TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ጥንቃቄ አድርጉ‼️ #ከኢትዮጵያ ወደ #ቻይና የምትሄዱ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሰዎች ይህን እቃ እዛ ላለ ሰው አድርስልኝ/አድርሺልኝ ሲሏችሁ በደንብ የሚላከውን ነገር ፈትሹ። ቻይና ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ለመረዳት እንደቻልነው አንዳንዶች በሚላከው እቃ ውስጥ አደንዛዥ እፆችን በመጨመር እንደሚልኩ ጠቁመዋል። በተለይ ምግብ ነክ ነገሮች ውስጥ የአደንዛዥ እፆችን በመክተት ይልካሉ።…
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር‼️

በህገ ወጥ ደላሎች #ነፃ የትምህርት አግኝታችኋል ተብለው ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ #ነብያት_ጌታቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሁለቱ ሀገራት በሚገኙ ህገ ወጥ ደላሎች ነጻ የትምህርት እድል አግኝታችኋል ተብለው ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ወጣቶቹ አግኝታችሁታል የተባለው ነፃ የትምህርት እድል #ሀሰተኛ በመሆኑ ቻይና ሲደርሱ ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ከዚህ ባለፈም በቻይና አደገኛ እፅ #በማዘዋወር እና #ጫትን ከኢትዮጵያ ወደ ቻይና በማስገባት በህገ ወጥ ስራ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ቃል አቀባዩ አብራርተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በቻይና በዚህ አይነት ወንጀል መሳተፍ ከእድሜ ልክ እስራት እስከ #ሞት ቅጣት በሚደረስ ፍርድ የሚያስቀጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ 47 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት በፍርድ ቤት #ጥፋተኛ ተብለው የእርምት ጊዜያቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሲሆን የቀሪዎቹ ደግሞ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዜጎች ከተመሳሳይ ችግር ለመውጣት የትምህርት እድል አግኝታችኋል ሲባሉ ከተቋማቱ በቂ መረጃ መሰብሰብ እንደሚገባቸውም ቃል አቀባዩ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል ወደ ቻይና ለተለያዩ ጉዳዮች የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን የታሸጉ ነገሮችን ወደ ቻይና አድርሱልን ተብለው ሲጠየቁ ስለእቃዎቹ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ይገባቸዋልም ነው ያሉት።

እነዚህ ወንጀሎች የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት እንዳያበላሹም መንግስታቱ እርስ በርስ የተሳሰሩ ደላሎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሌሎች ሀገራት የሄዱ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ቃለ አቀባዩ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም በተያዘው ሳምንት 1 ሺህ 40 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እና 1 ሺህ 15 ኢትዮጵያውያን ከፑንትላንድ መመለሳቸውን ጠቅሰው፥ በቀጣይ ሳምንት ደግሞ 500 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እንዲሁም ከፑንትላንድ 517 ዜጎች እንደሚመለሱ አውስተዋል።

እነዚህን ዜጎች ከሀገራት ለማስመለስ ከአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia