TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HappeningNow : በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ የሠላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በኮንፈረንሱ ላይ ከፍተኛ የክልል፣ የዞን አመራሮች ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ወጣቶች ተገኝተዋል።

በጉራፈርዳ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ከዚህ ቀደም በነበረው የፀጥታ ችግር በርካታ ነዋሪዎች መገደላቸው ፤ እና መፈናቀላቸው አይዘነጋም።

ፎቶ : ከቤንች ሸኮ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#ENDF : የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዛሬ በምእራብ ግንባር የአየር ድብደባ መፈፀሙ ተገለፀ።

ከኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፤ ዛሬ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ማሠልጠኛ እና የሰው ኃይል ማደራጃ የሆነው ማይጠብሪ በአየር ተመቷል ሲል አሳውቋል።

ፎቶ : ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ENDF : የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዛሬ በምእራብ ግንባር የአየር ድብደባ መፈፀሙ ተገለፀ። ከኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፤ ዛሬ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ማሠልጠኛ እና የሰው ኃይል ማደራጃ የሆነው ማይጠብሪ በአየር ተመቷል ሲል አሳውቋል። ፎቶ : ፋይል @tikvahethiopia
#ተጨማሪ

የመንግስት የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ ዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓም፣ ዐድዋ አካባቢ የሚገኝ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር /TPLF/ ወታደራዊ ትጥቅ እና ወታደራዊ አልባሳትን አመሳስሎ የሚያመርትበት ማዕከል በአየር ድብደባ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ሲል አሳውቋል።

ከዚሁ ከአየር ጥቃት ጋር በተያያዘ በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የትግራይ ነፃ አውጪ ቃል አቃባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የጥቃቱን መፈፀሙን ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።

"የመጀመረው ጥቃት በአንድ የገጠር ሆስፒታል አቅራቢያ ተፈጽሟል" ነው ያሉት።

በዐድዋ በተፈጸመው ጥቃት "ቀደም ሲል በኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደሮች ውድመት ደርሶበት የነበረው እና ጥቂት ተርፎ የነበረው የአልሜዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ መመታቱን" ለሮይተርስ ተናግረዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ስደተኞች የሚገኙባቸው የማይ አኒ እና አዲ ሃሩሽ የመጠለያ ጣብያዎች በማይጠምሪ አቅራቢያ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን ሚንስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የመጠለያ ጣብያዎቹ ለአየር ጥቃቱ ተጋላጭ እንዳልነበሩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ እየፈፀመ የሚገኘው የአየር ጥቃት ከንፁሃን በራቀ ሁኔታ በሽብረተኛ ድርጅትነት የተፈረጀውን TPLF ኢላማ ያደረገ እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጿል።

ፎቶ : ፋይል

@tikvahethiopia
የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣኗ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ እና ሱዳን ይጓዛሉ።

ኮሚሽነር ጁታ በሶስቱ ሀገራት ቆይታ የሚያደርጉት ከጥምቅት 14 እስከ ጥቅምት 17 ድረስ ነው።

ጉዟቸው የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ቀንድ #ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም ከአፍሪካ ጋር ያለውን ጠንካራ ግንኙነት ለመግለፅ እና ለማጠናከር ነው ተብሏል።

ነገ ሰኞ ኮሚሽነር ኡርፒላይነን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ አኔት ዌበር ጋር አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ማክሰኞ ከኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና ከገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ጋር ይገናኛሉ እንደ አውሮፓ ህብረት መረጃ።

በአዲስ አበባ ያላቸው ቆይታ ካጠናቀቁ በኃላ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች ስብሰባን ለመካፍል ኪጋሊ የሚገቡ ሲሆን በመጨረሻም ረቡዕ ዕለት በሱዳን ካርቱም የሽግግሩን አመራሮች የሚያገኙ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት እና ሱዳን የፖለቲካ ውይይትንም እንደሚያስጀምሩ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 11 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,377 የላብራቶሪ ምርመራ 247 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 523 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#UGANDA : የኡጋንዳ የፀረ ሙስና መ/ቤት በሀገሪቱ ያለውን ሙስና ለመቆጣጠር ልጆችን በመጠቀም አዲስ ዘዴ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አሳወቀ።

መ/ቤቱ ኃላፊ ቤቲ ካምያ ለአውሮፓ ሕብረት የዲፕሎማቶች ቡድን ሲናገሩ እንደተሰማው ፤ ወላጆችን በልጆቻቸው በኩል በመከታተል አዲስ የሙስና መቆጣጠሪያ መንገድ እንዳለ አመለክተዋል።

ይኸው ዘዴ ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲከታተሉ የሚደረግበት እንደሆነና ወጪ ቆጣቢ መሆኑንም ነው ያመለከቱት።

አዲሱ ሙስናን የመከታተያ መንገድ ትኩረቱን በተማሪ ልጆች ላይ ያደረገ ሲሆን በተለይ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያሉ ልጆች ሕገወጥ ገንዘብ ምን እንደሆነ እንዲያውቁና "ወላጆቻቸው ያላቸው ቅንጡ ቤትና መኪና እንዲሁም ሌሎች ወጪዎች በሚያገኙት ደሞዝ የሚሸፈኑ መሆናቸውን እንዲጠይቁ እንፈልጋልን" ቤቲ ካምያ ተናግረዋል።

በተጨማሪ ከፍተኛ ገንዘብ በሚከፈልባቸው ትምህርት ቤቶች ያሉ መምህራን 10 ዓመት ለሆናቸው ተማሪዎች የአባታቸውን ስም፣ የት እንደሚሰራ፣ የሥራው ኃላፊነት፣ የሚያሽከረክረው መኪና ዋጋ እና የቤታቸውን ፎቶ የሚያሳይ የቤት ሥራ እንዲሰጡ በማድረግ የሙስና ክትትል ለማድረግ እንዳቀዱ ኃላፊዋ ተናግረዋል።

ነገር ግን አንድ ተማሪ ከታዘዘው የቤት ሥራ ላይ የሚገኝን መረጃ ለፀረ ሙስና ባለሥልጣን አሳልፎ መስጠት ይቻላል ወይ የሚለው ጥያቄ ግልጽ መልስ አልተሰጠበትም።

ባለሥልጣኗ መሥሪያ ቤታቸው ከአገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ሙስናን በሚመለከት ውይይት እንዲያደርጉ ይበረታታሉ ማለታቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
የጎረቤታችን ሱዳን የፖለቲካ ቀውስ !

ጎረቤታችን ሱዳን በከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ናት።

ዛሬ ደግሞ ከባለፈው ሌላ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሳይደረግ እንዳልቀረ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየተዘገበ ነው።

የታጠቁ ወታደሮች በርካታ የአገሪቱ የሽግግር መንግሥት አባላትን በቤታቸው ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው ይነገራል።

ማንነታቸው ያልተወቁ ወታደራዊ ኃይሎች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክን መኖሪያ ቤትን መክበባቸውን ተዘግቧል።

ወታደሮቹ የሽግግር መንግሥቱ አባል የሆኑ 4 ሚኒስትሮችን እና 1 ሲቪልን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተነግሯል።

ባለሥልጣናቱን በቁጥጥር ስር ያዋለው ወታደራዊ አካል ማን እንደሆነ አልታወቀም።

በከባድ ሁኔታ የታጠቁ ወታደሮች እና የፀጥታ ኃይሎች በካርቱም ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የተሰማሩ ሲሆን የነዋሪዎችን እንቅስቃሴ ገድበዋል።

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተካሄደ መሆኑ ከተሰማ በኋላ የሲቪል አስተዳደሩን የሚደግፉ ሰዎች ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ ለመውጣት መሞከራቸውን ተከትሎ ወደ ዋና ከተማዋ የሚያስገቡ ዋና መንገዶችን ወታደሮች ዘግተዋል።

የሱዳን መገናኛ ብዙኀን እንደዘገቡት በዋና ከተማዋ ካርቱም ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል።

የሱዳንን የሽግግር መንግሥትን በጋራ በሚመሩት ወታደራዊ እና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ወራት ተቆጥረዋል።

ባለፉት ሳምንታት ወታደራዊ መሪዎቹንና የሲቪል አስተዳደሮቹን የሚደግፉ ሰልፎች በአገሪቱ ውስጥ ሲካሄዱ ነበር።

መረጃው የተገኘው ከቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ፣ የቱርክ እና እንግሊዝ አምባሳደሮች ውይይት አካሄዱ።

ትላንት በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አእምሮ በሱዳን ከቱርክ አምባሳደር ኢርፋን ናዚር ኦግሎ ጋር ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪ አምባሳደር ይበልጣል ከእንግሊዝ አምባሳደር ጊልስ ሊቨር ጋር በተናጠል ተገናኝተው መክረዋል።

ውይይቱ የነበረው በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ እና ሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ስላለው ችግር ነበር።

ውይይቱን ተከትሎ አምባሳደር ይበልጣል ባወጡት ፅሁፍ ፤ " ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ፤ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ ቀጣይ ምክክር ለማድረግም ከክቡራን አምባሳደሮች ጋር ተስማምተነናል" ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የጎረቤታችን ሱዳን የፖለቲካ ቀውስ ! ጎረቤታችን ሱዳን በከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ናት። ዛሬ ደግሞ ከባለፈው ሌላ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሳይደረግ እንዳልቀረ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየተዘገበ ነው። የታጠቁ ወታደሮች በርካታ የአገሪቱ የሽግግር መንግሥት አባላትን በቤታቸው ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው ይነገራል። ማንነታቸው ያልተወቁ ወታደራዊ ኃይሎች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክን…
#SUDAN : የሱዳን ጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክ እየተካሄደ ያለውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የሚደግፍ መግለጫ ለማውጣት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወደማይታወቅ ቦታ ተወስደዋል ሲል አል አረቢያ ዘግቧል።

በመዲናይቱ ካርቱም ውስጥ አብዛኛዎቹ የአገሪቱ ካቢኔ አባላት እና በርካታ የመንግስት ደጋፊ ፓርቲ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Arbaminch : የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 22ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ እያካሄደ ነው።

ጉባኤው ለቀጣይ 4 ዓመት ከ6 መቶ ሺ በላይ አባላት ያሉትን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር (ኢመማን) የሚመር ፕሬዘዳንት እና የስራ አስፈፃሚ አባላትን በዛሬው እለት ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪ የማህበሩን የቀጣይ 4 አመት ተግባራት ላይ ወሳኔ የሚሰጥ ይሆናል::

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የሀገር ሽማግሌወች እና የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ነው መካሄድ የጀመረው።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከ6 መቶ ሺ በላይ መምህራንን በአባልነት የያዘና አፍሪቃን በመወከል የአለም አቀፍ መምህራን ማህበር አባል ነው።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን / በጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው

@tikvahethiopia