TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኦነግ አቀባበል⬇️

ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የሚደረገው የአቀባበል ስነ ስርዓት ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ #ህብረተሰቡ የበኩሉን እንዲወጣ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር የፊታችን ቅዳሜ መስከረምን 5 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ደማቅ የአቀባበል ስነ ስርዓት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

ለኦነግ የሚደረገው አቀባበል ስነ ስርዓት ለኦሮሞ ህዝብ ክብር የሚዘጋጅ ነው ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር የሚደረገው አቀባበል ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ የበኩሉን ሀላፊነት እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

ዶክተር ነገሪ፥ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ምህዳር መስፋፋቱን ተከትሎ መቀመጫቸውን በውጭ ሀገራት አድርገው የነበሩ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሀገር እየገቡ መሆኑን አንስተዋል።

ከውጭ ሀገራት እየተመለሱ ላሉና ለተመሱ የፖለቲካ ድርጅቶችም በክልል እና በፌደራል ደረጃ አቀባበል ተደርጎላቸዋልም፤ እየተደረገላቸው ይገኛልም ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ መስከረም 5 2011 ዓ.ም ምህረት የሚደረገው አቀባበል በተለይ ወጣቶች የህዝቡን አንድነት በሚጠብቅ መልኩ እንዲሆን ማድረግ አለበት ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ይህ የአቀባበል ስነ ስርዓት #የማያስደስታቸው አካላት ሊኖሩ ይችላሉ ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ በተለይ ወጣቱ ከእነዚህ አካላት የሚመጡ ትንኮሳዎችን በብስለት ማለፍ እንዳለበትም አሳስበዋል።

እንዲሁም የአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ለየት ያለ ነገር በሚመለከቱበት ወቅት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡም ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

ዶክተር ነገሪ አክለውም፥ ማንኛውም አካል #ይገልፀኛል፤ ይወክለኛል የሚለውን ምልክትና ባንዲራ የመያዝ መብት አለው፤ የተደረገው ትግልም ሀሳብን በነፃነት መግለጽ እንዲቻል ነው ብለዋል።

ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ከባንዲራ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማ በትናንትናው እና በዛሬው እለት የሚስተዋሉ ችግሮች በምንም መስፈርት #ተቀባይነት የሌለ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

አሁን ያለንበት ወቅት ምክንያት ፈልገን የምንጣላበት ሳይሆን ምክንያት ፈልገን አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ ማንኛውም አካል ከባንዲራ ጋር በተያያዘ #ሊጋጭ አይገባም ብለዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፌደራል ፖሊስ-አልታገስም አለ⬆️

ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል እየተፈጠረ ያለውን ግጭትና ህገወጥ ተግባር ከዚህ በኋላ #እንደማይትገስ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ኢብሳ ነገዎ ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይም ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል፥ በትናንትናው እለት እና ዛሬ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩን አስታውቀዋል።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን #የኦነግ ቡድን ለመቀበል እየተደረገ ባለ ቅድመ ዝግጅት ወቅት ወጣቶች የድርጅቱን አርማ ለመስቀል ዝግጅት እያደረጉ ነበር፤ ይህንን የከለከላቸው አካል የለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ሆኖም ግን አስፋልትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን እንዳያቀልሙ ተከልክው፤ ይህንንም ተወያይተን እሺ ብለው ተቀብለው ትተው ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን ማንም ያልፈቀደላቸው አካላት የእነሱን ባንዲራ አውርደው የሌላ ለመስቀል ሲሉ ግጭት ተፈጥሯል ሲሉም ገልፀዋል።

ግጭቱ ለማንም ጠቃሚ አይደለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ችግሩን #በውይይት መፍታት ሲቻል ወደ አላስፈላጊ ግጭት መግባት ተገቢ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።

ፖሊስ የህግ የበላይነትን የማስከበር ሀላፊነት ስላለበት ከዚህ በኋ እንዲህ አይነት #ግጭቶችን በትእግስት እንደማያልፍም ኮሚሽነር ዘይኑ አሳስበዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋ፥ የዴሞክራሲ ስርዓትን እንገንባ ብለን ስንሰና ስርዓቱን ለመገንባት የሚያስፈልግ እነዚህን ባህሪያትን ተቀብለን ካልተነሳን ግን ስርዓቱን መገንባት እንችልም ብለዋል።

የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ልዩነቶችን መቀበል የግድ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ልዩነቶቹ ደግሞ ሀሳቦችን፣ አርማዎችን እና ባንዲራዎችን ሊያጠቃልል ይችላል ብለዋል።

ትናንትና እና ዛሬ በአዲስ አበባ የተስተዋሉ ችግሮች ደግሞ ከዚህ ጋር የሚፃረሩ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ማንኛውም አካል ስሜቴን ይገልፅልኛል ያለውን አርማ የመያዝ እና የማውለብለብ #መብት አለው ሲሉም ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ #ኢብሳ_ነገዎ በበኩላቸው፥ ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የተስተዋለው ችግር #ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አንስተዋል።

ወጣቱም ከዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች ሊቆጠብ እንደሚገባም አቶ ኢብሳ ጥሪ አስተላልፈዋል።

አሁን ላይ እየታየ ያለው ግጭት እና ያልተገባ #ፉክክር ድርጅታቸውን የማይወክል መሆኑንም ነው አቶ ኢንብሳ ተናግረዋል።

©Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባ ምንጭ! ነገ በአርባ ምንጭ ከተማ በአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈፀመው ድርጊት የሚያወግዝ ሰልፍ እንደሚደረገ ሰምቻለሁ። ጨዋው የአርባ ምንጭ ህዝብ ተቃውሞውን እና ሀዘኑን በሰላማዊ መልኩ እንደሚገልፅ ሙሉ እምነት አለኝ። ለዚህ ደግሞ ሰላም ወዳዶቹ የአርባ ምንጭ ወጣቶች ምስክር ናቸው።
.
.
ተጨማሪ...

የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳደር ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ለጊዜው የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንደሚያደርግ የተጠቆመ ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈፀመውን ድርጊት በእጅጉ ኮንኗል። ጋሞ ጎፋ ዞን ብሔር ብሔረሰቦች ተቻችለው #በፍቅር የሚኖርበት ዞን በመሆኑ መላው የዞኑ ህዝብ በትግስት እና #አኩሪ ዕሴቱን በመጠበቅ እንዲሁም በህግ #ተቀባይነት የሌለው ተግባር #በላመፈጸም እንዲተባበር ከዞኑ ጥሪ ቀርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወቅታዊ መግለጫ‼️

‹‹ወደ አማራ ክልል የሚመጡ የየትኛውም አካባቢ ተማሪዎች የአማራ #ልጆች ናቸው፡፡››

‹‹የግለሰቦችን ችግር #በግለሰብ ደረጃ መጨረስ ሲገባ ለጋ ወጣቶችን #መጠቀሚያ ማድረግ ተቀባይነት የለውም፡፡›› ርዕሰ መስተዳድር አቶ
ገዱ አንዳርጋቸው
.
.
.
ሃገራችን በለውጥ እንቅስቃሴ በምትገኝበት በዚህ ወቅት አልፎ አልፎ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተፈጠረው ችግር ተማሪዎች የህይዎት እና የአካል ጎዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በዚህም የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን የገለፁት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የግለሰቦች ግጭት ወደ ቡድን ወይም አካባቢ ወስዶ በተደራጀ አግባብ ዕርስ በዕርስ ተማሪዎችን #ማጋጨት በምንም መንገድ #ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል፡፡

ችግሩ የተለየ የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው እና አሁን እየተፈጠረ ያለው አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ያላስደሰታቸው አካላት በታቀደ መንገድ የሚያራምዱት የግጭት ሴራ ነው ያሉት አቶ ገዱ ተማሪዎችም #ስሜታዊ በመሆን የሌሎች አጀንዳ ፈፃሚዎች ሳይሆኑ ችግር ፈጣሪዎችን
አጋልጠው እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

ከመላ ሃገሪቱ የሚመጡ ተማሪዎችና ልጆቻቸውን አምነው የሚልኩ ወላጆች ዓላማቸው ግልፅ ነው፤ እሱም ተምሮ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ፡፡ ይህንን የተማሪዎችና የወላጆች ዓላማ ስኬታማ ለማድረግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የእውቀት እንጅ የግጭት ማዕከል መሆን ስለሌለባቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለዘላቂ ሰላም በጋራ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

ወደ አማራ ክልል የሚመጡ የየትኛውም አካባቢ ተማሪዎች የአማራ ልጆች ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የአካባቢው ማህበረሰብ ተማሪዎቹን ሲቀበል ያሳየውን ጨዋነት እና እንግዳ ተቀባይነት እስከመጨረሻው ማሳየት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

ግጭት በተፈጠረባቸው አካባቢዎች ካሉ የዩኒቨርሲቲ #አመራር አካላት፣ የክልል መስተዳድሮችና ከፊዴራል መንግስት ጋር በተማሪዎቹ #ደህንነት ዙሪያ እየተነጋገርን ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UNSC : ትላንት ለሊት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር።

በዚህ ስብሰባድ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እየተባባሰ መሄዱ በጽኑ እንዳሳሰበውና በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ።

ከስብሰባው በኋላ በ15ቱም አባላት #ተቀባይነት_አግኝቶ በወጣ መግለጫ ሁሉም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች ጦርነቱን በማቆም "ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ የተኩስ አቁም ለማድረግ" ውይይት እንዲጀምሩ ጥሪ አቀርቧል።

መግለጫው ለተፈጠረው ቀውስ መፍትሔ ለማግኘት እንዲቻል እና ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት ለማካሄድ አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠር ጠይቋል።

የምክር ቤቱ አባላት ችግሩን ለመፍታት #የአፍሪካ_ሕብረትን በመሰሉ አካባቢያዊ ድርጅቶች በኩል የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፉና የሕብረቱ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ተኩስ እንዲቆምና ጦርነቱ ሰለማዊ መቋጫ እንዲያገኝ የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚደግፍ ገልጿል።

በተጨማሪ ሁሉም ወገኖች "ከአደገኛ ጥላቻ ከሚያስፋፉ፣ ግጭትንና መከፋፈልን ከሚያነሳሱ ንግግሮች" እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia