TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Menz_lalo : በስንዴና በባቄላ ላይ የሰብል በሽታ ተከሰተ።

በመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ በስምንቱም ቀበሌ በስንዴ ላይ ዋግና ባቄላ ላይ ቆርምድ ፣ቸኮሌት ስፖት መከሰቱን የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ፅ/ቤት ገለፀ።

በሽታው የተከሰተው በብዛት በስንዴ ላይ ሲሆን 26.3 ሄክታር መሬት የዋግ በሽታ የተከሰተ ሲሆን የመከላከል ስራ 15.3 ሄክታር መሬት ላይ መሰራቱ ተገልጿል።

ባቄላ ላይ የተከሰተ ቸኮሌት ስፖት 17.5 ሄክታር ፣ ቆርምድ 207 ሄክታር መሬት ላይ መከሰቱ ተጠቁሟል።

አርሶ አደሮች በሽታው ከመከሰቱ አስቀድሞ ማሳቸውን በመከታተል የሰብል ደህንነቱን መጠበቅ አለባቸው ተብሏል።

በሽታው የተከሰተባቸው ማሳዎች በኬሚካል ርጭት እና በባህላዊ መድሃኒት በመጠቀም የሰብል ደህንነት እንዲጠበቅ ለማድረግ አርሶ አደሩ ከባለሙያ የሚሰጠውን ሙያዊ ድጋፍ በመቀበል መስራት እንዳለባቸው የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ፅ/ቤት መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በምዕራብ ምዕራብ ሪጅን የ4G LTE አገልግሎት ጀመረ። ዛሬ በአሶሳ ከተማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ በተገኙበት የምዕራብ ምዕራብ ሪጅን 4G LTE አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ተካሂዷል። አገልግሎቱ በምዕራብ ምዕራብ ሪጅን የሚገኙ ፦ - ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አካባቢ ፣ ጉባ - በመተከል ዞን ፥ ግልገል በለስ - አሶሳ እና ባምባሲ ከተሞች ተጠቃሚ ያደርጋል።…
ኢትዮ-ቴሌኮም በ22 ከተሞች የ4G LTE አድቫንስድ አገልግሎት አስጀመረ።

ኢትዮ-ቴሌኮም በ2ኛ ዙር ማስፋፊያ ስራው በ22 ከተሞች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4G LTE አድቫንስድ የኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል።

ከጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ኩባንያው ፦
- ደደር፣
- ዱብቲ፣
- ደባርቅ፣
- እስቴ፣
- ሸሃዲ፣
- ወረታ፣
- ጃዊ፣
- አዴት፣
- ቢቸና፣
- ደጀን፣
- ሞጣ፣
- አሰላ፣
- ጎባ፣
- ሮቤ፣
- ሶደሬ፣
- ባቱ፣
- ሃላባ፣
- ዱራሜ፣
- ኮንሶ፣
- ሳውላ፣
- ሺንሺቾ፣ እና ወራቤ የ4G LTE አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ቀደም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በሆኑት የደሴ ፣ ደብረ-ታቦር ፣ ጎንደር ፣ ባህር-ዳር፣ ደብረ-ማርቆስ ፣ ሎጊያ ፣ ሆሳህና፣ ሶዶ፣ አርባ-ምንጭ እና ቡታጅራ ከተሞች ተጨማሪ የማስፋፊያ ስራ ተከናውኖ ተግባራዊ መደረጉም ተገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ፥ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ 112 ከተሞችን የ4G LTE አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን እንደገለፀ ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : በጉለሌ ክ/ከተማ 1ዐዐ ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለ የወረዳ አስተዳደር የስራ ሃላፊ ከነኤግዚቢቱ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን የአ/አ ፖሊስ አስታወቀ።

የግል ተበዳይ በሽሮ ሜዳ ገበያ በባህል አልባሳት ንግድ ስራ ተደራጅቶ እየሰራ የሚገኝ ግለሰብ ነው፡፡

ወደ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ጉዳይ ለማስፈፀም በሄደበት አጋጣሚ በአስተዳደሩ የስራ ሃላፊነት ላይ የተመደበ ግለሰብ አግኝቶት እንኳን ደህና መጣህ ስፈልግህ ነው ያገኘሁህ ካለው በኋላ የምትሰራበት የንግድ ሱቅ ፈቃድ የሌለው ስለሆነ 100 ሺ ብር ካላመጣህ እናሽገዋለን በማለት ጉቦ እንደጠየቀው በምርመራ መረጋገጡን የአ/አ ፖሊስ ገልጿል፡፡

በወረዳው በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅቶ ፈቃድ ተሰጥቶት እየሰራ የሚገኘው እና የእኛ የስራ ክፍል ካልፈቀደ መስራት አትችልም ተብሎ ጉቦ እንዲሰጥ የተጠየቀው የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለክ/ከተማው ፖሊስ መምሪያ በማሳወቅ እና በመነጋገር ተጠርጣሪው የስራ ሃላፊ ጥቅምት 2/ 2014 በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 መነን ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 100 ሺ ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ እንዲያዝ ተደርጓል።

ምርመራውም እየተጣራበት እንደሚገኝና በዚሁ ወንጀል ተሳትፎ አለው ተብሎ የተጠረጠረ ሌላ የስራ ሃላፊን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ እንደሆነ የጉለሌ ክ/ተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል ምርመራ ክፍል ገልጿል።

ፖሊስ ፥ አንዳንድ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም ህዝብ በነፃ ማግኘት ያለበትን አገልግሎት በገንዘብ እየሸጡ እንደሚገኙ በመጥቀስ ህብረተሰቡ ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ መንግሥት እርምጃ እንደሚወስድ በመገንዘብ ጥቆማ የመስጠት ልምዱን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 37 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 37 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,382 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 929 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 708 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ስንት ሰው ሲሞት፣ ስንት ሰው ሲያልቅ ነው የዓለም ማህበረሰብ ወለጋ ላይ ሰው እያለቀ ነው ብሎ ድምፁን የሚያሰማው ? " - የምስራቅ ወለጋ [ሀሮ አዲስ ዓለም] ነዋሪዎች በምስቅራ ወለጋ [ሀሮ አዲስ ዓለም] በሸኔ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ ሰዎች እየተገደሉ መሆኑን ነዋሪዎች ገልፀዋል። በምስራቅ ወለጋ ባሉ ወረዳዎች እየተፈፀመ ባለው ጥቃት የትኛውም ኃይል ሊከላከልላቸው እንዳልገባ የሚናገሩት ነዋሪዎች…
#EastWollega : በኪራሙ ወረዳ ሀሮ ቀበሌ ባለፉት ተከታታይ ቀናት በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፣ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ተፈናቅለውም ተሰደዋል።

ይህ እየሆነ ያለው በአካባቢው በታጣቂዎች እየተፈፀመ ባለ ጥቃት መሆኑን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪው በሰሞኑ ጥቃት ኃይለኛ እልቂት መድረሱን ተናግረው ፤ ነዋሪዎች ንብረታቸው ተዘርፎ ወደ ኪረሙ፣ ወደ ጊዳ ፣ ነቀምት መሰደዳቸው ጠቁመዋል፤ ችግሩን የሚያበርድም አካል አልተገኘም ብለዋል።

የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በሰጡት ቃል ፥ በህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው "ሸኔ" ከህወሓት ጋር አንድ መሆኑን ካወጀ ለኃላ የብሄር ግጭት ለማስነሳት የተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት እየፈፀመ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

"ሸኔ" ባለፉት 3 ቀናትም ኪረሙ ወረዳ ላይ ጥቃት መፈፀሙን እና ንፁሃን መገደላቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪ ከሌላ አካባቢ የመጣ ሳይሆን ፤ በዛው አካባቢ የሚንቀሳቀስ የ "ሸኔ" ተፃራሪ "ፅንፈኛ" ቡድን አለ ያሉ ሲሆን የሚሰራው ድርጊት ከ "ሸኔ" ጋር ይጋራል አብሮ የሚኖረውን ማህበረሰብ ለይቶ በማጥቃት የፖለቲካ አጀንዳ ለማግኘት የሚንቀሳቀስ የ "ሽፍታ" ቡድን ነው ብለዋል።

ኃላፊው #ለኢቲቪ በሰጡት ቃል ደግሞ ይህ የ "ሸፈተ" ቡድን ያሉት ኃይል የአማርኛ ተናጋሪ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ሁለቱ አካላት ናቸው በንፁሃን ላይ ጥቃት ያደረሱት የሚሉት አቶ ኃይሉ ፥ ከሰሞኑ በነበረው ጥቃት 15 ሰዎች መገደላቸውን አሳውቀዋል፤ ድርጊቱ የብሄር ግጭት ለመቀስቀስ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

" የሰሞኑን ጥቃት ማንነት መሰረት አድርጎ ተፈፀመ የሚለውም ሊስተካከል ይገባል " ሲሉም የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ ኃይሉ አዱኛ ሲናግሩ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ዛሬ ምሽት " አሳሳቢነቱ የቀጠለው የአገራችን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ " በሚል አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኮትዲቯር፣ የጋቦን ፣ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና የቡርኪፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ የሚገኙት ነገ በሚጀመረው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ ለመታደም ነው። በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የሕብረቱ 55 አባል አገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች…
#Update

39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የሕብረቱ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ተወካዮች ተገኝተዋል።

ሚኒስትሮች በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ ትናትንና ከትናንት በስቲያ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

የምክር ቤቱ ስብሰባ የአገራት መሪዎች፣ የአፍሪካ ሕብረት ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማኀበረሰብ ተቋማትና በሕብረቱ ስር የሚገኙ ተቋማት የሚያደርጉት በሶስተኛው አጋማሽ ዓመት ለሚያደርጉት ጥምር ውይይት አጀንዳዎች የሚቀርቡበት ነው።

በዚሁ መሰረት 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ የሚመክር ይሆናል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : 8ኛው አለም አቀፉ የቴሌኮም ልማት ኮንፈረንስ ከግንቦት 27/2014 ጀምሮ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ከ2 ሺ በላይ እንግዶች የሚስተናገዱበት ኮንፈረንስ በስኬት እንዲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ዝግጅት እያደረገች ነው።

በዝግጅቱ ዙሪያ የአለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት ተወካዮች ከቴሌኮም ልማት ኮንፈረንሱ አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጋር በአዲስ አበባ እየተወያዩ ይገኛሉ።

የኮንፈረንሱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ባልቻ ሬባ (ኢንጂ.) ኮንፈረንሱን እውነተኛ የአፍሪካ መድረክ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል።

ጉባኤው ኢትዮጵያ ራሷን ለአለም የምታስተዋውቅበት መድረክ ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው ለጉባኤው ስኬትም ሁሉም ርብርብ እንዲያደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

Credit : የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#Amhara : 1.5 ሚሊዮን ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ የሉም።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል በህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት ፦
- በሰሜን ወሎ
- በሰሜን ጎንደር
- በዋግኽምራ
- ከፊል ደቡብ ወሎ
- ከፊል ደቡብ ጎንደር በከፈተው ጦርነት እና ወረራ ሳቢያ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀዋል።

በተጨማሪ በጦርነቱ ምክንያት 277 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደሙን፤ ከ1 ሺህ 300 በላይ በከፊል ተጎድተዋል (የትምህርት ቁሳቁሶች ተሰርቋል፣ ወድሟል፣ ቁሳቁሶች ከጥቅም ውጭ ሆኗል) ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ተፈናቅለው በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት እንዲቀጥሉ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ አመቻቻለሁ ብሏል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ጌታቸው ፤ ተፈናቅለው የሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃቸውን ይዘው ባለመምጣታቸው ምክንያት ባሉበት አካባቢ ሁሉ በሚፈልጉበት ትምህርት ቤት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመዘገቡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል የምስራቅ ጎጃም ዞን ባለፈው ወር 10 ሺ ተፈናቃይ ተማሪዎችን የምግብ ወጪያቸውን ጨምሮ ለመቀበል ባደረገው ጥሪ እስካሁን 235 ተማሪዎች መመዝገቡን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ለቪኦኤ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : አዲስ አበባ ከያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ ተማሪዎቿን ወደ ትምህርት ቤት ጠርታለች።

በዚህ ምክንያት በክረምቱ ወቅት የነበረው የትራንስፖርት ፍሰት ይበልጥ ተጨናንቆ እና የታክሲ እጥረት ተስተውሎ ተገልጋዮችን ወደ ማጉላላት እየደረሰ ነው።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለዚህ ወቅታዊ የትራንስፖርት እጥረት በምክንያትነት ካነሳው ጉዳይ አንዱ ከተሰጣቸው ፍቃድ ውጪ ለተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ባለታክሲዎች መበራከታቸው እንደሆነ ገልጿል። እየሰጡ ያሉትን አገልግሎትም ወዲያው እንዲያቆሙ አስጠንቅቋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ በ @tikvahethmagazine ሀሳባቸውን ያካፈሉን በርካታ የቲክቫህ ቤተሰቦች የአዲስ አበባ ትራንስፓርት ቢሮን ዉሳኔ የተሳሳተና ፍታዊነት የጎደለዉ ሲሉ ገልጸውታል።

''ዛሬ አይደለም የተጀመረዉ የተማሪ ሰርቪስ ጥንትም የነበረ ነዉ። ይህ ዉሳኔ ቀላሉን ችግር በከባድ ችግር መተካት ማለት ነዉ።'' ሲሉም ነው የገለጹት።

''እንዲህ እንደዛሬው ያለ ከፋተኛ የህዝብ ጥቅም የሚነካ ጉዳይ ላይ የሚሰጥ ውሳኔ ከፋተኛ ጥንቃቄ ይጠየቃል።'' ሲሉ ውሳኔውን ነባራዊ ሁኔታውን ያላገናዘበ ነው ሲሉ በውይይቱ ጠቅሰዋል።

ይህንኑ ጉዳይ ይዘን ወደ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጥያቄዎችን አቅርበናል።

የቢሮው የኮሚውኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ይመሩ ባለፉት ቀናት የትራንስፖርት ፍሰቱ መጨናነቅ ተከትሎ ቢሯቸው ቅኝት ማድረጉን የገለጹ ሲሆን በዚህም ቁጥራቸው በርካታ የትራንስፖርት ሰጪ መኪኖች(ታክሲ) ወደ ሰርቪስነት መቀየራቸውና ይህም ከህግ ውጪ በመሆኑ ከፍተኛ ችግርም በመፍጠሩ የተወሰነ ውሳኔ መሆኑን አስረድተዋል።

ያንብቡ 👉 https://telegra.ph/Addis-Ababa-10-14

Tikvah-Magazine : t.iss.one/joinchat/Rx7P5YHQp_G16wyX
#NBE : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለተለያየ የቢዝነስ ዘርፎች ባንኮች ይሰጡ የነበረውን ብድር ላልተወሰነ ጊዜ እንዲያቆሙ የተላለፈው መመርያ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ከ4 ሳምንታት በላይ አስቆጥሯል፡፡

ባንኮች በዚህ መመርያ መሠረት የተፈቀዱ ብድሮች ሳይቀሩ እንዳይለቀቁ ተደርገው ቆይተዋል፡፡

በዚህ መመርያ መሠረት የተለያዩ ቢዝነሶች ከባንክ ሊያገኙ የሚችሉትን ብድር ባለማግኘታቸው በሥራዎቻቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል።

የማይንቀሳቀስ ንብረት አስይዞ መበደር እንደማይችል ጭምር የሚደነግገው ይህ መመርያ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ግን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ‹‹ብድር ሊለቀቅላቸው ይገባል›› ያላቸውን የቢዝነስ ዘርፎችና ሁኔታዎች እየፈተሸ፣ ባንኮች ብድር መስጠት እንዲችሉ በተከታታይ እያስታወቀ ነው፡፡

ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ምርት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ኩባንያዎች የተቋረጠው የብድር አቅርቦት እንዲለቀቅላቸው ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰኞ ዕለት ለባንኮች ባስተላለፈው መልዕክት መሠረት በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ በማምረትና ለውጭ ገበያ በማቅረብ ላይ ለሚገኙ ኢንቨስተሮች ብድር መስጠት የሚችሉ በመሆኑ፣ በዚሁ መሠረት ደንበኞቻቸውን ማስተናገድ እንደሚችሉ አሳውቋቸዋል፡፡

የአበባ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ኢንቨስተሮች ብድር እንዲሰጥ የተፈቀደበት አንዱ ምክንያት፣ በአብዛኛው ሥራቸው ከባንክ ብድር ጋር የተገናኘ በመሆኑ፣ ብድር እንዲቋረጥ መደረጉ ሥራዎቻቸው ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል በሚል የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማኅበር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቤቱታ በማቅረቡ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Credit : ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#Dejen : 15 ቀን የሆነውን ህፃን ሽንት ቤት የከተተችዉ ግለሰብ በቁጥጥር ዋለች።

ድርጊቱ በደጀን ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ቦታዉ ቀጠና 5 እየተባለ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ ነው ተፈፀመው።

ተጠርጣሪ ለምለም ዋለ የተባለችዉ አድራሻዋ ወረጃርሶ ወረዳ ፍልቅልቅ 01 ቀበሌ ነዋሪ የሆነችዉ ግለሰብ ከተወለደ 15 ቀን የሆነዉን ህጻን ጥቅምት 3 ቀን 2014 ዓ/ም ከንጋቱ በግምት 12 ሰዓት ሲሆን ሽንት ቤት ዉስጥ ከታዉ ትሰወራለች።

የቤቱ ባለቤት ከመኝታ ተነስታ ሽንት ቤት ስትጠቀም ከሽንት ቤቱ ዉስጥ ህጻኑ ሲያለቅስ ስትሰማ የድረሱልኝ ጩኸት በማሰማቷ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ህጻኑን ከሽንት ቤት አዉጥቶ ለፖሊስ ሪፖርት አድርጓል።

የደጀን ከተማ ፖሊስ ወደ ቦታዉ ሄዶ ህጻኑን ደጀን ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ እንዲደረግለታ ያደረገ ሲሆን ፖሊስ አጥፊዋን ተከታትሎ በመያዝ ምርመራዉ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

መረጃው ከደጀን ከተማ ፖሊስ/የደጀን ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikavhethiopia