TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በቦሌ ክፍለ ከተማ #በጦር_መሳሪያ የተደገፈ #ዘረፋ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ 24 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች፥ በትናንትናው እለት ከሌሊቱ 7 ሰዓት ከ20 የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ – 3 – 30212 ኦ.ሮ የሆነ ሚኒባስ ተሸከርካሪ በመያዝ ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ ህብረተሰቡ አስቀድሞ ለፖሊስ በሰጠው #ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ክትትል በማድረግ በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስፍራው ሰሚት ሴንትራል ሆቴል አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን፥ የሰሚት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር #ካሳሁን_ፍቃዱ ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅትም አንድ ሽጉጥ፣ ስምንት ጥይት፣ ሁለት ፓውዛ መብራቶች፣ የብረት መቁረጫ፣ 20 ማዳበሪያዎች እና ከተር እንደተገኘባቸውም ነው ምክትል ኮማንደሩ የተናገሩት። አሁን ላይም ፖሊስ ምርመራውን እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በቦሌ ክፍለ ከተማ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ የሚውሉ ልዩ ልዩ የኤሌክትሪክ ገመዶችን የሰረቁ ተጠርጣሪዎች በህብረተሰቡ ትብብር ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስታውሰዋል።

ህብረተሰቡም ጥቆማዎችን በመስጠትና መሰል ተግባራትን በመከወን እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የጥበቃ ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia