TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
' ጋዜጠኛው የት እንዳለ ማወቅ አልተቻለም ' የኢትዮጵያ ኢንሳይደር መስራች እና ጋዜጠኛ የሆነው ተስፋለም ወልደየስ ከትላንት ጀምሮ የት እንዳለ አይታወቅም። ጓደኞቹ እና የስራ ባልደረቦቹ በአዲስ አበባ የነበረውን የሆራ ፊንፌኔ የኢሬቻ በዓል ከዘገበ በኃላ ሊያገኙት እንዳልቻሉ አሳውቀዋል። ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ዛሬ በቢሾፍቱ የተከበረውን የሆራ ሀርሰዲ ኢሬቻ በዓል ለመዘገብ እቅድ እንደነበረውም ገልፀዋል።…
#Update

ጋዜጠኛ ተስፋዓለም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ነው።

የ "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" መስራችና ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ የፌደራል ፖሊስ አሳወቀ።

ፌዴራል ፖሊስ ይህን ያሳሰወቀው ለቢቢሲ ነው።

ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ ከቅዳሜ መስከረም 22/2014 ዓ.ም ረፋድ ጀምሮ ያለበትን እንደማያውቁ የሥራ ባልደረቦቹ እና ጓደኞቹ መናገራቸው ይታወቃል።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ፥ ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ በፌደራል ፖሊስ እጅ ስር እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

ኃላፊው እንደተናገሩት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም በአሁኑ ጊዜ "የፌደራል ፖሊስ የምርመራ ቢሮ የሜክሲኮ ማቆያ እንደሚገኝ" ገልጸው፤ "ምንም የሚፈጠር ነገር የለም። ያለውን ነገር እያጣራን ነው። ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም" ሲሉ ተናግረዋል።

የወንጀል ምርመራ ቢሮ ምክትል ኃላፊው፤ ጋዜጠኛ ተስፋዓለም በምን ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ቢቢሲ ከታማኝ ምንጮቼ ሰማሁኝ እንዳለው ከሆነ ጋዜጠኛ ተስፋዓለም በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ መኖሪያ ቤቱ ላይ ፍተሻ ተካሂዷል።

Credit : BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ታገሰ ጫፎ ለኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት አፈ ጉባኤነት በእጩነት ቀርበዋል። @tikvahethiopia
#Update

አቶ ታገሰ ጫፎ የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ።

አቶ ታገሰ በም/ቤቱ አባላት 419 ድምፅ እና በ6 ድምፀ ታአቅቦ ነው የተመረጡት።

አቶ ታገሰ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ በመሆን ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ወ/ሮ ሎሚ በዶ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው በእጩነት ቀርበዋል። @tikvahethiopia
#Update

ወ/ሮ ሎሚ በዶ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።

በአብላጭ ድምፅ እና በ7 ድመፀ ታአቅቦ ነው የተመረጡት።

ወ/ሮ ሎሚ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

@tikvahethiopia
#Update

ዶ/ር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በእጩነት ቀርበዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በእጩነት አቅርቧል።

እጩውን ያቀረቡት አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው።

@tikvahethiopia
#Update

አቶ አገኘሁ ተሻገር የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ አገኘሁ ተሻገር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት እንደነበሩ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ አገኘሁ ተሻገር የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል። አቶ አገኘሁ ተሻገር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት እንደነበሩ ይታወሳል። @tikvahethiopia
#Update

የአፋር ክልል የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃለፊ የነበሩት ወ/ሮ ዛራ ሁመድ የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ሆነው ተመርጠዋል።

@tikvahethiopia
#Update

የጅቡቲ እና ሶማሊያ መሪዎች ኢትዮጵያ ገቡ።

የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ እንዲሁም የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ኢትዮጵያ፣ (አዲስ አበባ) ገብተዋል።

መሪዎቹ ኢትዮጵያ የገቡት ዛሬ በሚካሄደው የመንግስት ምስረታ ስነስርዓት ላይ ለመታደም ነው።

Photo Credit : ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#Update

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የመክፈቻ ስነ ስርዓት ተጠናቋል።

ኘሬዝዳንት ስህለ ወርቅ ዘውዴ ለሁለቱም ም/ቤቶች የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ከሰዓታት በኃላ ደግሞ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የበዓለ ሲመት ስነስርዓት ይካሄዳል።

@tikvahethiopia
#Update

ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዓሊ በዓለ ሲመታቸው በመስቀል አደባባይ የሚካሄድ ሲሆን ለዚሁ ስነስርዓት በርካታ ነዋሪዎች ወደ መስቀል አደባባይ እያቀኑ መሆኑን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጅቡቲ እና ሶማሊያ መሪዎች ኢትዮጵያ ገቡ። የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ እንዲሁም የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ኢትዮጵያ፣ (አዲስ አበባ) ገብተዋል። መሪዎቹ ኢትዮጵያ የገቡት ዛሬ በሚካሄደው የመንግስት ምስረታ ስነስርዓት ላይ ለመታደም ነው። Photo Credit : ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር @tikvahethiopia
#Update

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልቫኪር ማያርዲት የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

በተጨማሪ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃን ሚኬል ሳማ ሉኮንዴ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፎቶ : የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia