TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ⬇️

በድሬደዋ አስተዳደር ባሳለፍናቸው ጥቂት ቀናት በከተማው ግጭቶችና ሁከቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችና የተለያዮ የህ/ብ ክፍሎች #የስጋት ሀሳቦች መመንጨታቸውን ተከትሎ ፖሊስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠቱ የሚታወቅ ነው::

ይህንንም ተከትሎ ፖሊስ ሌሎች የፀጥታ ሀይሎችና መላው ህብረተሰብ ባከናወናቸው ተግባራት ስጋቶቹን #እያመከነ በከተማው አሁን ላይ ያለው አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዲገኝ ያደረገ ሲሆን ይህው የፀጥታ ሀይልና ህብረተሰብም ይህንኑ ሰላምና ፀጥታ አጠናክሮና የበለጠ አስጠብቆ በማስቀጠል ላይም ይገኛል። በዚህም ፖሊስ ለመላው የአስተዳደሩ ነዋሪና ወጣቶች ምስጋናውንም ያቀርባል።

ይህ ይሁን እንጂ ከፀጥታ ማስፈንና የህግ የበላይነት ከማረጋገጥ ተግባር ጋር ተያይዞ እያጋጠሙ ያሉና ሊታረሙ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉም ልብ ሊባል ይገባል።

በመሆኑም አሁን ላይ ያለውን ሰላምና ፀጥታ ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የተጀመሩ የለውጥ ሂደቶች ለማስቀጠል ብሎም የትርምስና የብጥብጥ አላማ ያላቸውን ሀይሎች ከምንጫቸው ለማድረቅና እኩይ ተግባራቸውን ለማምከን ትኩረት መስጠትና ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፖሊስ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ክልከላ የተደረገ መሆኑን ያሳውቃል።

1ኛ:- ለፖሊስና ለፀጥታ ሀይሉ አሳዉቆ ተገቢውን ባጅና መለያ ሳያደርጉና ሳይዙ በቡድን ተደራጅቶ የጥበቃ እገዛ ሰጪነን ብሎ መንቀሳቀስ

2ኛ:-በተናጥልም ይሁን በቡድን የስለት መሳሪያዎችን ይዞ መንቀሳቀስ

3ኛ:-ከአስተዳደሩ የፀጥታ ምክር ቤትና ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኙ ህዝባዊ ስብሰባ ማካሄድ የተከለከለ መሆኑን #በጥብቅ ያሳስባል።

መላው የአስተዳደራችንም ነዋሪ ይህንኑ በመገንዘብና በመረዳት ለሰላሙና ለህግ የበላይነት መረጋገጥ እያደረገ ያለውን አስተዋፆና እያሳየ ያለውን እጅግ ከፍተኝ ትብብርና እገዛውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጨምሮ ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።

መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም
የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ASTU🔝

"...ከሰኞ 24/03/2011 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ትምህርት ገበታችሁ እንድትመለሱ #በጥብቅ እያሳወቅን ይህ ሆኖ ባይገኝ ግን ዩኒቨርሲቲው ህግን እና ስርዓትን ለማስከበር የሚገደድ መሆኑን በአንክሮ እናስገነዝባለን።"
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️

#ሼር #Share

በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ለምትገኙ በሙሉ -- የተከሰተውን #ግጭት ለማርገብ እና ሰላም ለማስከበር የመከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ይሰራል።

አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ #የተከለከሉ ተግባራት፦

• ከጎንደር - መተማ መስመር 5 ኪ.ሜ. ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ #በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በጎንደር ከተማ ከፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው መሳሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• "ሰላም ለማስከበር" በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከኮሚሽኑ ፍቃድ ውጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

#ማንኛውም በፀጥታ መደፍረስ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል #እርምጃ ይወሰድበታል‼️

የሰላም ጥሪ፦

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጎንደር ወጣቶችና አክቲቪስቶች በጎንደር እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንድትሰሩ #መከላከያ_ሰራዊት ጥሪ አቅርቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️

#ሼር #Share

በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ለምትገኙ በሙሉ -- የተከሰተውን #ግጭት ለማርገብ እና ሰላም ለማስከበር የመከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ይሰራል።

አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ #የተከለከሉ ተግባራት፦

• ከጎንደር - መተማ መስመር 5 ኪ.ሜ. ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ #በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በጎንደር ከተማ ከፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው መሳሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• "ሰላም ለማስከበር" በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከኮሚሽኑ ፍቃድ ውጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

#ማንኛውም በፀጥታ መደፍረስ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል #እርምጃ ይወሰድበታል‼️

የሰላም ጥሪ፦

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጎንደር ወጣቶችና አክቲቪስቶች በጎንደር እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንድትሰሩ #መከላከያ_ሰራዊት ጥሪ አቅርቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላማዊ ሰልፍ አልተጠራም‼️

በአዲስ አበባ ከተማ እሁድ የካቲት 17/2011 ዓ/ም #በመስቀል_አደባባይ ሠላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል በሚል በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች የተላለፈው ዘገባ ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት ምንም ዓይነት የሠላማዊ ሰልፍ ሆነ ስብሰባ እናድርግ የሚል #ጥያቄ ያልቀረበለት መሆኑን ለኮሚሽኑ የገለፀ ሲሆን ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው ነው።
በመሆኑም #ሰልፍ_እንወጣለን በሚል በህብረተሰቡ ላይ የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላት ከተግባራቸው እንዲታቀቡ ኮሚሽኑ #በጥብቅ አሳስቧል።

ይህን ተላልፎ በሚገኙ አካላት ላይም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል አስፈላጊውን ህጋዊ #እርምጃ የሚወስድ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል ፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የተሳሳተ_መረጃ

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ETHIO FM የኮሚሽኑ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገልፀዋል በሚል '38 የህውሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል' ሲል ያስተላለፈው መረጃ ሐሰት እና በም/ኮሚሽነር ጀነራሉ ያልተላለፈ መሆኑን አሳወቀ።

ተያዙ በሚል ሃላፊው የገለፁትም በመከላከያ ውስጥ የግንኙነት መስመር ያቋረጡና ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዱን (ወዲ ነጮን) ጨምሮ 38 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው ነው።

በህግ ከሚፈለጉት የህወሓት ቡድን አባላት እስከአሁን የተያዙ አለመኖራቸው ታውቆ ሌሎች ሚዲያዎችም ይህንን "የተዛባ መረጃ" ለህበረተሰቡ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ የፌዴራል ፖሊስ #በጥብቅ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የጥሞና ወቅት ምንድነው ?

የጥሞና ወቅት በቅድመ የምርጫ ዑደት ውስጥ የሚገኝ ጊዜ ሲሆን በኢትዮጵያ የምርጫ ዑደት መመሪያ መሠረት ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉትን 4 ቀናት ያካትታል፡፡

በጥሞና ወቅት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ማለትም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ሊተገብሯቸው የሚገቡ ኃላፊነቶች አሉ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች መተግበር ያለባቸው ፦

• የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም ደጋፊዎቻቸው ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚየካሂዱት የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ ድምጽ መስጠት ከመጀመሩ ከ4 ቀን በፊት መጠናቀቅ አለበት፡፡

• የፓለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው 4 ቀን ሲቀረው ማንኛውም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡ (በኢንተርኔት ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ፣ በግንባር፣ ቤት ለቤት፣ በአደባባይ ፣ በአዳራሽ ስብሰባ ምንም አይነት ቅስቀሳ ማከናወን #በጥብቅ የተከለከለ ነው)

• የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት እንዲሁም ቃለ-መጠይቆችን ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡

• ብሄራዊ የምረጫ ቦርድ የሚያወጣቸውን መመሪዎች ሊፈጽሙ ይገባል፡፡

መገናኛ ብዙሀን ተቋማት መተግበር ያለባቸው ፦

• የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ማንኛውንም ምርጫ ተኮር እንቅስቃሴዎችን ማሰራጨት አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪ የፓለቲካ ፓርቲ እጩዎችን አግኝተው ቃለ መጠይቆችን መስራት አይፈቀድላቸውም፡፡

• የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚወጡ መረጃዎችን የማስተጋባት ሀላፊነት ሲኖርባቸው ከዚህ ውጪ በመመሪያዎች ላይ ያልተደነገጉ ተግባራትን እንዲፈጽሙ አይፈቀድላቸውም፡፡

(የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)

@tikvahethiopia
#UK

አሜሪካ #በጥብቅ የምትፈልገው የ " ዊኪሊክስ " መስራች ጁሊያን አሳንጅ ለአሜሪካ ተላፎ እንዲሰጥ የብሪታኒያ ፍርድ ቤት ዛሬ ወስኗል።

አሳንጅ ለአሜሪካ ፍርድ ቤት ተላልፎ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው የብሪታኒያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ሲያጸድቀው ነው ተብሏል።

አሳንጅ የአሜሪካን ወታደራዊ መረጃዎች አውጥቷል ፤ አትሟል ፤ ወታደራዊ ሚስጥሮችን የያዙ ሰነዶች ለውጭ ኃይሎች አሳለፎ ሰጥቷል በሚል እና በሌሎችም ጉዳዮች ነው አሜሪካ የምትፈልገው።

18 በሚሆኑ ክሶችም ዋና ተፈላጊ ሰው ነው።

የ50 ዓመቱ አሳንጅ በአሜሪካ የቀረበለትን ክስ ውድቅ ቢያደረግም፤ አድርጎታል ከተባለ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለ7 ዓመታት በለንደን በሚገኘው የኢኳዶር ኤምባሲ፤ እንዲሁም እንደፈረንጆቹ ከ2019 አንስቶ አስካሁን ድረስ በደቡብ ምስራቅ ለንደን በሚገኘው ቤልማርሽ እስር ቤት እንዲታሰር አድርጎታል።

መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የዑለማ ጉባዔ የ2ኛ ዓመት መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ጉባኤው በመግለጫው ፦

- በየሳምንቱ የሚደረገው የጁምዓ ኹጥባ አርካኑን በጠበቀ መልኩ በአረብኛ ቋንቋ መሆኑ የተመረጠ ቢሆንም እንደ አስፈላጊነቱ ማህበረሰቡ እንዲረዳው በተለያዩ ቋንቋዎች ቢደርግ ችግር እንደሌለው ጉባኤው መስማማቱ ተገልጿል። በተጨማሪም የቁርአንናና የሐዲስ ጥቅሶች ባሉበት በአረብኛ ቋንቋ ተነበው መተርጎም አለባቸው ብሏል።

- በሸሪአ የተፈቀደው የጋብቻ አይነት በተቃራኒ ጾታዎች ማሃከል የሚደረግ ጋብቻ ብቻ ሲሆን የተፈጥሮ ህግንና ሸሪአን በተፃረረ መልኩ የሚደረገውን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግንኙነት በሸሪዓ በጥብቅ የተከለከለና የአላህን ቁጣ የሚያስከትል ተግባር በመሆኑ ጉባኤው #በጥብቅ_እንደሚያወግዝ አሳውቋል።

- የኢትዮጵያ ዑላማዎች ለሰላም ዘብ እንደሚቆሙ ፤ ህዝበ ሙስሊሙም ለአገር ሠላም ዘብ እንዲቆም ፤ በአገራችን የሚታዩት አለመግባባትና ግጭቶች በሰላማዊ መልኩ በውይይት እንዲፈቱ ለመንግስትና ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ሁሉ ጥሪውን አስተላልፏል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia