TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MostWanted

ከኢትዮጵያ ያመለጠው ኤርትራዊ ሰው አዘዋዋሪ ኪዳኔ ዘካሪያስ ሀብተማርያም በኔዘርላንድስ በጥብቅ ከሚፈለጉ ዝርዝር ውስጥ ተካተተ።

የኔዘርላንድስ ዐቃቤ ሕግ ኤርትራዊውን በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪነት የሚፈለገውን ኪዳኔ ዘካርያስ ሀብተማርያምን በሕግ በጥብቅ ከሚፈለጉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ አካቶታል።

ኪዳኔ ዘካርያስ ሀብተማርያም ከሚቀርቡበት በርካታ ክሶች መካከል ፦
- ግድያ፣
- ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና
- በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም የሚሉት ይገኙበታል።

የኔዘርላንድስ ዐቃቤ ሕግ ኤርትራዊው ተይዞ በወንጀል እንዲጠየቅ በሚል በከፍተኛ ደረጃ ከሚፈለጉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ እንዳካተተው ተዘግቧል።

ኪዳኔ በአዲስ አበባ ለአንድ ዓመት ገደማ የሁለት ስደተኞች ግድያን ጨምሮ በስምንት ሰዎች ዝውውር ተከሶ የፍርድ ሂደቱን እየተከታተለ ሳለ ነው ከእስር ያመለጠው።

በወቅቱ "መጸዳጃ ቤት ውስጥ ልብስ ቀይሮ" ከፖሊስ እጅ እንዳመለጠ ተዘግቧል።

በፍርድ ቤት ቀጠሮ ዕለት ከፍርድ ቤት ማምለጡ በርካቶችን ያነጋገረ እና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለፍርድ እንዲቀርብ ንቅናቄ የሚያደርጉ የመብት ተሟጋቾችን ያስቆጣ ነበር።

ኪዳኔ ከእስር ቢያመልጥም ፍርድ ቤቱ በሌለበት የእድሜ ልክ እስራት ፈርዶበታል። ኪዳኔ አሁን የት እንዳለ በትክክል አይታወቅም።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BBC-10-20-2

Photo Credit : POLITIE NEDERLAND

@tikvahethiopia