TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethio_Sudan

የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ወቅታዊ ችግር ለመፍታት በተመረጡ የሀገር ሽማግሌዎች ውይይት ተደረገ።

ከሁለቱም ሀገራት የተመረጡ የሀገር ሽማግሌዎች በመተማ ዮሃንስ ከተማ በሀገራቱ መሀል ባለው ችግር ዙርያ ምክክር መደረጉን የመተማ ዮሃንስ ከተማ ኮሚኒኬሽን ማምሻውን አስታውቋል።

ኮሚኒኬሽኑ እንዳስታወቀው ከነበሩት የውይይት አጀንዳዎች መሀል፣
1.ችግሮቻችን ምን ምን ናቸው የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፣
2. የኢትዮ-ሱዳን ግንኙነትን ለማጠናከር ከኛ ምን ይጠበቃል፣
3. በቀጠናው የሚታዩ ሰው የማገትና ሌብነትን እንዴት እንከላከል፣
4. ድንበሩ ከዚህ በፊት እንደነበረው ግንኙነት እንዲፈጠር ከኛ ምን ይጠበቃል፣
5.ህዝባችን ሰላሙ የተጠበቀ እንዲሆን የሀገር ሽማግሌዎች እስከ ባህር ዳር ድረስ እንዲቋቋምና
ግንኙነቶችን ለማጠናከር ህብረተሰባችን ላይ የግንዛቤ ትምህርት በመስጠት ስራ መስራት እንደሚገባ የሚሉ ሃሳቦች ተገልፀዋል።

ለዚህም የጋራ የሆነ ትብብር 20 ሽማግሌዎችን በመምረጥ ውይይትን ማድረግ እንደሚችሉ ወስነዋል። ሌላው የሁለቱንም መንግስታት ጠንካራ ግንኙነትን በመፍጠር የህብረተሰብን ችግሮች ለመቅረፍ የጋራ ጥንካሬ ያስፈልጋል ሲሉ የሀገር ሽማግሌዎች ገልፀዋል።

Via የመተማ ዮሀንስ ኮሚኒኬሽን / Elias Meseret

@tikvahethiopia
#Ethio_Sudan

ለስድስት ወራት የተዘጋው በመተማ - ጋላባት በኩል ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው መንገድ ነገ ክፍት ይሆናል ተብሏል።

ዛሬ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች እና የሁለቱ ሀገራት አጎራባቸው አስተዳደሮች ማለትም የምዕራብ ጎንደርና በሱዳን በኩል ደግሞ የጋላባት አካባቢ አስተዳደር ተወካዮች በመተማ ተወያይተዋል፡፡

ይህን በተመለከተ የመተማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብቴ አዲሱ ለአል ዐይን አማርኛ ክፍል በሰጡት ቃል ሐምሌ17 ቀን 2013 ዓ.ም የመተማ-ጋላባት መንገድ በሱዳን በኩል ተዘግቶ ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።

የሱዳን መንግስት መንገዱን የዘጋው አንድ ወታደራዊ አመራር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ተገድሎብኛል ብሎ በማሰቡ መሆኑን አቶ ሀብቴ ተናግረዋል፡፡

ከንቲባው እንዳሉት መንገዱ አለምአቀፍ መስመር ስለሆነ እንዲከፈት በአካባቢው አስተዳደር እና በሀገር ሽማግሌዎች ለማስከፈት ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

በስብሰባው ላይ መንገዱ ተክፍቶ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ እንዲቀጥል መግባባት ላይ መደረሱን የገለጹት አቶ ሀብቴ ከዚህ በተጨማሪም ለሁለቱ ሀገራት አለመግባባት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችም ተነስተዋል ብለዋል፡፡

በሱዳን ግዛት ውስጥ ሚንቀሳቀሱ የህወሓት ኃይሎች መኖራቸውንና ያሉበትን ቦታ ጭምር በመጥቀስ እና ትክክል እንዳልሆነ ለሱዳን ወታደራዊ አመራር እንደተነገራቸው ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
ፎቶ ፦ የምዕራብ ጎንደር ዞን

@tikvahethiopia
#Ethio_Sudan

በሱዳን ኃይሎች የተያዘው የአልፋሽቃ መሬት ሰላማዊ መፍትሄ ካላገኘ በኢትዮጵያ በኩል በኃይል የመፍታት እድል ይኖረው እንደሆነ ከጀርመን ሬድዮ የተጠየቁት የመከላከያ ሰራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ጄነራል ባጫ ደበሌ፥ "በእኛ በኩል መንግስታችን ከሱዳን ጋር ተዋጉ የሚል ትዕዛዝ አልሰጠንም" ብለዋል።

አክለውም፥ "እኛ የያዝነው ውጊያ አለ፤ ከእነዚህ ሰዎች (ከሱዳኖች) ጋር ድሮውንም እንዳልነው ነው በውይይት የምንፈታው ነገር ነው። እነሱ ከነበሩበት የቀጠሉት የለም። ስለዚህ ትኩረት የተነፈገው አይደለም። በሚገባ እየተከታተልን ነው ያለነው" ሲሉ ገልፀዋል።

ጄነራል ባጫ፥ " ሁሉንም ድስት ጥደህ አንዱንም ሳታማስል ሊያርብህ አይገባም። ሆኖም በየትኛውም አካባቢ በኢትዮጵያ ድንበር ላይ የሚመጣ ችግር ካለ ግን ይሄን መመለስ የሚችል አቅሙ አለን " ብለዋል።

በሌላ በኩል ከአል ዓይን ኒውስ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ጀማል አል ሼክአምባሳደር ጀማል አል ሼክ፤ በሱዳን ቁጥጥር ስር ስለሚገኘውና የይገባኛል ጥያቄና ክርክር እየተነሳበት ስላለው ስፍራ የሱዳንን አቋም አንፀባርቀዋል።

አምባሳደሩ፥ "አሁን ክርክር እያስነሳ ያለው መሬት ሱዳን የኔ ነው ብላ ታምናለች" ያሉ ሲሆን " ሱዳን ጉዳዩ ከፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ ውጭ በሌሎች አማራጮች ይፈታል ብላ አታምንም " ብለዋል።

አምባሳደሩ፥ " እነዛ ቦታዎች የሱዳን ናቸው፤ ለዚህ ማስረጃም እንደፈረንጆቹ 1902 በሁለቱም ሀገራት የተደረሰው ታሪካዊ ስምምነት እንዳለ ይታወቃል፤ ስለዚህም የድንበር ውዝግቡ የስምምነቱን ዋና ዋና ጉዳዮች መሰረት በማድረግ ሊፈታ ይችላል የሚል እምነት አለኝ" ሲሉ ተናግረዋል።

ሱዳን ጉዳዩን በዲፕሎማሲ እና ፖለቲካዊ ውይይት ለመፍታት ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።

@tikvahethiopia