TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ የመንግስት የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ ዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓም፣ ዐድዋ አካባቢ የሚገኝ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር /TPLF/ ወታደራዊ ትጥቅ እና ወታደራዊ አልባሳትን አመሳስሎ የሚያመርትበት ማዕከል በአየር ድብደባ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ሲል አሳውቋል። ከዚሁ ከአየር ጥቃት ጋር በተያያዘ በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የትግራይ ነፃ አውጪ ቃል አቃባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የጥቃቱን መፈፀሙን…
#EthiopianAirForce
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ክልል የሚወስደውን የአየር ጥቃት የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት መቐለ ኵሃ አካባቢ የአየር ጥቃት ፈፅሟል።
የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳሳወቀው ፥ ዛሬ መቐለ ኲሃ አካባቢ የተፈፀመው የአየር ድብደባ ኢላማው የልዩ ኃይል ፖሊስ ማሠልጠኛ ተቋም ነው።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ በአየር የተመታው ተቋም በአሁኑ ወቅት በርካታ በአሸባሪነት የተፈረጀው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ቡድን ታጣቂዎች እየሰለጠኑበት ያለ ተቋም መሆኑን አመልክቷል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በአዲሱ የኢትዮጵያ መንግስት የተቋቋመና በተለይም በአሁን ወቅት ወቃታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለውጭ እና ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን እንዲሁም ለሚነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ እየሰጠ የሚገኝ ተቋም ነው።
ፎቶ : ፋይል
@tikvahethiopia