TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
July 14, 2021
"... የፌዴራል መንግስት በልዩ ሁኔታ ካለው መጠባበቂያ በጀት ላይ ክልሉን እንዲያግዝ ጠይቀናል" - ዶ/ር ጥላሁን መሃሪ

የአማራ ክልል መንግስት ከፍተኛ የበጀት ጫና ውስጥ እንደሚገኝ የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮው ይህን ያሳወቀው ለሸገር ሬድዮ በሰጠው ቃል ነው።

ፌዴራል መንግስት ለክልሉ በሚደለድለው በጀት ውዝግብ ውስጥ እንደነበረ ያሳታወሰው ቢሮው በክልሉ ያጋጠመው ወቅታዊ ሁኔታ ተጨምሮ ችግሩ መበርታቱን ገልጿል።

የእንደ አማራ ክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ መረጃ ዘንድሮ በጀት ሰማንያ ቢሊዬን አንድ መቶ አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺ ሶስት መቶ ዘጠና ሰባት ብር ነው።

የክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጥላሁን መሃሪ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጡት ቃል በበጀት ዙሪያ ያለውን ቅሬታ እንደሚከተለው አብራርተዋል ፦

" መጀመሪያ በ1999 ዓ/ም የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ተደርጎ መረጃ ሲወጣ ብዙ ክርክር የተደረገበት፣ ውዝግብም የነበረበት እንደሆነ ይታወቃል። 

በወቅቱ የአማራ ህዝብ አመታዊ የእድገት ምጣኔ 1.7 ፐርሰንት ተብሎ ነበር የተሰላው፤ ይህም ከሁሉም የሀገሪቱ ክልል #የመጨረሻው ነው።

ይህ ግን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሲተያይ ብዙ አሳማኝ ያልሆኑ ነገሮች እንዳሉ ያመላክታል።

የአማራ ክልል ህዝብ ከሌላው ክልል ህዝብ የተለየ ባህሪ የለውም፤ የተለየ የእድገት ምጣኔ ሊኖረው የሚችልበት አሳማኝ ምክንያት የለውም። 

ይሄ እንደገና መታየት አለበት በትክክል አልተሰራም ፣ ስህተቶች አሉ የሚል ቅሬታ ነበር በወቅቱ ፤ ይህን መሰረት ተደርጎ ኢንተርሴንሳል ሳምፕሊንግ መንገድ ተጠቅመው እንደገና የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ይደረጋል በየክልሎቹ 2004 ዓ/ም 2005 ዓ/ም ይመስኛል ድጋሚ ቆጠራ ተደርጎ ሳምፕል ተወስዶ የእድገት ምጣኔው ወደ 2.34 ፐርሰንት አድጓል በሚል ማሻሻያ ተደርጎ ቀርቧል።

በዛ ፐርሰንት ካደገ ከታች ጀምሮ 1999 ፣ 1998 ዓ/ም የነበረው ቤዙ በዛ ደረጃ ቢያንስ ሙሉ ይቆጠር የሚለውን ትተትን በዛ ብቻ መስተካከል ነበረበት ያ ስላልተስተካከለ አጠቃላይ ክልሉ ለበጀት ክፍፍል ታሳቢ የሚደረግበት የህዝብ ቁጥር እንዲያንስ ተደርጓል ፤ ብዙ የበጀት ማከፋፈያ ቀመሩ ላይ የተካተቱት ብዙ ፓራሜትሮች ደግሞ የህዝብ ቁጥርን መሰረት ያደረጉ ናቸው "

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Sheger-FM-10-21-2
October 21, 2021
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ዛሬ በሳዑዲ አረቢያ አካባቢ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ዕለት እንደሚውል ተገልጿል። Via Haramain @tikvahethiopia
April 8, 2024