TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#INVEA : በህገ-ወጥ መንገድ ፓስፖርት ሲያዘጋጁ የተገኙ 10 የኢሚግሬሽን ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በፌዴራል ፖሊስ የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክተር ኮማንደር ታደሰ አያሌው ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ ተጠርጣሪዎቹ ህጋዊውን የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደት ወደ ጎን በመተው፣ የፓስፖርት ባለቤቶችን ሙሉ መረጃ በመቀየር እና በአንድ ማእከል መጠናቀቅ የነበረበትን አገልግሎት ወደ ተለያዩ ቅርንጫፎች በማዘዋወር ወንጀሉን በኔትወርክ መፈፀማቸውን ገልፀዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ከደላሎች ጋር በፈጠሩት የጥቅም ትስስር በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦች እና የውጭ ሀገር ዜጎችም ጭምር ፓስፖርት እንዲያገኙ ማመቻቸታቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም መንግስት ሊያገኝ ይችል የነበረውን ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳሳጡ ነው ኮማንደር ታደሰ አያሌው ለቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN : " ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ እኔ ቤት ነው ያለው " - ሌ/ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን የሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን በመግለጫቸው በሱዳን ጦር በቁጥጥር ስር የዋሉት ጠቅላይ ሚኒስትር በአብደላ ሀምዶክ ያሉበትን አስታውቀዋል። አልቡርሃን ፥ “ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እኔ ቤት ነው…
#SUDAN : መፈንቅለ መንግስት የተካሄደባቸ እና ወዳልታወቀ ቦታ ተውስደዋል የተባሉት አብደላ ሃምዶክ ከነበሩበት ስፍራ ትላንት ምሽት ወደቤታቸው ገብተዋል።

ትላንት የሱዳን ጦር አዛዥ አብዱን ፈታህ አልቡርሃን " ጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክ ለደህንነታቸው ሲባል እኔ ቤት ነው ያሉት" ብለው ነበር።

ሀምዶክ ትናንት ምሽት ከታሰሩበት ስፍራ ወደመኖሪያ ቤታቸው እንደተመለሱ የተዘገበ ሲሆን ወደቤታቸው ከተመለሱ በኃላ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር በስልክ አውርተዋል፡፡

ብሊንከን በትዊተር ባሰራጩህ ፅሁፍ በሀምዶክ መፈታት መደሰታቸውን ገልጸው አሁንም በእስር ላይ ያሉ ሌሎች የሲቪል አስተዳደር አመራሮች እንዲፈቱ አሳስበዋል፡፡

#አልዓይን

@tikvahethiopi
TIKVAH-ETHIOPIA
ፒተር ማውረር ኢትዮጵያ ገብተዋል። የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ፕሬዝዳንት ፒተር ማውረር በኢትዮጵያ ያለውን ሰብአዊነት ሁኔታ ለመገምገም ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ታውቋል። ማውረር በኢትዮጵያ 3 ቀናት የሚቆዩ ሲሆን ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር በአሁናዊ ሁኔታ ዙሪያ ይወያያሉ። በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ተወካዮች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ…
#Update

አቶ ደመቀ መኮንን ከፒተር ማውረር ጋር ተወያዩ።

ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ፕሬዚዳንት ፒተር ሞረርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ባለው የረጅም ጊዜ አገልግሎት በመንግስት በኩል እየተደረገለት ስላላው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ፕሬዚደንቱ ICRC በገለልተኝነት መርህ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን አስታውሰው ፤ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በትግራይ ክልል እያደረገ ካለው እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ፦
- የአየር በረራ ፈቃድ፣
- የጥሬ ገንዘብ መጠን መጨመር
- የነዳጅ ፍላጎትን በተመለከተ መንግሰት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ICRC በአገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ሳይገባ ፤ በሰብዓዊነት መርህ ተልዕኮውን ለመወጣት እየሰጠ ስላለው አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድርጅቱ በትግራይ ክልል እያደረገ ካለው የሰብዓዊ ድጋፍ ጋር ተያይዞ በትክክለኛ ፍላጎት ላይ በመመስረት የነዳጅ ሆነ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት እንዲሟላ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ደመቀ ፤ " ህወሓት በከፈተው ወረራ ምክንያት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚፈልጉ ዜጎችን ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ነውም" ሲሉ አስረድተዋል።

በተጨማሪ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ያሉትን የጦር እስረኞች በተመለከተ " ታሳሪዎቹ ዜጎቻችን ከመሆናቸውም ባሻገር የዓለም አቀፍ ህግን ታሳቢ በማድረግ ተገቢው አያያዝ ይደረግላቸዋል " ብለዋል።

መረጃውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#Afar : የአፋር ክልል የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ቢሮ ለ ቢቢሲ በሰጠው ቃል በክልሉ በተለይም ከጭፍራ እና ከመጋሌ ወረዳዎች ባለፉት ጥቂት ቀናት ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ ይገኛሉ።

ከጭፍራ ወረዳ ከ35 ሺህ በላይ ሰው ተፈናቅሏል ፤ ከመጋሌ ወረዳ ደግሞ ወደ 10 ሺህ ሕዝብ ተፈናቅሏል፤ ከዚህ ወረዳ የሁለት ቀበሌ ሕዝብ ነው የተፈናቀለው።

ከዚህ በፊት ከነበረው 150 ሺህ ተፈናቃይ ጋር ሲደመር አሁን ያለው የተፈናቃዮች ቁጥር ከ200 ሺህ በላይ ደርሷል።

ጭፍራ ወረዳ ከአማራ ክልል ጋር የሚዋሰን ሲሆን፤ መጋሌ ወረዳ ከትግራይ ክልል ጋር ይዋሰናል።

ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ቢሮው ገልጿል፤ ግጭት በቀጠለባቸው አካባቢዎች ሰዎች አሁንም እየተፈናቀሉ ይገኛሉ።

ቢሮው ፥ በርካታ ሰዎች በየጫካው፣ በየጥሻው ተበትነው እንደሚገኙ አሁን የጠፉ እና ከቤተሰብ የተለያዩ ሰዎችን አግኝቶ አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክቷል።

የአፋር ክልል ማስ ሚዲያ ትላንት ባወጣው ዘገባ ህወሓት በከፈተው ጦርነት እና ወረራ ሳቢያ በተለይም ከጭፍራ ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎች ለአደጋ በመጋለጣቸው መንግስት ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ተፈናቃዮች ውሃ፣ መጠለያ፣ ምግብና የህክምና ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

የክልሉ አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ተፈናቃዮች የሚያነሱት ችግር መኖሩን በመቀበል ችግሩን ለመፍታት ርብርብ እንደሚደረግ ፤ በቀጣይ ቀናቶችም ችግሩ ይቃለላል ብሎ እንደሚያስብ አሳውቋል።

የተፈናቃዮች ቁጥር መብዛት ለፈጣን ድጋፍ ፈተና ሆኗል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : የፍትህ ሚኒስቴር የህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ብሎ ለፈረጀው ትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ድጋፍ ያደርጋሉ፤ ግንኙነትም አላቸው ተብለው የታሸጉ ፋብሪካዎች ፣ የተለያዩ ድርጅቶች አስተዳዳሪ ተሹሞላቸው በቅርቡ ስራ ይጀምራሉ ሲል አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ለሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

ከጥቂት ወራት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የንግድ ድርጅቶች እና ሆቴሎች የንግድ ህጉን በመጣስ እና ለTPLF የሽብር ተግባር ድጋፍ ያደርጋሉ በሚል ጥርጣሬ ታሽገው ነበር።

ከተዘጉት የንግድ ድርጅቶች መካከል በርካቶቹ ተመልሰው እንደተከፈቱ ነገር ግን ቁጥራቸው በግልፅ የማይታወቅ ትልልቅ ሆቴሎች ጭምር አሁንም ድረስ ዝግ እንደሆኑ ናቸው።

ከሆቴሎቹ መካከል ፦
- ካሌብ ሆቴል
- ኔክሰስ ሆቴል
- አክሱም ሆቴል
- ንግስተ ሳባ ሆቴል
- ሀርመኒ ሆቴል እና ሌሎችም ይገኙበታል።

ቃላቸውን ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ፀጋ ፥ " በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን የንግስ ድርጅቶች እና ሆቴሎች አስተዳዳሪ ተሹሞላቸው ስራቸውን እንደገና እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየተሰራ ነው" ብለዋል። ነገር ግን በድርጅቶቹ ላይ የሚደረገር ምርመራ እንደሚቀጥል ለጋዜጣው አሳውቀዋል።

ፍትህ ሚኒስቴር በወንጀል የተጠረጠሩትን ተቋማትና ግለሰቦች ወደፍርድ እንደሚያቀርብ የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው የከተማ አሰተዳደሩ ድርጅቶቹን ለመክፈት ወይም ላለመክፈት አስተዳደራዊና የወንጀል ህጉን መሰረት በማድረግ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

አቶ ፍቃዱ ፥ በሆቴሎችም ሆነ በንግድ ድርጅቶች ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞች ስራ አጥ መሆን የለባቸውም ያሉ ሲሆን ድርጅቶቹ በተቻለ መጠን ወደ ስራ እንዲመለሱ ለማድረግ እተሰራ ነው ብለዋል።

telegra.ph/ER-10-27

@tikvahethiopia
#HU : ከሰሜን ኢትዮጵያ የመጡ ተመራቂ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መቸገራቸውን ገልጸዋል።

በጦርነቱ ምክንያት ለማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር እንደተጋለጡ የሚናገሩት ተማሪዎቹ፤ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል፡፡

ከአፋር ክልል የመጣው ተማሪ አሊ ሰይድ፤ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት አካባቢ በተቀሰቀሰ ጦርነት ምክንያት የባንክም ሆነ የኔትወርክ አገልግሎት በመቋረጡ የገንዘብ ችግር እንዳጋጠመው ተናግሯል።

ከወልዲያ አካባቢ የመጣው ተማሪ ያሬድ በሪሁን በጦርነቱ ምክንያት ቤተሰቦቹ ከቀያቸው ተፈናቅለው በወሎ ተፈናቃዮች ካምፕ እንደሚገኙ ተናግሯል።

ሌላኛው ተማሪ አንድሚሊዮን አምባው ከትግራይ ክልል የመጣ ሲሆን ቤተሰቦቹን ካገኘ ከስምንት ወር በላይ እንደሆነና ለጭንቀት በመጋለጡ በትምህርቱ ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረበት ተናግሯል።

በተለይም ከምርቃት በኋላ ያለው ጊዜ እንዳሰሰባቸው ተማሪዎቹ ይገልጻሉ፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዓለም ዐቀፍ እና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አለምሽት ተሾመ ተማሪዎቹ ያቀረቡትን የእርዳታ ጥያቄ ለመፍታት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመነጋገር የመመረቂያ ልብሶችን እና የገንዝብ ድጋፎችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በቀጣይ ጊዜ ስለሚኖሩ ጉዳዮች ዩኒቨርሲቲው ከትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ እየተጠባበቀ እንደሆነም ዳሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

መረጃው የሐዩ ኤፍኤም ነው።

@tikvahuniversity
ትላንት ለሊት በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ ቤት አስታወቀ።

አደጋው የደረሰው በወረዳው በገርቢ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ቀልቀልቲ " በሚባል አካባቢ ከለሊቱ 9 ሰአት ነው።

በአደጋው ሹፌሩን ጨምሮ በውስጥ የነበሩ 3 ሰዎች ህይወት ወዲያው አልፏል።

ታርጋ ቁጥሩ A 21594 የሆነ የጭነት አይሱዙ መኪና ከሸዋሮቢት ወደ ኮንቦልቻ ቲማቲም ጭኖ ሲሄድ ነው አደጋው የደረሰበት።

ፖሊስ በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳትና የትራፊክ አደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN : መፈንቅለ መንግስት የተካሄደባቸ እና ወዳልታወቀ ቦታ ተውስደዋል የተባሉት አብደላ ሃምዶክ ከነበሩበት ስፍራ ትላንት ምሽት ወደቤታቸው ገብተዋል። ትላንት የሱዳን ጦር አዛዥ አብዱን ፈታህ አልቡርሃን " ጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክ ለደህንነታቸው ሲባል እኔ ቤት ነው ያሉት" ብለው ነበር። ሀምዶክ ትናንት ምሽት ከታሰሩበት ስፍራ ወደመኖሪያ ቤታቸው እንደተመለሱ የተዘገበ ሲሆን ወደቤታቸው ከተመለሱ በኃላ…
#SUDAN : ጎረቤታችን ሱዳን ከአፍሪካ ህብረት (AU) አባልነት ታገደች።

የአፍሪካ ህብረት ሱዳን በየትኛውም የድርጊት መርሃ ግብሮቹ ላይ እንዳትሳተፍ አግዷታል።

እገዳው የሽግግር ሂደቱን ይመራ የነበረው የሲቪል አስተዳደር ወደ ቦታው እስከሚመለስ የሚቀጥል ነው ማለቱን አል አይን ዘግቧል።

* የአፍሪካ ህብረት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል (በAMANI AFRICA)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተጨማሪ

ሱዳን በአፍሪካ ህብረት ከአባልነት መታገዷን ተከትሎ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ የድርድር ሂደት ላይ እንደማትሳተፍ ተሰምቷል።

በየትኞቹም የድርጊት መርሃ ግብሮቹ እንዳትሳተፍ በአፍሪካ ህብረት የታገደችው ሱዳን የአፍሪካ ህብረት መር በሆነው የግድቡ የድርድር ሂደት እንደማትሳተፍ አል ዐይን ኒውስ የአማርኛው አገልግሎት ከህብረቱ ምንጮች መረጃ ማግኘቱን አሳውቋል።

ዜና ወኪሉ እገዳው በሁሉም የህብረቱ እንቅስቃሴዎች መባሉ የግድቡን የድርድር ሂደት እንደሚመለከት የህብረቱ ምንጮች ገልፀውልኛል ብሏል።

ውሳኔው የሲቪል አስተዳደር ወደቦታው እስከሚመለስ ድረስ የሚቀጥል ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
Pዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 19 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,815 የላብራቶሪ ምርመራ 472 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 510 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ/ም (በእቅድ ደረጃ ያለ ቀን) መንግስት ለመመስረት ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል። ይህን የገለፁት የህዝበ ወሳኔው ማድፈፀሚያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ምትኩ ከድር ናቸው። በፌዴሬሽን ምክር ቤት በኩል የሚያልቁ ጉዳዮች አልቀው በጊዜ የደቡብ ክልል መንግስት የስልጣን ርክክብ ማድረግ የሚችል ከሆነ ጥቅምት 29 የክልሉን…
#Update

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የፊታችን ቅዳሜ አስቸኳይ ስብሰባ የሚያካሂድ ሲሆን በዚሁ ስብሰባ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ውሳኔ ውጤትን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ ለ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ በሰጡት ቃል ፥ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝበ ውሳኔውን ውጤት ለፌደሬሽን ም/ቤት በደብዳቤ ማሳወቁን፤ ምክር ቤቱም ቅዳሜ ጥቅምት 20/2014 በሚያካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የህዝበ ውሳኔውን ውጤት ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።

ከዚህ ስብሰባ አንድ ቀን በኃላ ሰኞ ዕለት የደቡብ ክልል ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ የሚያደርግ ሲሆን በዚሁ ስብሰባ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 11ኛው ክልል መሆኑ ይረጋገጣል/የደቡብ ክልል ምክር ቤት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሆኖ መውጣቱን ይፋ ያደርጋል ተብሏል።

በአስቸኳይ ስብሰባው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ ክልል የስልጣን የሚያስረክብ መሆኑንም ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ ላይ አስነብቧል።

@tikvahethiopia