TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አሳዛኝ_ዜና⬇️

በሶማሊያ የፑንትላንድ የንግድ ከተማ በሆነችው ቦሳሶ ውስጥ ሦስት #ኢትዮጵያዊያን #በአይሲስ ታጣቂዎች #ሲገደሉ ቢያንስ አንድ መቁሰሉ ተዘገበ።

ስለጥቃቱ በቀዳሚነት የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት ታጣቂዎቹ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ይኖሩበታል በሚባለው ሳንቶስ ተብሎ በሚጣራው የከተማዋ ክፍል ውስጥ ባገኟቸው አራት ኢትዮጵያዊያን ላይ #ተኩስ ከፍተው ነው ጥቃቱን የፈፀሙት።

አንድ ስማቸውን ያልጠቀሱ የአካባቢው ባለስልጣን ኢትዮጵያዊያኑ በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ለቢቢሲ ሲያረጋግጡ፤ አፍቃሬ አይኤስ የሆነ ቡድንም በትዊተር ገጹ ላይ ስለጥቃቱ አስፍሯል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሃገራት የኤደን ባህረ ሰላጤን በትናንሽ ጀልባዎች በማቋረጥ ወደ የመንና የመካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት በህገ ወጥ መንገድ ለመሻገር የሚፈልጉ ስደተኞች #የቦሳሶን የባህር በር ይጠቀማሉ።

በአካባቢውም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንደሚገኙ ተገልጿል።

እነዚህ በጥቃቱ የሞቱትና የቆሰሉት ኢትዮጵያዊያንም በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች አማካይነት ባህሩን ተሻግረው በጦርነት ወደ የምትታመሰው #የመን ለመጓዝ በቦታው የነበሩ ስደተኞች እንደሆኑ ይታመናል።

አይሲስ ከቅርብ ወራት ወዲህ በጉልህ የሚታዩ በርካታ ጥቃቶችን በሶማሊያ ውስጥ እየፈፀመ ሲሆን በተለይ ደግሞ በፑንት ላንድ ግዛት ውስጥ የአይኤስ ቡደን ከሌሎች አካባቢዎች በበለጠ ሰፊ እንቅስቃሴ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል።

ፑንትላንድ በሰሜን ሶማሊያ የምትገኝ ከፊል ራስ ገዝ የሆነች ግዛት ናት።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia