TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት 12ኛ ክልል እንዲቋቋም የሚያስችል ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል። ምክር ቤቱ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር የነበሩ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል። ሕዝበ ውሳኔ የሚያካሂዱት ፦ - የወላይታ ዞን፣…
#ደቡብ_ኢትዮጵያ_ክልል

" በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ "

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ፦
- የወላይታ፣
- የጋሞ፣
- የጎፋ፣
- የደቡብ ኦሞ፣
- የጌዴኦ፣
- የኮንሶ ዞኖች እንዲሁም
- የደራሼ፣
- የአማሮ፣
- የቡርጂ፣
- የአሌ፣
- የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በጋራ " የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል " ለመመስረት ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጿል።

ም/ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት እንዲያስችል የሕዝብን ይሁንታ ማረጋገጥ በማስፈለጉ ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ በሆነ መልኩ ገለልተኛ በሆነው ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አማካኝነት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ ወስኗል።

የሕዝብ ውሳኔው ውጤት ሪፖርትም ለምክር ቤቱ እንዲቀርብ፣ እንዲሁም የሕዝብ ውሳኔው ሂደት ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና የሕዝብን ሰፊ ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ የሀድያ ፣ ሀላባ ፣ ከምባታ ጠምባሮ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ  ዞኖችና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አንድ ላይ የሚቀጥሉ ይሆናል ብሏል።

@tikvahethiopia