TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Monkeypox

ጎረቤት ሀገር ኬንያ የመጀመሪያ በዝርጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) ሳይያዝ አልቀረም ተብሎ የተጠረጠረ ሰው ማግኘቷን አሳውቃለች።

ሀገሪቱ የተጠርጣሪውን ናሙና ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሴኔጋል እንዲላክ አድርጋለች።

የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሀገሪቱ የመመርመር አቅሟ ውስን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ናሙናው ወደ ሴኔጋል እንዲላክ መደረጉን አሳውቋል።

ናሙናው በትክክል ቫይረሱ መኖሩን የሚያረጋግጥ ከሆነ ሀገሪቱ በጀት መድባ ለምርመራ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በማሟላት ምርመራው በሀገር ውስጥ እንዲደረግ ለማድረግ መሰራት አለበትም ብሏል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ በአፍሪካ የዝንጀሮ የፈንጣጣ በሽታ በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ፣ ናይጄሪያ፣ ካሜሩን እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፓብሊክ ቫይረሱ በስፋት እየተሰራጨ ነው።

@tikvahethiopia
#Monkeypox #እንድናውቀው

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) በተለያዩ ሀገራት እየተሰራጨ ነው። ጎረቤት ኬንያም ከዚህ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ አግኝታ ናሙናዎችን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሴኔጋል ልካለች።

ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር በተያያዘ ማወቅ ያለብን ጉዳዮች ፦

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው ?

በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዙ ሰዎች መጀመሪያ ላይ ሙቀት፣ራስ ምታት፣ የጀርባ ሕመም፣ የጡንቻ ሕመም፣ የሰውነት ማበጥ እና በማንኛውም ነገር ላይ ፍላጎት ማጣት ይታይባቸዋል።

ሙቀቱ ጋብ ሲል ሰውነት ከፊት ጀምሮ ማሳከክ ይጀምራል። መላው ሰውነትን ቢያሳክክም ክንድና እግር የበለጠ ያሳክካሉ።

የሚከሰተው እከክ በጣም የሚያምና በተለያየ ደረጃ የሚያልፍ ነው።

ቆዳ ላይ የሚከሰተው እብጠት ኋላ ላይ ቆዳ እንዲቆስልና እንዲረግፍም ያደርል። ጠባሳ ጥሎም ሊያልፍ ይችላል። ሕመሙ በራሱ ጊዜ የሚጠፋ ሲሆን ከ14 - 21 ቀናት ይወስድበታል።

በሽታው እንዴት ይይዛል ?

በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ተጋላጭ ናቸው። በቆዳችን ክፍተቶች በኩል፣በዓይን፣ በአፍንጫ ወይም በአፍ በኩል ቫይረሱ ወደ ሰውነታች ይገባል።

በወሲብ ወቅት ባለ ንክኪም ቫይረሱ ይተላለፋል።

በቫይረሱ ከተያዙ ዝንጀሮዎች፣ አይጦች ወይም ሌሎች እንስሳት ጋር ንክኪ ከተደረገ ቫይረሱ ወደሰው ይተላለፋል። ቫይረሱ በልብስ/በሌሎች ንክኪ ባላቸው ጨርቆች በኩል ይተላለፋል።

ምን ያህል አስጊ ነው ?

አብዛኞቹ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ለከፋ ሕመም አይዳረጉም።

ልክእንደ ፈንጣጣ በተወሰኑ ሳምንታት ውስጥ ይጠፋል። ሆኖም ግን በሽታው ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስም ይችላል።

በምዕራብ አፍሪካ በበሽታው ሳቢያ የሞቱ ሰዎች አሉ።

ሕክምና አለው ?

ሕክምና የለውም። ስርጭቱን ግን መቆጣጠር ይቻላል።

Via BBC/WHO

@tikvahethiopia
#Monkeypox

(Europe)

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በአውሮፓ ሀገራት እጅግ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው ተብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሶስት እጥፍ መጨመሩን አሳውቀዋል።

እንደ አሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (CDC) መረጃ እስካሁን በዓለም ደረጃ ከ5,000 የሚበልጡ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ኬዞች ከ51 ሀገራት ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን በአውሮፓ ውስጥ ያለው ኬዝ ከአጠቃላዩ ኬዝ 90 በመቶውን ይሸፍናል ተብሏል።

እስካሁን ድረስ ባለው #ሞት ስለመመዝገቡ ሪፖርት አልተደረገም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Monkeypox (Europe) የዝንጀሮ ፈንጣጣ በአውሮፓ ሀገራት እጅግ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው ተብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሶስት እጥፍ መጨመሩን አሳውቀዋል። እንደ አሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (CDC) መረጃ እስካሁን በዓለም ደረጃ ከ5,000 የሚበልጡ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ኬዞች ከ51 ሀገራት ሪፖርት የተደረጉ…
#Monkeypox

(Africa)

የአፍሪካ የጤና ባለስልጣናት በአህጉሪቱ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ እየተስፋፋ መምጣቱን በመጠቆም እንደ #ድንገተኛ ሁናቴ እያስተናገዱት መሆኑን ገልፀዋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሚታዩትን የፍትሃዊነት ችግሮች ለማስወገድ የበለፀጉ ሀገራት ውስን የክትባት አቅርቦቶችን እንዲያካፍሉም ጠይቀዋል።

እስካሁን ባለው በአፍሪካ 1,800 የሚጠጉ የዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠረጠሩ ኬዞች ያሉ ሲሆን ከ70 በላይ ሰዎች እንደሞቱ ተነግሯል ፤ ነገር ግን በላብራቶሪ ምርመራ የተረጋገጠው 109 ኬዝ ብቻ ነው ተብሏል።

ለበሽታው ምርመራ የሚያስፈልጉ የላብራቶሪ ምርመራ ገብአቶች እጦት እና ደካማ የሆነ የክትትል ስርዓት ብዙ ኬዞች ሳይታወቁ እንዲቀሩ እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Monkeypox (Africa) የአፍሪካ የጤና ባለስልጣናት በአህጉሪቱ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ እየተስፋፋ መምጣቱን በመጠቆም እንደ #ድንገተኛ ሁናቴ እያስተናገዱት መሆኑን ገልፀዋል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሚታዩትን የፍትሃዊነት ችግሮች ለማስወገድ የበለፀጉ ሀገራት ውስን የክትባት አቅርቦቶችን እንዲያካፍሉም ጠይቀዋል። እስካሁን ባለው በአፍሪካ 1,800 የሚጠጉ የዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠረጠሩ ኬዞች…
#Monkeypox

(Ethiopia)

በኢትዮጵያ ፤ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ሳይያዙ አልቀሩም ተብሎ #የተጠረጠሩ 2 ሰዎች ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጋቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ምንም በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር / ኬዝ ካለበራቸው አሁን ላይ የተጠረጠሩ ኬዞችን ለዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ካደረጉ 7 ሀገራት አንዷ ናት ተብሏል (ሀገራቱ ኢትዮጵያ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ሞዛምቢክ ፣ ሴራሊዮን ፣ ሱዳን፣ ዩጋንዳ ናቸው) ።

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ናሙናቸው ውጭ ሀገር ተልኮ የምርመራ ውጤቱ እስኪታወቅ በለይቶ ማቆያ ይቆያሉ የተባለ ሲሆን ገለሰቦቹ ከፍተኛ የቆዳ በሽታ ምልክት ይታይባቸዋል ነው የተባለው።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣን ከሁለቱ አንደኛው ግለሰብ አሁን ላይ ከዝንጀሮ ፈጣጣ ውጪ የሌላ ምልክት እያሳየ ነው ብለዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የዝንጀሮ ፈንጣጣ መመርመሪያ የሌላት ሲሆን የተጠርጣሪዎቹ ናሙና መቼ ወደውጭ ሀገር እንደተላከ እንዲሁም ውጤቱ መቼ እንደሚደርስ የታወቀ ነገር እንደሌለ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Monkeypox

ጎረቤታችን ሱዳን በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች።

የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር በምዕራብ ዳርፉር የዝንጀሮ ፈንጣጣ ያለበት ሰው ማግኘቱን አሳውቋል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣው በብሔራዊ የህዝብ ጤና ቤተሙከራ በተካሄደ ምርመራ በአንድ የ 16 ዓመት ተማሪ ላይ ሀሙስ ዕለት መገኘቱ ተገልጿል።

ወረርሽኙ ከአንድ ሰው ውጭ በሌሎች ላይ አለመገኘቱን ሀገሪቱ አሳውቃለች።

ወረርሽኙ አለባቸው ተብለው የተጠረጠሩት 38 ሰዎች ቢሆኑም በሽታው የተገኘው ግን በአንድ ሰው ላይ ብቻ ነው ተብሏል።

የዳርፉር ግዛትና የሱዳን የጤና ሚኒስቴር ጉዳዩን እየተከታተሉት እንደሆነ ገልጸዋል።

መረጃውን የሱዳን ዜና አገልግሎት/ አል ዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia