#EMMPA
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ከሰሞኑ የተወሰኑ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች፦
- የተዛቡ፣
- ትክክለኛ የጋዜጠኝነት መርህን ያልተከተሉ፣
- የአገር ሉዓላዊነትና የህዝቦችን አንድነት አደጋ ውስጥ የሚጥሉ ብሎም የፖለቲካዊ ውግንና ያላቸውን ዘገባዎች ማሰራጨታቸውን አጥብቆ ኮነነ።
ማህበሩ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ የሰሩትን ዘገባ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።
በዚህ መግለጫው ሰሞኑን አዲስ አበባን እና ዙሪያዋን በተመለከተ የተሰራጩ ዘገባዎችን ትክክለኛነትና ሚዛናዊነት ለማጣራት ጥረት ማድረጉን ገልጿል።
ለዘገባ ከተንቀሳቀሱና በየአካባቢው ከሚኖሩ አባሎቹ ብሎም ከነዋሪዎች ባገኘነው መረጃ መሰረት እስካሁን ድረስ አዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙት አካባቢዎች ሁሉ በተለመደው እንቅስቃሴያቸው ላይ ይገኛሉ ብሏል።
ማህበሩ ከሰሞኑ ዓለምአቀፍ ሚዲያዎች የተዛቡ እና ፖለቲካዊ ውግንና ያላቸውን ዘገባዎች ማሰራጨታቸውን አጥብቆ የኮነነ ሲሆን በእንደዚህ ያሉ ሙያዊ መርሆን ባልተከተሉ ዘገባዎች እየተሳተፉ ያሉ ጋዜጠኞች ጋዜጠኝነታቸውን በሙያዊ አስተምህሮው መሰረት እንዲፈፅሙ ጠይቋል።
በተጨማሪ መቀመጫቸውን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለም ያደረጉና ስለኢትዮጵያ የሚዘግቡ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ባለሙያዎች ከእንደዚህ አይነት አዘጋገብ እንዲወጡ አጥብቆ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ መንግስትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም የየትኛውም መገናኛ ብዙኃን ዘጋቢዎች ተገቢውን መረጃ እንዲያገኙና በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረው እውነተኛ መረጃ ለህዝብ ማቅረብ እንዲችሉ አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስቧል።
የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃንም ፈጣን፣ ወቅታዊ፣ ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ መክሯል።
*ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል። ም/ቤቱ እያካሄደ ባለው ሰብሰባ የም/ቤቱን 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤ መርምሮ አፅድቋል። በተጨማሪ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የስራ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት አፅድቋል። በዚህም መሰረት ፦ 1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤…
#EMMPA
ከቀናት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሾሙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት በተመለከተ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ሹመቱ በእራሱ ምክር ቤቱ መጋቢት 2013 ዓ.ም በወጣው " የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ " (አዋጅ ቁጥር 1238/2013) ውስጥ የተካተቱ ድንጋጌዎችን የጣሰ ነው ብሎታል።
ማኅበሩ ሹመቱ ግልፅ የሆነና የማያሻማ የሕግ ጥሰት ያለበት መሆኑ የገለፀ ሲሆን ሕግን ሳይሸራረፍ መተግበር ያለመቻልን ችግር አጉልቶ ከማሳየቱ ባሻገር የሀገሪቱን የሚዲያ እድገት በእጅጉ የሚጎዳ ነው ብሎታል።
ሕዝብም በሕግ አውጭው ተቋም ላይ እምነት እንዳይኖረው የሚያደርግ እንደሆነ አስገንዝቧል።
ከዚህ በተጨማሪም የሙያ ማኅበሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቃቸውን አዋጆችንና ድንጋጌዎችን ተፈፃሚነታቸውን በትኩረት መከታተል ስለመቻሉ ጥያቄ የሚያጭር ነው ብሏል።
ማኅበሩ ግልፅ የሕግ ጥሰት የተስተዋለበት የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ አባላት ሹመት እና የሥራ ምደባ በአመዛኙ መስተካከል አለበት ብሏል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)