TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ERCS

• የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የአምቡላንስ ሹፌር በታጣቂዎች ተገደለ።

• ማኅበሩ በባልደረባው ሞት የጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው ገልጾ ግድያውን አውግዟል። ታጣቂ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ማህበሩ ተማፅኗል።


የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ #የአምቡላስ_ሾፌር የነበረው አቶ መንግስት ምንይል ታጣቂ ሃይሎች በፈፀሙት ጥቃት ተገድለዋል።

ማህበሩ፤ ግድያውን በአፅንዖት አውግዟል።

አቶ መንግስት ምኒል በምዕራብ ደንቢያ ሰብዓዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረና በሰብዓዊ ህይወት የማዳን ስራ ወልቃይት አዲ ረመፅ ሆስፒታል ተመድቦ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነበር።

አቶ መንግስት አድዋ፣ ትግራይ ተሰማርተው በግጭት የተጎዱ ወገኖችን በማገዝ ላይ ከነበሩ 2 አምቡላንሶች አንዱን በማሽከርከር ከአድዋ ወደ ወልቃይት አዲ ረመፅ ሆስፒታል ቁስለኞችን ለማድረስ በተንቀሳቀሰበት ወቅት ቁስለኞቹን ጨምሮ በታጣቂ ሃይሎች በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸውን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ገልጿል።

የአምቡላንስ ሹፌሩ አቶ መንግስት ምኒል የ40 ዓመት ጎልማሳ እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበር።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ አምቡላንስ በማሽከርከር ሰብኣዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ በነበረው  ባደረባው ግድያ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

በመላ ሀገሪቱ በሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የቀይ መስቀል ማኅበር  ሠራተኞችና በጎ ፈቃደኞችን ሰብዓዊ ተግባራቸውን በገለልተኝነት እና በአለማዳላት መንፈስ በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ እንዲሁም ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ታጣቂ ሃይሎች ከእንደዚህ አይነት ጥቃት እንዲቆጠቡ ተማፅኗል።

@tikvahethiopia