#Baro : በባሮ ወንዝ ላይ በጊዜያዊነት ተገንብቶ ለትራፊክ ክፍት የሆነው ድልድይ በመበላሸቱ መቸገራቸውን የኑዌር ዞን ነዋሪዎች ለጋምቤላ ክልል ፕ/ሴ አሳውቀዋል።
25 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበት የተገነባው ድልድይ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ከላሬ ኝንኛንግ በመገንባት ላይ ያለው የ34 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ አካል ሲሆን ድልድዩ 180 ሜትር ርዝመትና 6 ሜትር ስፋት አለው፡፡
ተገጣጣሚ ድልድዩ ዋናው ድልድይ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ በጊዜያዊነት አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ቢሰራም የባሮ ወንዝ ከመጠን በላይ በመሙላቱ ምክንያት አንድ አመት ሳያገለግል ለብልሽት ተዳርጓል፡፡
በዚህም ምክንያት ነዋሪዎች ለተለያየ እንግልት እየተዳረጉ ይገኛሉ።
በተለይ ነፍሰ ጡር እናቶችና አዛውንቶች ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ ሲሆን ተሸከርካሪ ባለማሳለፉ ምክንያት ረጅም መንገድ በእግር ለመሄድ እንደተገደዱ ናቸው።
ብልሽቱ በአጭር ጊዜ ተስተካክሎ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ነዋሪዎች ጠይቀዋል፡፡
የጂካዎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቾር ዎር፥ ተገጣጣሚ ድልድዩ ሲገነባ ትናንሽ መኪናዎችን ብቻ እንዲያሳልፍ ተብሎ የተሰራ ቢሆንም አልፎ አልፎ ከባድ ጭነት የያዙ ተሸከርካሪዎች ሲያልፉበት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
የድልድዩን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የልዩ ሀይል አባላትን በመመደብ ተገቢውን ጥበቃ እያከናወኑ ቢሆንም በድልድዩ ጫፍ ላይ በደረሰ የአፈር መንሸራተት አገልግሎት እየሰጠ እንዳልሆነ ገልፀዋል።
የክልሉ ገጠር መንገዶች ባለስልጣና ዋና ዳይሬክተር አቶ ጋትሉዋክ ዎል በበኩላቸው፥ ድልድዩ በኑዌር ዞን የሚገኙ ወረዳዎችን በቀላሉ ለማገናኘት ፋይዳው የጎላ እንደነበር ጠቅሰው ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰሩ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
@tikvahethiopia