TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN : የሱዳን ጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክ እየተካሄደ ያለውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የሚደግፍ መግለጫ ለማውጣት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወደማይታወቅ ቦታ ተወስደዋል ሲል አል አረቢያ ዘግቧል። በመዲናይቱ ካርቱም ውስጥ አብዛኛዎቹ የአገሪቱ ካቢኔ አባላት እና በርካታ የመንግስት ደጋፊ ፓርቲ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቧል። @tikvahethiopia
" ሱዳን ሙሉ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እያጋጠማት ነው " - የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር

የሱዳን ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ሱዳን ሙሉ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እያጋጠማት ነው ብሏል።

ሚኒስቴሩ ሁሉም እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱም አሳስቧል።

የሱዳን ህዝብ ወታደራዊው ኃይል የሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ለማገድ የሚያደርገውን ጥረት ለማስቆም መሞከር አለበት ሲል ለሮይተርስ በሰጠው መግለጫ አክሏል።

የሱዳን ሽግግር መንግስትን በኃይል ለመቀየር መሞከር አሜሪካ ለሱዳን የምታደርገውን ድጋፍ ሊያሳጣ እንደሚችል ደግሞ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ሀገራቸው በሱዳን ያለው ፖለቲካዊ ለውጥ እንደሚያሳስባት አስታውቀዋል፡፡

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር መንግስት በወታደራዊ ቁጥጥር ስር መዋሉን አስመልክቶ አሜሪካ ሁኔታውን በከፍተኛ ሁኔታ እየተከታተለችው ነው ብለዋል።

አሁናዊ ተጨማሪ መረጃ ፦ የሱዳን ጦር የሱዳን ቲቪ እና የሬዲዮ ዋና መስሪያ ቤትን በመውረር ሠራተኞችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

መረጃዎቹ ከአል አረቢያ፣ ከኤፍ ፒ የተገኙ ናቸው።

@tikvahethiopia
ፒተር ማውረር ኢትዮጵያ ገብተዋል።

የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ፕሬዝዳንት ፒተር ማውረር በኢትዮጵያ ያለውን ሰብአዊነት ሁኔታ ለመገምገም ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ታውቋል።

ማውረር በኢትዮጵያ 3 ቀናት የሚቆዩ ሲሆን ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር በአሁናዊ ሁኔታ ዙሪያ ይወያያሉ።

በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ተወካዮች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

Credit : ICRC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Arbaminch : የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 22ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ እያካሄደ ነው። ጉባኤው ለቀጣይ 4 ዓመት ከ6 መቶ ሺ በላይ አባላት ያሉትን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር (ኢመማን) የሚመር ፕሬዘዳንት እና የስራ አስፈፃሚ አባላትን በዛሬው እለት ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪ የማህበሩን የቀጣይ 4 አመት ተግባራት ላይ ወሳኔ የሚሰጥ ይሆናል:: በጉባኤው መክፈቻ ላይ የሀገር…
#Update

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር (ኢመማ) ለሁለት ኢትዮጵያውያን እውቅና ሰጠ።

የኢትዮጵያ መምህርን ማህበር በ22ኛ ጠቅላላ ግባኤው ላይ ለቀድሞው ጠ/ሚ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና ለጋዜጠኛና መምህር ዮናስ ከበደ እውቅና ሰጥቷል ፤ ጋዜጠኛ እና መምህር ዮናስን የክብር አባሳደርም ሆነዋል።

እውቅናው የተሰጣቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስተር አቶ ሀይለማሪያም ደስላኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ መምህራን የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ለደረጉት አስተዋፆ እና ስልጣናቸውን በሰላማዊ መንገደ እንዲተላላፍ ስላደረጉ መሆኑ በመድረኩ ተፈልጿል።

ጋዜጠኛ ዮሀንስ ከበደ ደግሞ በመምህርነት ለባረከቱት አስተዋፆ እና መምህርነትን በመልካመነት ለማስተዋወቅ በሚሰሯቸው ተግባራት የዋንጫ ሽልማትና የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባሰደርነት ማእረግ ተሰጥቷቸዋል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም በስራ መደራረብ በአርባ ምንጭ እየተካሄደ ባለው መድረክ ባይገኙም ጋዜጠኛ እና መምህሩ ዮናስ በመድረኩ ተገኝተው የተዘጋጀላቸውን ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 22ኛ ጠቅላላ ግባኤ በአርባምንጭ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን / ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሱዳን ሙሉ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እያጋጠማት ነው " - የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር የሱዳን ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ሱዳን ሙሉ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እያጋጠማት ነው ብሏል። ሚኒስቴሩ ሁሉም እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱም አሳስቧል። የሱዳን ህዝብ ወታደራዊው ኃይል የሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ለማገድ የሚያደርገውን ጥረት ለማስቆም መሞከር አለበት ሲል ለሮይተርስ በሰጠው መግለጫ አክሏል።…
በሱዳን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ።

የሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን መግለጫ ሰጥተዋል። በሀገሪቱ የአስቸኳ ጊዜ አዋጄ መታወጁን አስታውቀዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ ጀነራል አልቡርሀን አልተናገሩም።

ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን በመግለጫቸው የሉአላዊ ምክር ቤት እና ሚኒስትሮች ምክር ቤት መፍረሱን ፤ የክልሎች አሰተዳዳሪዎች እና ሌሎች አመራሮች ከስልጣን መነሳታቸውን አስታውቀዋል።

በሱዳን በሲቪል አስተዳድሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት የተካሄደ ሲሆን ጠ/ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን ጨምሮ በርካታ የሲቪል አስተዳድሩ አመራሮች በእስር ላይ ናቸው።

መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሱዳን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ። የሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን መግለጫ ሰጥተዋል። በሀገሪቱ የአስቸኳ ጊዜ አዋጄ መታወጁን አስታውቀዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ ጀነራል አልቡርሀን አልተናገሩም። ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን በመግለጫቸው የሉአላዊ ምክር ቤት እና ሚኒስትሮች ምክር ቤት መፍረሱን ፤ የክልሎች አሰተዳዳሪዎች እና ሌሎች…
#SUDAN : የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ያለው ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ አሳውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሱዳን ጉዳይ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው የኢትዮጵያ መንግሰት የሁለቱን ህዝቦች ለከፍለ ዘመናት የቆየ ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ ሱዳን አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልጿል።

በሲቪል መንግስቱና በወታደራዊ ሃይሉ መካከል የስልጣን ሽግግር በሚካሄድበት ሁኔታ ላይ የኢትዮጵያ መንግሰት ኩሰዳን ጋር በቅርበት ሲሰራ መቆቱንም አስታውሷል።

አሁንም “በሱዳን የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ ሁሉም ወገኖች በሰላማዊ ሁኔታ እንዲሰሩ የኢትዮጵያ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህ ሂደት የሱዳን መንግስት በሚያካሂደው የዴሞክራሲ ግንባታና የሽግግር ህገ መንግስቱ ላይ በሰፈረው መርህ መሰረት ኢትዮጵያ ድጋፏን እንደምታደርግ ገልጿል።

“ኢትዮጵያ የሱዳን ሉዐላዊነት የማይጣስበትና የሱዳናውያን ፍላጎት የሚከበርበትን መርህ እንዲጠበቅና የውጭ ሃይሎች በአገሪቱ ጣልቃ አለመግባታቸው አስፈላጊነትን በድጋሚ ታስገነዝባለች” ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት የሱዳን ህዝቦች ጥበባዊ በሆነ መንገድ ችግሮቻቸውን በሰላማዊ ሁኔታ እንደሚፈቱም ያምናል ሲል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አመልክቷል።

እንደ ሁልጊዜው ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን ዴሞክራሲያዊ ሂደት ሰኬት ጎን ይቆማልም ሲል አስታውቋል።

CREDIT : ENA

@tikvahethiopia
#OFC : የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ በቅርቡ ብሔራዊ ውይይትን አስመልክቶ ስለአቀረበው ሐሳብ ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መገለጫ ሰጥቷል።

ባለፉት 3 ዓመታት ሆነ ቀደም ሲል በነበሩት ዓመታት ውስጥ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የኢትዮጵያን ሥር የሰደደና ከምንጊዜውም በላይ እየተባባሰ የመጣውን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት የሚያግዝ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ መጠየቁ በመግለጫው አስታውሷል።

ኦፌኮ ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ አቅርቤዋለሁ ላለው የብሄራዊ ውይይት ጥያቄ ገዥው ፓርቲ እና መንግስት እንዲሁም ደጋፊዎቹ ሐሳቡን በበጎነት ከመውሰድ ይልቅ ፓርቲውም ማግለል እና ማስፈራራት ላይ ያነጣጠረ አሉታዊ የሚዲያ ዘመቻ አድርገዋል ሲል ወቅሷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ገዢው ፓርቲ ስለብሔራዊ ውይይት አስፈላጊነት በለሆሳስ ማወጅ ጀምሯል ያለው ኦፌኮ "ብዙዎች ግለሰቦችና ቡድኖች የመንግሥትን የውይይት ማስታወቂያን በጣም ዘግይቷል ብለው ውድቅ ያደርጋሉ ፓርቲያችን ግን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ከሚቀር ዘገየ እንላለን እንጂ የታሰበው ውይይት በትክክል እና በእውነቱ ተመርቶ ኢትዮጵያን ከውድቀት ቢታደግ እንመርጣለን" ብሏል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvhaethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OFC : የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ በቅርቡ ብሔራዊ ውይይትን አስመልክቶ ስለአቀረበው ሐሳብ ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መገለጫ ሰጥቷል። ባለፉት 3 ዓመታት ሆነ ቀደም ሲል በነበሩት ዓመታት ውስጥ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የኢትዮጵያን ሥር የሰደደና ከምንጊዜውም በላይ እየተባባሰ የመጣውን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት የሚያግዝ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ መጠየቁ በመግለጫው…
#OFC : ይደረጋል የተባለው ብሔራዊ ውይይትን በተመለከተ ኦፌኮ ብሄራዊ ውይይቱ ሊያምላ ይገባዋል ያላቸው ቅድመ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው ፦

1. በአሁኑ ጊዜ በሕግ ማስከበር ተጀምሮ የሕልውና ማስጠበቅ እየተባለ የሚካሄደው ጦርነት በሁሉ አቅጣጫ በአስቸኳይ ቁሞ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ።

2. ውይይቱ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና እና ድጋፍ በተሰጣቸው ወገኖች ሁሉ ተቀባይነት ባለው ገለልተኛ እና ተዓማኒ፣ የማያዳላና በሁሉም ወገኖች ተቀባይነት ባለው አካል መመራት አለበት።

3. ብሔራዊ ውይይቱ ተቃዋሚ የታጠቁ ቡድኖችን ጨምሮ ሁሉንም የፖለቲካ ቡድኖች በእውነት ያካተተ መሆን አለበት። የእነዚያን ቡግንኖች ውክልና ለማንቃትም ሕጋዊ እና የደህንነት መሰናክሎች ከወዲሁ መወገድ አለባቸው።

4. የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ተፈትተው በውይይቱ እንዲሳተፉ መፍቀድ አለበት።

(ከኦፌኮ መግለጫ የተወሰደ)

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የአሜሪካ ተ/ም/ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውሳኔ አሳልፏል።

ኮሚቴው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም ሁከትና ሰብአዊ መብት ረገጣዎችን ያወገዘ ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ያሉ ሁሉም ተዋጊ ኃይሎች ግጭት እንዲያቆሙ፣ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ፣ ያልተገደበ የሰብአዊ ተደራሽነትን እንዲፈቅዱና ተዓማኒነት ያላቸው የግፍ እና ጭካኔ ድርጊቶች ክሶችን በተመለከተ ለገለልተኛ ምርመራዎች እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።

የውሳኔ ሃሳቡ ከተላለፈ በኋላ ካረን ባስ ባወጡት መግለጫ፥ " እኔ ይህንን ውሳኔ የመራሁት በብሔር፣ በፖለቲካና በታሪክ የተወሳሰበ ለዚህ ሁለገብ ግጭት ሰላማዊ ፣ የድርድር መፍትሄ ማየት ስለምፈልግ ነው" ብለዋል።

ባስ እኤአ በጥቅምት 2020 የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ግጭቱ መጀመሩንና ግጭቱ ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች መስፋቱን ገልፀዋል።

" H.Res 445 " የተሰኘው ይህ የውሳኔ ሃሳብ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁከት እንዲቆም ፤ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) በአስቸኳይ ተኩስ እንዲያቆሙ ይጠይቃል።

ከውሳኔ ሀሳቡ በተጨማሪ TPLF ህፃናትን ለውትድርና መጠቀም እንዲያቆም፤ ከአማራ ክልልም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ፤ ከOLA-ሸኔ ጋር ያለውን ጥምረት እንዲያቆም ተጠይቋል።

ባስ፥ የውሳኔ ሀሳቡ ያልተገደበ ሰብዓዊ ተደራሽነት እንዲኖር ሚጠይቅ በቀን ቢያንስ 100 የጭነት መኪናዎችን ወደትግራይ መላክ እንዳለበት የሚገልፅ ነው ብለዋል።

TPLF መራሾቹ ኃይሎች ጦርነት ለመቀጠል ሲሉ የጭነት መኪናዎችን ወይም የእርዳታ ዕቃዎችን ከመዝረፍ እንዲቆጠቡ እንደሚያሳስብም ተናግረዋል።

telegra.ph/US-HFAC-10-25

@tikvahethiopia
#ሰላም_እና_እርቅ !

በጅሌ ጥሙጋ እና ሃደለኤላ ወረዳ (አፋር ክልል) የሰላም እና እርቅ ኮንፍረንስ በሃደሌኤላ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በኮንፈረንሱ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች ተሣታፊ ይሆናሉ።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ኮንፈረንስ በሁለቱ ወረዳዎች መካከል ያለውን የሰላም እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የበለጠ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ውይይቶች ይደረጋሉ።

መረጃው የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሱዳን ሙሉ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እያጋጠማት ነው " - የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር የሱዳን ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ሱዳን ሙሉ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እያጋጠማት ነው ብሏል። ሚኒስቴሩ ሁሉም እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱም አሳስቧል። የሱዳን ህዝብ ወታደራዊው ኃይል የሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ለማገድ የሚያደርገውን ጥረት ለማስቆም መሞከር አለበት ሲል ለሮይተርስ በሰጠው መግለጫ አክሏል።…
#SUDAN : አሜሪካዊው ባለስልጣን ሱዳንን ለቀው መውጣታቸው ተነግሯል።

ላለፉት 2 ቀናት ካርቱም ውስጥ የነበሩት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ከሱዳን ወጥተው ወደ ሃገራቸው ሄደዋል።

ፌልትማን ካርቱም በነበሩባቸው ቀናት ከሱዳን የሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ጋር ሲመክሩ እንደነበር አል ዓይን ዘግቧል።

ዛሬ በሱዳን ሲቪል አስተዳድሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት መካሄዱ ጠ/ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን ጨምሮ በርካታ የሲቪል አስተዳድሩ አመራሮች መታሰራቸው ይታወቃል።

አሜሪካ በሱዳን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ እንደሚያሳስባት ፤ የሱዳን ሽግግር መንግስትን በኃይል ለመቀየር መሞከርም አሜሪካ ለሱዳን የምታደርገውን ድጋፍ ሊያሳጣ እንደሚችል በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ማስታወቋ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 19 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,703 የላብራቶሪ ምርመራ 337 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 491 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#Facebook

CNN ለአሜሪካ ህግ መምሪያ ምክር ቤት የቀረበ አንድ ሚስጥራዊ የፌስቡክ ኩባንያ ሰነድ መመልከቱን አሳውቋል።

ይኸው ሚስጥራዊ ሰነድ ፌስቡክ በኢትዮጵያ ግጭትን እያባባሰ እንደሆነ እያወቀ አንደችም ርምጃ እንዳልወሰደ የሚገልፅ ነው።

የፌስቡክ ኩባንያ ኢትዮጵያን "ለግጭት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑ ሀገራት" በሚለው ምድብ ያስቀመጣት ሀገር ናት።

የኩባንያው ሰራተኞች ፌስቡክ በኢትዮጵያ ግጭትን ለማባባስ እየዋለ መሆኑን ላቀረቧቸው ጥቆማዎች ኩባንያው ምላሽ እንዳልሰጠ ከሚስጥራዊው ሰነድ መመልከቱን CNN ዘግቧል።

ይኸው ሚስጥራዊ ነው የተባለው የፌስቡክ ሰነድ የውጭ መንግስታት እንዲሁም ድርጅቶች በኢትዮጵያ #የጥላቻ_ንግግር እና ግጭትን ለመስበክና ለማሰራጨት ፌስቡክን እንደተጠቀሙበት ያሳያል ሲል CNN ባወጣው ዘገባ ጠቅሷል።

ሙሉ የCNN ሪፖርት በዚህ ተያያዟል : https://edition.cnn.com/2021/10/25/business/ethiopia-violence-facebook-papers-cmd-intl/index.html?utm_content=2021-10-25T11%3A51%3A04&utm_term=link&utm_medium=social&utm_source=twCNN

Credit : CNN/WAZEMA

@tikvahethiopia
" ... ከግድያው ጋር በተያያዘ 10 ተጠርጣሪዎች ታስረዋል ፤ የገዳዮቹም ማንነት በምርመራ ላይ ነው " - አቶ ምስጋኑ ዋቅጋሪ

የነቀምቴ ከተማ የስራ እድል ፈጠራ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ ፈይሳ ቅዳሜ ዕለት በመንግስት ስራ ላይ ቆይተው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ከጀርባቸው በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን የነቀምቴ ፀጥታ እና አስተዳደር ፅ/ቤት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ አስታወቀ።

የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ምስጋኑ ዋቅጋሪ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ " ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች አቶ መልካሙ ላይ ጥይት ካዘነቡ በኃላ 03 ቀበሌ ውስጥ ወልደአራራ ቤተክርስቲያን አካባቢ ደርሰን በፍጥነት ወደነቀምቴ ሆስፒታል ብንወስደውም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም" ብለዋል።

ከግድያው ጋር በተያያዘ 10 ተጠርጣሪዎች መታሰራቸውን እና የገዳዮቹም ማንነት በምርመራ ላይ መሆኑን አቶ ምስጋኑ ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።

አቶ ምስጋኑ ፤ " ነቀምቴ ከተማ ውስጥ መንግስትን የሚቃወም ኃይል ታጥቆ እና ሲቪል መስሎ አልፎ አልፎ በመንግስት አመራሮች ላይ ግድያ ሲፈፅም ቆይቷል፤ አቶ መልካሙንም የገደለው ይኸው ኃይል ነው ብለን እንጠረጥራለን ነገር ግን የሚረጋገጠው በፖሊስ ምርመራ ነው " ብለዋል።

ባለፉት 4 ዓመታት በከተማይቱ ማንነታቸው አልታወቀም በተባሉ አካላት በርካታ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ንፁሃን ዜጎች የተገደሉ ሲሆን የምርመራ ሂደቱ በፖሊስ እጅ መሆኑን የነቀምቴ ፀጥታ እና አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ምስጋኑ ዋቅጋሪ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

Photo Credit : Nekemte Communication

@tikvahethiopia