣቸዋል፤  ከሐምሌ ከ19 - 21/2015 ፈተናው ለ 3ት ቀናት ይሰጣቸዋል ፤ ሐምሌ 22-23/2015 ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ሐምሌ 22 -23/2015 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ፤ ሐምሌ 24/2015 የፈተና ኦረንቴሽን ይሰጣል ፤ ከሐምሌ 25 -28/2015 ፈተናው ለአራት ቀናት ይወስዳሉ ሐምሌ 29-30/2015 ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NationalExam

ከነገ ሐምሌ 19 ጀምሮ በሚጀምረው ሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ከፈተና ደንብ ውጭ ማንኛውም እንቅስቃሴ ካደረጉ / ጥፋት ከፈፀሙ ውጤታቸው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ #ሊሰረዝባቸው ይችላል።

ፈተና በከፊል የሚያሰርዙ ጥፋቶችን አጥፍተው የተገኙ ተፈታኞች ጥፋቱ የተመዘገበባቸው ፈተና ውጤት ብቻ ነው የሚሰረዝባቸው።

ተፈታኞች በፈተናው ወቅት የፈፀሙት ጥፋት ሙሉ በሙሉ ፈተናቸውን እንዲያሰርዝ የሚያደርግ ከሆነ  ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ ይሰረዝባቸዋል።

ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ።

@tikvahethiopia