TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፕ/ር መሰፍን አርአያ ወልደተንሳይ ማናቸው ? የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ሹመት ዛሬ ፀድቋል። የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት ደግሞ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ናቸው። • በሕክምና የዶክተሬት ዲግሪ ( MD) ፣ ከፓቭሎቭ ዩኒቨርሲቲ ሩሲያ፤ • በሳይኮቴራፒ ፍልስፍና የፒኤች ዲ ዲግሪ (PhD)፣ ከኦማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰዊድን፤ • ስፔሻላይዝድ ድፕሎማ፤ በሳይኮሎጂካል ሜድስን እና ሳይካትሪ፣…
#አገራዊ_ምክክር

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕ/ር መስፍን አርአያ ከሹመቱ በኃላይ የተናገሩት ፦

" አስራ አንዳችንም ገና በሚገባ መተዋወቅ አለብን። እዚህ ውስጥ በተለይ አስሩ በጣም ብዙ ልምድ ያላቸው ናቸው። ደስ ብሎኛል ሴቶች አሉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ፤ ወጣቶች አሉ።

በእርግጥ በተወካይነቱ ላይ ኢትዮጵያ ከ86 ብሄረሰቦች በላይ ነው ያሏት ስለዚህ 86ቱንም ወደዚህ ማምጣት ሳይሆን 86ቱና ከዚያ በላይ ያሉትን ወደ መግባባት መድረኩ ማምጣት ስለሆነ ትልቁ ስራ እንግዲህ በጋራ ስንገናኝ ስራ ስንከፋፈል የምናየው እና የምናውቀው ይሆናል።

ይሄ ኃላፊነት ከሌሎች ኃላፊነት ለየት ሚያደርገው የመግባባት አጀንዳዎች በጣም ብዙ ናቸው። ስለዚህ እነዚህ አጀንዳዎች ነቅሶ ወደ ጠረጴዛ በማምጣት አጀንዳዎቹ ላይ በትክክል በጋራ፣ በኢትዮጵያዊነት ላይ ፣ መብትን በማስከበር ላይ ፣ ባህልን ፣ ቋንቋን እና ሌሎችንም የሚመለከታቸውን ነገሮች በማስከበር ላይ ትልቅ ብሄር ትንሽ ብሄር ሳንል ሁላችንም በጋራ መስራቱ ላይ ብዙ ነገር ስለሚጠበቅብን ይሄ ትልቅ ኃላፊነት ነው ብዬ አስባለሁ፤ ደግሞም ነው ይሄ ነው ከበድ ያደርገዋል ብዬ የማስበው።

በጋራ ከሰራን ወደ መፍትሄ የማንደርስበት ምክንያት የለም። ሁሉም ነገር ሰልችቶናል ሰላም ማጣቱና መጎዳቱ እና መብት በማስከበር ሂደቱ ላይ የደረሰብን ብዙ ጉዳዮች ስላሉ እነኛን በጋራ እንፈታለን ብዬ አስባለሁ።

ሀገርን በመገንባቱ ሂደት፣ ህዝብን ወደመግባባቱ በማምጣት ሂደት ሚዲያዎች ትልቅ ቦታ አላቸው ፣ፖለቲካ ፓርቲዎች ፣የሃይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ አባገዳዎች እና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወጣቶች በተለይ በዚህ ስራ ላይ ከጎናችን ሆነው ይረዱናል ያግዙናል ወደ መፍትሄ ያመጡናል ብዬ አስባለሁ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አገራዊ_ምክክር

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ ሂሩት ገብረስላሴ ከሹመቱ በኃላ የተናገሩት ፦

"... ሌላ ዓለም ላይ ሰርቻለሁ። ሌላ ዓለም ላይ ያለኝን እውቀት ፣ ያለኝን ልምድ ተጠቅሜ ነው ኢትዮጵያ ላይ ሲሆን ሀገሬ ስለሆነ እንደ ሚሽንም ነው ከፍተኛ ስሜትም አለው። ከእኔም ከሁላችም ከፍተኛ ቁርጠኝነት ይኖራል ብዬ አስባለሁ።

ትልቅ ኃላፊነት ነው የተሰጠን ፤ ትልቅ ክብርም ነው ግን የተሰጠን ለዛ ብቁ ሆነን ለመገኘት ማድረግ ያለብንን ጥረት እናደርጋለን።

... የዚህች ሀገር ችግር የህዝቦች ችግር አይደለም የኤሊቱ ፣ ተምሪያለሁ ባይ ፣ አንድ ቦታ ደርሻለሁ ባይ የኤሊቱ ችግር ስለሆነ ለኤሊቱ ነው ጥሪ ማቅረብ ያለብን ኤሊቱ ላይ ነው በጣም መሰራት ያለበት ህዝቡ መኖር ነው የሚፈልገው፤ በሰላም መኖር ነው የሚፈልገውና የህዝቡ ችግር አይደለም። ስለዚህ ማሸነፍ የሚኖርብን ኤሊቱን ነው።

እዚህች ሀገር ላይ ኤሊት መሆን ማለት እኮ Privileged የሆነ status አለህ ማለት ነው። የተሻለ ትምህርት አግኝተሃል ፣ የተሻለ ኑሮ ኖረሃል ፣ የተሻለ Experience አለህ ተብሎ የሚገመት የማህበረሰብ ክፍል አስቸጋሪ ሆኖ ሊቀጥል አይገባውም ፤ አይችልም።

እኔ ይመስለኛል እግዚአብሔር ከረዳን አንድ ቦታ እንደርሳለን። "

@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

እናት ፓርቲ ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ግልጽ ደብዳቤ ጻፈ።

ፓርቲው ለኮሚሽኑ በጻፈው ደብዳቤ ፤ " ኢትዮጵያ ሕልውናዋን በመፈታተን ደረጃ ላይ ከደረሰው ቀውስ ብቸኛው መውጫ መንገድ ሁሉን አቀፍ #አገራዊ_ምክክር ማድረግ ፤ እንደ አገር በዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሆነ በጽኑ እናምናለን " ብሏል።

" የምክክር ኮሚሽኑ በክልል ደረጃ የአጀንዳ ልየታ ውይይቶችን ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንና ለዚሁ በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተከታታይ ቀናት በሚደረጉ ስብሰባዎች የአጀንዳ ልየታ የሚያደርግ ጉባዔ መጥራቱ ይፋ ተድርጓል ፤ ጥሪው ለእኛም ደርሷል " ብሏል።

" የሚደረገው ምክክር ስልጣንን የጨበጠ አካል #በቀጥታም ሆነ #በስውር የሚመራው ውይይት መሆን እንደሌለበት እናምናለን " ሲል አስገንዝቧል።

ፓርቲው ፤ " በእኛ እሳቤ ይህ ምክክር በሥራ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥት በመሠረታዊ መልኩ እስከ ማሻሻል አስፈላጊ ከሆነ እስከ መለወጥ ድረስ የሚያዘልቅ እንደሆነ ብናምንም በሥራ ላይ ያለው የአሸናፊዎች ሕገ መንግሥት ዓይነት ተግባር እንዳይፈጸም እና እንደ አገር ዳግም ስህተት እንዳንሠራ ከፍተኛ ሥጋት አለን " ሲል አሳውቋል።

" አገር ልትመክርበት ይገባል ብለን የምናስባቸው የምክክር አጀንዳዎች ፦
➡️ ወቅት የማይለውጣቸውና ወጥነት ያላቸው፣
➡️ መንግሥት ብንሆን ልንተገብራቸው ይገባል ብለን ያስቀመጥናቸው ነጥቦች ስለሆኑ ከአጀንዳ ልየታው ጋር ምንም ችግር የሌለንና ይህንኑ ያቀረብን መሆናችንን ኮሚሽኑ እንዲያውቀው የአገራችን ሕዝብም እንዲረዳልን እንወዳለን " ብሏል።

እናት ፓርቲ ፥ " አጀንዳዎቻችንን የማቅረቡ ሂደት እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚደረገው የምክክር መድረክ ፦

1ኛ. አገር በከፍተኛ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባለችበት ሁኔታ ምክክርም ጦርነትም በአንዴ ማድረግ የማይቻል መሆኑ፣ ከአገራት ተሞክሮ እንዲህ ባለ ሁኔታ የሚደረግ ምክክር ውጤታማ እንደማይሆን ታውቆ በተቃራኒ ወገን የተሰለፉ ወንድማማቾችን እያጨራረሰ የሚገኘው የእርስ በርስ ጦርነት በድርድር ፖለቲካዊ መፍትሄ ሳይበጅለት ፤

2ኛ. በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በየእሥር ቤቱ ታጉረው ባሉበትና ፍትሕ ተነፍጓቸው የሰቆቃ ሕይወት በሚገፉበት፤

3. የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ለምክክሩ ጭምር ጉልህ አስተዋጽዖ ማድረግ የሚችሉ ወገኖቻችን ያለ ፍርድ በየእሥር ቤቱ በሚማቅቁበት፤

4ኛ. አገር በአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ባለችበት፤

5ኛ. በምክክሩ ከመሳተፍ ራሳቸውን ከመጀመሪያ ጀምሮ ከሂደቱ ያገለሉትን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ምክክር ማምጣት ባልተቻለበትና በመሳሰሉ ምክንያቶች ምክክሩ አገራችን በእጅጉ የምትሻውን አገራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ያስገኝላታል ብለን አናምንም። " ሲል አሳውቋል።

" እነዚህ ሁኔታዎች አጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ምክክር እስከሚደረግበት ባለው ጊዜ በቀዳሚነት መፍትሄ አግኝተው ሊፈቱ ካልቻሉና ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ካልተቻለ በምክክሩ ለመሳተፍ እንቸገረለን " ሲል ገልጿል።

(ፓርቲው ለኮሚሽኑ የላከው ሙሉ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia