TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሎዳ⬆️

"ሰላም ጸግሽ! ዛሬ በዜይሴ/ኤ/ሎዳ የተደረገው ስብሰባ በሰላም ተጠናቋል። ስብሰባውም የተደረገው ልዩ ወረዳ ይስጠን በሚል ላይ ነው። ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ እናካሂዳለን፤ እስከመጨረሻውም ድረስ የምወሰደውን መስዋእትነትም እንከፍላለን ብሏል የሎዳ ቀበለ ሊቀመንበር አቶ አየለ ክሎ። እናም ጥያቄያችንን ምንም አይነት #ሁከትም ሆነ #ብጥብጥ ሳንፈጥር እስከመጨረሻው እንዘልቃለን ስል መልእክቱንም አስተላልፏል። እናም በልዩ ወረዳ መደረግ ዙሪያ ያልሆነ ነገር አርባምንጭ ላይ እንደሰሩም አንዳንድ የጠየኳቸው ግለሰቦች ነግረውኛል እሱም በንግግሩ መካከል ስያነሳ ሰምቸዋለሁ። ሰፋ ያለ ገለጻ አጠያይቄ እነግርሃለሁ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
❗️ዛሬ እንጂ የዛኔ ምርጫ የላችሁም❗️

እናንተ ግጭትን ለማብረድ ከመሞከር ይልቅ በተነሳው እሳት ላይ ቤንዚን እየጨመራችሁ ያላችሁ ግብዞች ሆይ!!

ይህ እውነት የተፃፈው ለእናንተ ነው፡፡ በዚህ ርኩሰት ተግባር ከቀጠላችሁ…

እንዲመጣ እየወተወታችሁት ያላችሁት ክፉ ቀን ቢመጣ እንዲህ እንዳሁኑ ፌስቡክ ላይ ተጥዳችሁ #መዘብዘብ አይታሰብም። ያኔ ምኞታችሁ ዛሬን በህይወት መክረም ብቻ ይሆናል።

ያኔ አይደለም እንደልባችሁ #ወጥታችሁ መግባት ይቅርና ሱቅ ደርሶ መመለስ ቅንጦት ሊሆንባችሁ ይችላል፡፡ ምክንያቱም እንዲነድ ያቀጣጠላችሁት እሳት ወላፈን. .. ከቤታችሁ ወጣ እንዳላችሁ ሊበላችሁ ይችላል። ለነገሩ እያቀጣጠላችሁት ያለው እሳት.....ከቤታችሁም ሆናችሁ ከሰል አድርጎ ሊያስቀራችሁ ይችላል።

ያኔ ሀገሪቱ በትናንሽ ባለጠመንጃ መንግስታት የምትመራ ስለምትሆን እንደልብ የምትተቹት መንግስት አይኖራችሁም። ይህ ነገር አሁን አይገባችሁም።

እናንተን ምናልባት የሚገባችሁ…⬇️

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት በመድሃኒትና በምግብ እጦት #ሲያልቁ ያዩ እናቶች... ልጆቻቸውን ለማትረፍ ወደ ስደት በሚያደርጉት ጉዞ የአውሬና የሽፍታ ሲሳይ ሆነው ሲቀሩ ያኔ ይገባችኋል።

አስፓልቶች በታንክ ታርሰው..... ከተማይቱ በህንፃ ፍርስራሽ ተሞልታ በዘሩ ምክንያት በየቀኑ በየጎዳናው የሞተው ቀባሪ ያጣ አስከሬን ሽታው አገሩን ሲሞላው ያኔ ይገባችሁ ይሆናል።

እመኑኝ ....ዛሬ ላይ ለተፋችኋት እያንዳንዷ #ብጥብጥ ቀስቃሽ መልእክታችሁ መፈጠራችሁን #እስክትረግሙ ዋጋ ትከፍልባታላችሁ። ለኃጥዓን የወረደው ለፃድቃን ይተርፋል እንደሚለው ቅዱስ መፅሃፉ ዳፋችሁ ለሁሉም ሲሆን ያኔ ይገባችሁ ይሆናል ።

ያ እንዲመጣ የምትፈልጉት ቀን ሲመጣ. .. #ክልላችሁ ወይም #ከተማችሁ አያድናችሁም። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የላካቸው ሰላም አስከባሪ #ወታደሮችም ከመጣባችሁ መዓት ፈፅሞ ሊያስጥሏችሁ አይችሉም ።

ምናለፋችሁ ዛሬ እንደዋዛ #እያቀጣጠላችሁት ያላችሁት እሳት ለጎረቤት ሃገራትም ይተርፋልና ክልሌ መሸሸጊያዬ ብላችሁ #እንዳታስቡ

ዛሬ በሀገር ሰላም በድንገት በህዝቦች መካከል የተፈጠሩ ግጭቶችን ላጋጋላችሁበት አንድ ቀን #በቁጭት እና #ፀፀት የደም እምባ እያነባችሁ በህይወታችሁ ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ፡፡

አሁን እንጂ የዛኔ ምርጫ የላችሁም፡፡ ስለዚህ ያች እንድትመጣ እየጠራችኋት ያለችው ቀን ሳትመጣ፣ በዚች በመልካሟ በዛሬዋ ቀን ላይ ሳላችሁ ምርጫ አላችሁና አስቡበት።

ልቦና ይስጠን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ጠብቅልን!

©ቂርቆስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባይደዋ‼️

በሶማሊያዋ ባይደዋ ከተማ ለሁለተኛ ቀን #ብጥብጥ እንደቀጠለ እማኞች ገለፁ። የብጥብጡ መንስኤ በትናንትናው ዕለት የቀድሞ የአሸባብ መሪ እና የአሁኑ ፕሬዝደንታዊ እጩ ሙክታር ሮቦው በወታደሮች በቁጥጥር ሥር መዋሉ ነው። ዛሬ የሮቦው ደጋፊዎች ከፀጥታ ኃይላት ጋር ተጋጭተዋል፤ 11 ሰዎችም ተገድለዋል። DW ያነጋገረው አንድ ሶማሊያዊ ጋዜጠኛ ሮቦውን የተያዘው በኢትዮጵያውያን ወታደሮች መሆኑን ገልጿል። እንደ ጋዜጠኛው ቀደም ሲል የሶማሊያ መንግሥት በተለይም የፀጥታ ኃይሉ ሮቦው ለምርጫ መቅረቡን ተቃውሞ ነበር።

ምንጭ፦ DW የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል‼️

መንግስት የጦር መሳሪያ ሊያስፈታ ነው የሚለው ቅስቀሳ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በምዕራብ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች አንፃራ ሰላም መስፈኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው በሁለቱ ዞኖች አንፃራዊ ሰላም መታየቱን ያስታወቀው፡፡ በአካባቢው የነበረውን #አለመረጋጋት ወደ #ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልከላ እና ሌሎች እገዳዎች ከተላለፉበት ቀን ጀምሮ በሰውም ይሁን በንብረት ላይ ይደርስ የነበረው ጉዳት መቀነሱን ገልፃል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም እንደጠቆሙት የፌደራል እና የክልል የፀጥታ ሀይሎች ከህብረተሰቡ ጋር እየሰሩት ባለው ተግባር በቡድን ሲፈፀሙ የነበሩ የግድያ እና የንብረት ማጥፋት ወንጀሎች ቀንሰዋል፡፡

ከእገዳው በኋላ በጥምረት በተሰራው ስራም 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል። አሁንም አልፎ አልፎ በግለሰብ ደረጃ የሚፈፀሙ ወንጀሎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።
ከአሁን ቀደም ታግተው የነበሩ ግለሰቦችም ሙሉ በሙሉ መለቀቃቻን ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል፡፡

ከጎንደር መተማም ይሁን ከጎንደር ሁመራ የተሽከርካሪ መጓጓዣ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ በጎንደር ከተማ ከአሁን ቀደም የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር ያሉት ኮሚሽነር ዘላለም እገዳው ከተደረገ ወዲህ መቀነሱን አመላክተዋል፡፡

ይህ ደግሞ የፀጥታ ሀይሉ ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ ሆኖ በመስራቱ የመጣ ነው፤ የጎንደር ከተማ ወጣቶች ለሰላም እያሳዩ ያሉት ትብብርም የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

ወንድማማች ህዝቦቹ ካለፈው ጥፋት ተምረው በጋራ ችግሮቻቸውን ለመቅረፍ እየተወያዩ መሆናቸውም ታውቋል።

እገዳ በተደረገባቸው አካባቢዎች የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ መከልከሉን ምክንያት አድርገው መንግስት የጦር መሳርያ #ሊያስፈታ ነው እያሉ ቅስቀሳ የሚያደርጉ አካላት አሉ፡፡ "ቅስቀሳው ከእውነት የራቀ ነው፤ #ብጥብጥ በመፍጠር ክልሉን ለማዳከም የታለመ ሀሳብ በመሆኑ ማህበረሰቡ በአሉባልታዎች እንዳይታለል" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia