TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መከላከያ ሰራዊት🔝ዘመናዊና ብቁ የሆነ ሰራዊት መገንባት የሚያስችለው #የሪፎርም ትግበራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢ/ ሹም ጄኔራል #ሰዓረ_መኮንን አስታወቁ፡፡

ምንጭ~etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን🔝ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ከውጭ የገቡ ተፎካካሪ ፓረቲዎችን ጨምሮ ከየፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡ ውይይቱም ቀጣዪን ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው #የሪፎርም_ስራዎችና የጋራ ኃላፊነት ላይ ይመክራል፡፡

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
184 የፖሊስ አባላት ተሰናበቱ‼️

አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከተቋሙ ተልኮ በተፃረረ መልኩ በተለያዩ የወንጀል ድርጊት የተሳተፉ እና የስነ-ምግባር ችግር ያለባቸውን 184 የፖሊስ አባላትን ከሰራዊቱ #ማሰናበቱን ገለፀ።

ኮሚሽኑ ለfbc በላከው መግለጫ፥ በአገር አቀፍ ብሎም በከተማዋ ተግባራዊ የሆነውን ለውጥ ተከትሎ ከዚህ ቀደም በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን በማስተካከል ለከተማችንን የሚመጥን ፖሊሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ልዩ ልዩ የለውጥና የመልሶ ማደራጀት ወይም #የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ከህብረተሰቡ የተሰጡ ጥቆማዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የደረሱትን መረጃዎች መነሻ በማድረግ መላው የፖሊስ አባላትን ያሳተፈ ግምገማ ከማእከል እስከ ፖሊስ ጣቢያ ባለው መዋቅር የአጥርቶ ማጥራት ስራ በመስራት ከኮሚሽኑ ተልዕኮ ተፃራሪ በመሆን በልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ላይ የተሳተፉ እንዲሁም ከፖሊሳዊ ስነ-ምግባር ውጭ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 184 የፖሊስ አባላት ከሰራዊቱ ማሰናበቱን ነው ያስታወቀው።

በልዩ ልዩ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ገብተው የተገኙ የፖሊስ አባለት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል።

የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠልና ተቋሙ ህዝብና መንግስት የጣሉበትን ከፍተኛ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ቀጣይነት ያለው የማጥራት ስራዎችን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በመግለፅ፥ በቅርብ ጊዜ መላውን አባልና አመራር ያሳተፈ ስልጠናዊ ግምገማ ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

በመጨረሻም ለኮሚሽኑ ስራ መሳካት ህብረተሰቡና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እያደረጉለት ላለው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋናውን አቅርቦ ነዋሪው በአገልገሎት አሰጣጥ ይሁን የስነ-ምግባር ችግር ያለባቸውን የፖሊስ አባለት ሲያጋጥሙት በየአካባቢው በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ፖሊስ መምሪያዎች እና ፖሊስ ኮሚሽን ድረስ በአካል በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 ወይም 01-11-11-01-11 ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ገልጿል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መከላከያ የሰራዊቱን ተልዕኮ የመፈፀም አቅም እና ብቃት ለማሳደግ የሚያስችለው #የሪፎርም ሥራ ይገኛል። ዛሬ የተመረቁ ከፍተኛ መኮንኖችም የተጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም ከግብ ለማድረስ ሚናቸው የጎላ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም።" (የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም - ጄነራል አደም መሀመድ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia