TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ #ደቡብ_ሲዳን

የኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ዛሬ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው #ጁባ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደቡብ ሱዳን የገቡት ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" በክልሉ ሰላማዊ ትግል መታገል ባለመቻሉ  ነው ወደ ትጥቅ ትግል የተቀላቀልነው ፤ ... ካሁን በኃላ ታጥቆ የሚነቀሳቀስ ኃይል የለንም " - ጋነግ

የጋምቤላ ነጻነት ግንባር " ካሁን በኃላ በስሜ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ሀይል የለም " አለ። ቡድኑ ትጥቅ ማውረዱንም ገልጿል።

በጋምቤላ ክልል እና ደቡብ ሱዳን አዋሳኝ አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረው የጋምቤላ ነጻነት ግንባር የተባለ ታጣቂ ቡድን በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከመንግስት ጋር ከስምምነት ላይ ከደረሰ ወዲህ 205 አባላቱ ወደ ተሀድሶ ስልጠና መግባታቸውን አሳውቋል።

የክልሉ መንግስት በበኩሉ በሰላማዊ መንገድ ልዩነቶችን በመፍታት ታጣቂዎቹ ወደ ተሀድሶ ስልጠና መግባታቸውን ገልጿል።

የጋምቤላ ነጻነት ግንባር እና የክልሉ መንግስት ከየካቲት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ በደቡብ ሱዳን #ጁባ እና #በአዲስ_አበባ ውይይቶችን ካደረጉ በኃላ ከስምምት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡ 

የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ጋትሉዋክ ቡም ፥ በክልሉ ሰላማዊ ትግል መታገል ባለመቻሉ   ወደ ትጥቅ ትግል መቀላቀላቸውን ጠቁመዋል፡፡

ሆኖም ከመንግስት ጋር በተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች በሰላማዊ መንገድ ለመቀንቀሳቀስ ወደ ጋምቤላ መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሚያዚያ 12/2015 ዓ.ም 195 የሚደርሱት ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ ትጥቅ መፍታታቸውን አመልክተዋል ሲል የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የጋምቤላ ክልል ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia