TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ItsMyDam🇪🇹

ታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሊት የመጀመሪያውን ሃይል ለማመንጨት የሚያስችለውን ውሃ ይዟል፡፡

ዛሬ ሃምሌ 12/ 2013 የውሃ ሙሊቱ ተጠናቆ ከግድቡ አናት ውሃው መፍሰስ ጀምሯል።

ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሊት በያዝነው ሀምሌና ነሃሴ ወር ላይ ለማድረግ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም የዝናቡ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ከታሰበው ጊዜ ቀድሞ ውሃው ሊሞላ ችሏል።

በአመቱ የተከናወኑ ተግባራት የሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሊት ስኬታማ እንዲሆን እንዳስቻለው የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በስፍራው ተገኝተው ተናግረዋል።

22 በሮች እና ትራሽ ክሊነሮች ፤ የስዊች ያርድ ፤ እንዲሁም የትራንስፎርመር ገጠማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል ሚንስትሩ። አሁን ደግሞ የተርባይነሮች ገጠማ ስራ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ ፥ "በተለይ ዘንድሮ ግድቡን ለመገንባት የተኬደበት ፍጥንት የሚደነቅ ነው" ያሉ ሲሆን በቀጣይ ግድቡ እስኪጠናቀቅ በዚሁ ትጋት ስራው እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል፡፡ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ምንጭ፦ የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

ዳይስፖራው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚያደርግበት ድረገፅ ይፋ ሆነ።

በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴው ግድብ ባሉበት ሆነው ድጋፍ የሚያሰባስብቡበት ድረገፅን መሰረት ያደረገ ፕላትፎርም ይፋ ሆኗል።

ይህ ፕላትፎርም www.mygerd.com ድረገፅ በመግባት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ነው።

በድረ-ገፁ አማካይነት የሚሰባሰበው ድጋፍ በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በዘመን ባንክ ለግድቡ ግንባታ ወደተከፈተው የውጭ ምንዛሬ አካውንት እንዲገባ የሚደረግ ሲሆን የሚውለውም ለታለመበት ዓላማ ብቻ ይሆናል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም ለህዳሴው ግድብ ኢትዮጵያውያን በ8100 በኩል ድጋፍ ማድረግ የሚችሉበት አሰራር ተዘርግቶ በ3 የተለያዩ ዙሮች ከ252 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፤ ግድቡ ግንባታው ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ በቦንድና በልገሳ ድጋፍ ተደርጓል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ItsMyDam🇪🇹 ዳይስፖራው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚያደርግበት ድረገፅ ይፋ ሆነ። በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴው ግድብ ባሉበት ሆነው ድጋፍ የሚያሰባስብቡበት ድረገፅን መሰረት ያደረገ ፕላትፎርም ይፋ ሆኗል። ይህ ፕላትፎርም www.mygerd.com ድረገፅ በመግባት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ነው። በድረ-ገፁ አማካይነት የሚሰባሰበው ድጋፍ በብሔራዊ…
#ItsMyDam🇪🇹

ዛሬ ይፋ በተደረገው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ማድረጊያ የድረገፅ ፕላትፎርም ዜጎች ድጋፍ ማድረግ ጀምረዋል።

Mygerd.com የተሰኘው ድጋፍ ማድረጊያ ድረገፅ ይፋ በተደረገ በደቂቃዎች ውስጥ 36 ሰዎች ባደረጉት ልገሳ ስለማድረጋቸው ታውቋል። በዚህም 1,899 የአሜሪካ ዶላር ሊሰበሰብ ችሏል።

አምስትሰዎች ለሌሎች በማስተዋወቅ ዘመቻውን ስለመቀላቀላቸው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የወጣው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ItsMyDam🇪🇹 ዛሬ ይፋ በተደረገው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ማድረጊያ የድረገፅ ፕላትፎርም ዜጎች ድጋፍ ማድረግ ጀምረዋል። Mygerd.com የተሰኘው ድጋፍ ማድረጊያ ድረገፅ ይፋ በተደረገ በደቂቃዎች ውስጥ 36 ሰዎች ባደረጉት ልገሳ ስለማድረጋቸው ታውቋል። በዚህም 1,899 የአሜሪካ ዶላር ሊሰበሰብ ችሏል። አምስትሰዎች ለሌሎች በማስተዋወቅ ዘመቻውን ስለመቀላቀላቸው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ…
#ItsMyDam🇪🇹

Mygerd.com ይፋ መደረጉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ህዳሴ ግድብን በገንዘብ እንዲደግፉና አሻራቸውን ዕድል ፈጥሯል።

እስካሁን 291 ሰዎች ባደረጉት ስጋፍ 23,410 የአሜሪካ ዶላር ተሰብስቧል፡፡ 28 ሰዎች ደግሞ ለሌሎች በማስተዋወቅ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል፡፡

ድጋፉ ቀጥሏል፡፡ ግድቡም ይጠናቀቃል።

#የኢኤኃ

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

Mygerd.com በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።

እስካሁን 898 ሰዎች ባደረጉት ስጋፍ 114,435 የአሜሪካ ዶላር ተሰብስቧል፡፡ 47 ሰዎች ደግሞ ለሌሎች በማስተዋወቅ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል፡፡

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ለግድቡ ድጋፍ ማድረጋቸው ተጠናክሮ መቀጠሉን የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ም/ቤት ፅ/ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሃይሉ አብረሃ ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፥ በቅርቡ በውጭ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለማሰባሰብ ታስቦ በተሰራው ዘመናዊ የሃብት ማሰባሰቢያ ሥርዓት (www.mygerd.com) አማካኝነት ከ132 ሺ ዶላር በላይ ተሰበብስቧል ብለዋል።

ገንዘቡ የተገኘው ከ1 ሺ 29 ለጋሾች መሆኑንም ገልፀዋል።

በድረገፁ ከሚደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ በተጨማሪም #የቴሌብር የሃብት ማስባሰቢያ ተከፍቶ እስካሁን 30 ሺ ብር መሰብሰቡን አቶ ኃይሉ አብርሃ ተናግረዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ከ15 ቢሊዮን 729 ሚሊዮን ብር በላይ ከሕዝቡ መሰብሰቡን ተጠቁሟል።

በሌላ መረጃ ፦ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ24 ሰዓት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ተሰብስቧል።

በ24 ሰዓት የተሰበሰብው 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሲሆን በጎፈንድሚ በኩል ነው። ጎፈንድሚው በድር ኢትዮጵያ በኩል ከ1 ወር በፊት የተከፈተ መሆኑን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን 1,005,060 የአሜሪካ ዶላር ተሰብስቧል።

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ለማድረግ የሚያገለግል የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ።

ይፋ የተደረገው መተግበሪያ" Its My Dam" የተሠኘ ስያሜ ያለው ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ነው ይፋ የተደረገው።

የገቢ ማሰባሰቢያ መተግበሪያውን ወደ ሥራ ለማስገባት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

መተግበሪያዉ ከ1 ዶላር ጀምሮ እስከ 10 ሺህ ዶላር ድረስ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ነው።

Photo Credit : EEP

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

የህዳሴው ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት ሃይል ለማመንጨት በሚያስችል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ም/ቤት ጽ/ ቤት አስታውቋል።

ፅህፈት ቤቱ ይህንን ያሳወቀው በአማራ ክልል የሚገኙ አስር ዩኒቨርሲቲዎች "አንድ እቅድ፤ አንድ ሪፖርት ለተቀናጀ የአባይ ተፋሰስ ልማት" በሚል መሪ ሃሳብ በባህር ዳር እያካሄዱት ባለው ሀገር አቀፍ ዓውደ ጥናት ላይ ነው።

በዚሁ መድረክ ላይ የግድቡ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ሃይል ለማመንጨት በሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሱ እና ግንባታው ከ81 በመቶ በላይ መከናወኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም #ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲውን የበላይነት እንድትጎናጸፍ ማስቻሉን ተገልጿል።

ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 65 ሚሊየን ለሚበልጥ የሀገራችን ህዝብ መብራት እንዲያገኝ ያደርጋል የተባለ ሲሆን ግድቡ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን #ለመላ_አፍሪካዊያን በፖለቲካው የተጎናጸፉትን ድል በኢኮኖሚው መስክ ለመድገም የሚያስችል ነው ተብሏል።

የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በተፋሰሱ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ትስስር በመፍጠር በምርምር የተደገፈ የአፈር መከላትን በማስቀረት የዲፕሎማሲ የበላይነት ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ በባህር ዳሩ መድረክ ላይ ገልጿል።

በባህር ዳት ትላንት የተጀመረው ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት ዛሬም ይቀጥላል።

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

www.mygerd.com ላይ ምን ያህል ገንዘብ ተሰባሰበ ?

በታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ በውጭ ሀገር ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያና የኢትዮጵያ ወዳጆች ታሪካዊ አሻራቸውን የሚያሳርፉበት ድረ ገፅ (www.mygerd.com) ይፋ ሆኖ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ እንደሆነ ይታወቃል።

እስካሁን ድረስ በ1,170 ለጋሾች 149,202 የአሜሪካ ዶላር የተሰበሰበ ሲሆን 53 ሰዎች ደግሞ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ እያደረጉ ይገኛሉ።

ይህ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ የአንድ ወቅት ብቻ ጉዳይ እንዳይሆን እና ዘላቂነት እንዲኖረው ድረገፁን በማስተዋወቅ ገንዘብም እንዲሰባሰብ በማድረግ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባዋል።

እውነተኛ ሀገርን መውደድ እና ለሀገር ማሰብ በተግባር የሚገለፀው እንደታላቁ ግድብ አይነት ስራዎችን ከዳር በማድረስ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገር አሻራን ጥሎ በማለፍ ነውና በተለይ በውጭ ሀገር ብዙ ተከታዮች ያላቸው አካላት ፣ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲሁም አክቲቪስቶች ስራቸውን ማጠናከር አለባቸው።

#ሀገር_ማለት_ሰው_ነውና ከትውልድ እስከ ትውልድ ዘመናትን የሚሻገረውን ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ከጨለማ ውስጥ የሚያወጣውን፣ ድህነታችንንም አሽቀጥሮ የሚጥለውን ከጫፍ የደረሰውን ሀገራዊ ግዙፍ ፕሮጀክት ማጠናቀቅ የሁላችንም ግዴታ ነው።

@tikvahethiopia
#ItsMyDam

ከአሜሪካ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ወገኖች ከተሰባሰበው ገንዘብ ውስጥ ለ3ኛ ግዜ ወደ ኢትዮጵያ 🇪🇹 መላኩን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አሳወቁ።

አሁን ከአሜሪካ የተላከው $757,294.78 ሲሆን በድምሩ $1,757,304.78 የአሜሪካን ዶላር በኢትዮጵያ የግድቡ የባንክ ሂሳብ ገቢ መደረጉን ገልፀዋል።

ለግድቡ ድጋፍ ማሰባሰቡ ስራ መቀጠሉንም አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ የጅማ ፣ አዲስ አበባ ፣ ባህር ዳር እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች በውጭ ካሉ ተመራማሪዎች ጋር የሚመክሩበት የኦን ላይን ሲምፖዚም ይካሄዳል።

ሲምፖዚየሙን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ውሃ ጉዳዮች መማክርት ነው።

ይህን ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየም ለማካሄድ መነሻ ሃሳቡን በተመለከተ ከአስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት ፕ/ር አቻምየለህ ደበላ እንዲህ ሲሉ አብራርተዋል ፦

" ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው አንድ ተለቅ ያለ ይዘት ያለው ጉባኤ ብንፈጥር በዛ ጉባኤ አማካኝነት በተለይ ኢትዮጵያውያኖችን እና የውጭ ሰዎችን ጋብዘን የኢትዮጵያውያን ሳይንቲስቶች ድምፅ የሚሰማበትና በተለይ እውነታው ከምን ጋር እንደሆነ እንዲያውቁ ያደርጋል በሚል ነው የተነሳነው። "

በሲምፖዚየሙ ላይ የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ የኢትዮጵያን ትርክት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስረዳት በምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ ህጋዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ ታልሟል።

ይህን ሲምፖዚየም በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች እና የህዳሴድ ግድብ ዋና ተደራዳሪ እና አማካሪ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ነው ይከፍቱታል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ሲምፖዚየሙ የአባይን ጉዳይ ከብዙ አቅጣጫ ለማየት የሚሞክር መሆኑን ደግሞ ከአስተባባሪዎች መካከል አንዷ የሆኑት መቅደላዊት መሳይ ተናግረዋል።

አስተባባሪዋ ሲምፖዚየሙ ኢትዮጵያውያን ስለህዳሴ ግድቡ በሚገባ አውቀው ለሀገራቸው ትልም እንዲሞግቱ ያደርጋል ተብሎ ታምኖበታል።

ሲምፖዚየሙ ዛሬ ቅዳሜ እና ነገ እሁድ እንዲሁም በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜና እሁድ (ለ4 ቀናት) በኦንላይን በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንደሚካሄድ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ዶቼ ቨለ) ከአስተባባሪዎች መስማቱን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

" የተርባይኖቹ ሃይል ማመንጨት ተከዜና ጣና በለስ ግድቦችን በአንድ ጊዜ የማጠናቀቅ ያህል ነው " - ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ

የታላቁ የህዳሴ ግድብ 2 ተርባይኖች ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት መጀመር ተከዜንና ጣና በለስ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦችን በአንድ ጊዜ የማጠናቀቅ ያህል መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አባል ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ገለጹ።

ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ በጣና በለስና በተከዜ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦች የሚመረተው የኤሌክትሪክ ሃይል የህዳሴው ግድብ ሁለቱ ተርባይኖች ከሚመነጩት ኤሌክትሪክ ሃይል እኩል ነው ብለዋል።

ሁለቱ ተርባይኖች ተጠናቀው ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት መጀመር ሁለት ግዙፍ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክቶች በአንድ ጊዜ እንደማጠናቀቅ ይቆጠራል ሲሉም ገልፀዋል።

ፕሮፌሰሩ ፥ ጣና በለስና ተከዜ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦች እንደቅደም ተከተላቸው 460ና 300 ሜጋ ዋት ሃይል እንደሚያመነጩ አውስተው፤ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሃይል ማመንጫ ግድብ ሁለት ተርባይኖች ስራ መጀመር 750 ሜጋ ዋት ሃይል ስለሚያመነጩ ሁለት ትልልቅ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦችን የማጠናቀቅ ያህል ነው ብለዋል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

ሀገራችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ከ2022 ጀምሮ ከታላቁ የኅዳሴ ግድብ በዓመት 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር የኢትዮጵያ የኢኖቬስን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ሚኒስትር ደኤታ ሁሪያ አሊ ማህዲ አስታወቁ።

ኢትዮጵያ በዚሁ ከመጀመሪያ ዙር እንደምታመነጭ ከሚጠበቀው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አጠቃላይ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በ14 ከመቶ እንደሚያሳድገው ገልፀዋል።

ሚኒስትር ደኤታዋ ሁሪያ አሊ ይህን ያሳወቁት ዛሬ በይነ መረብ በተካሄደ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

ኢትዮጵያን በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለማሳደግ በርካታ ፕሮጄክቶችን እያከናወነች ነው ያሉት ምኒስትር ዴኤታዋ ፥ ከዋነኞቹ ፕሮጀክቶች ግንባር ቀደሙ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ከጥቂት ወራት በኃላ 700 ሜጋ ዋት ማመንጨት ይጀምራል ብለዋል።

@tikvahethiopia
#GERD #ItsMyDam 🇪🇹

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለአል-አረቢያ ሚዲያ የተናገሩት ፦

" ... ሀገራችን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በፍጥነት እንድታጠናቅቅ ግብፅ ማበረታታት አለባት።

ግድቡ ግብፅን በድርቅ ወቅት እንኳ የውሃ ቋት ሆኖ የሚያገለግል እንደመሆኑ ፕሮጀክቱን ልትደግፈው ይገባል።

ሱዳን በአነስተኛ ግድቦቿ ላይ ይደርስብኛል ብላ የምታነሳውን የደህንነት ስጋት በሚመለከት መደበኛ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ ኢትዮጵያ ዝግጁ እንደሆነች አቋሟን አስርድታለች።

ሀገሪቱ ግን አሁን ላይ የራሷን ብሄራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ይልቅ የሶስተኛ ወገን ጉዳይ አስፈፃሚ አየሆነች መጥታለች።

ኢትዮጵያ አንድ ወገን ብቻ ከአባይ ሀብት ተጠቃሚ ሲሆን ዘላለም አለሟን መጠበቅ አትችልም። በመሆኑም ሱዳን እና ግብፅ አሁን ላይ ከያዙት ግትር አቋም መላቀቅ አለባቸው።

ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ በሚመለከት ብዙ አዎንታዊ የሆኑ እድሎችን አቅርባ ነበር። ግብፅና ሱዳን ባለመቀበላቸው ምክንያት ግን ሳይሳኩ ቀርተዋል።

የህዳሴ ግድብ ከጭቅጭቅ ይልቅ የቀጠናዊ ህብረትና አንድነት ማሳያ ነው። ኢትዮጵያ በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ ምንም አይነት የጎላ ጉዳት ሳታደረስ የራሷን ሀብት መጠቀም ትችላለች "

(ኤፍቢሲ)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ItsMyDam

የቀድሞ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ስመኘው በቀለ የተናገሩት ፦

" በዚህ ዘመን ላለነው ትውልድ አይደለም ለኢትዮጵያውያኖች ፣ ለትውልደ ኢትዮጵያውያኖች፣ በውጭ ለሚኖሩ ዜጎች ብቻ ሳይሆን ለመላው የዓለም ህዝብ የተለየ ልዩ መልዕክት እያስተላለፈ ያለ ፕሮጀክት ነው።

በአጠቃላይ ሀገራችንን በተለየ ገፅታ እንድትታይ (በበጎ መልኩ) ፣ በአጠቃላይ ትውልድ በስራ የሚያምን እንዲሆን ፣ በስራ የሚያምን ትውልድ ፣ በእራሱ የሚተማመን ትውልድ መፍጠር የቻለ ፕሮጀክት ነው።"

@tikvahethiopia
አይቀሬው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት እና የግብፆቹ ሚዲያዎች የፈጠራ ወሬ !

ሁሌ ጊዜም ሀገራችን የታላቁ ህዳሴውን ግድብ ባፋጠነች እና የውሃ ሙሌቱን በየዓመቱ ባከታተለች ቁጥር የግብፅ ሚዲያዎች እንቅልፍ ይነሳቸዋል።

በቅርቡ የሶስተኛው ሙሌት መጠናቀቅ አይቀሬ መሆኑን ሲያውቁ ከወዲህ ያልተረጋገጠ መረጃ ለህዝብ ማሰራጨቱን አጥብቀው ተያይዘውታል።

አመር አዲብ የተባለ የሚዲያ ሰው በአንድ ቻናል ላይ ቀርቦ " በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ብዙ እምነት የለንም በግድቡ ላይ መሰነጣጠቆች እንዳሉ እና አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይነገራል " ሲል ያልተረጋገጠ መረጃ ሲናገር ተደምጧል።

" የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ አብዛኛው ሰው ረስቶታል። የህዳሴው ግድብ ሶስተኛው ሙሌት ሊጠናቀቅ ቀናት ቀርተዋል " ሲልም አክሏል።

የዚህን ሰው ንግግር ሚዲያዎች እየተቀባበሉት እያስጮኹ ነው ፤ በእርግጥ የግብፅ ጋዜጠኞች እና ሚዲያዎች ፣ ምሁራን ከዚህም አለፍ ያሉ ብዙ የፈጠራ ወሬዎችን ሲያስወሩ ዓመታትን ያለፉ በሚሆንም በግንባታው ላይ ያመጡት ለውጥ የለም።

አሁንም ሶስተኛው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌት መጠናቀቅ አይቀሬ መሆኑን ሲያውቁ የሚዲያ ዘመቻውን ተያይዘውታል።

#ItsMyDam🇪🇹

@tikvahethiopia