TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አቶ ጌታቸው አሰፋ⬇️

የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው እና ከአገር እንደሸሹ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን በስፋት ሲዘግቡት ሰንብተዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሔርን ስለጉዳዩ BBC ጠይቋቸዋል።

ወ/ሮ ፈትለወርቅ ''እንደ ድርጅት በዚህ ደረጃ #የምናውቀው ነገር የለም። ለድርጅት #የክስ መጥሪያ አይመጣም'' ይላሉ።

በአንድ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ላይ ድርጅቱ ሳያውቀው ክስ ሊመሠረት ይችላል ወይ ተብለው የተጠየቁት የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፤
''ውይይት የሚያስፈልገው ነገር ካለ ፖለቲካዊ ግምገማና ይደረጋል እንጂ ክስን በተመለከተ የመንግሥት ሥራ ነው የሚሆነው'' ሲሉ መልሰዋል። ኾኖም የአቶ ጌታቸው ጉዳይ በግምገማም እንዳልተነሳ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ተናግረዋል።

የኢህአዴግና የሕወሓት የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው አሁን በተካሄደው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ #እንዳልተገኙ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ጠቁመዋል።

የአቶ ጌታቸው በስብሰባው ያለመገኘት ጉዳይ "የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዋል ከሚለው ዜና ጋር የሚያያዝ ነው ወይ?" ተብለው የተጠየቁት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ''አንድ ሰው ሰብሰባ ላይ በግል ጉዳይ ላይገኝ ይችላል። በስብሰባዎች ላይ ሁሉም ሰው ይገኛል ማለት አይደለም። የእሱ ከስብሰባ መቅረት ከዚህ ጋር ይገኛል ማለት #ላይሆን ይችላል። በሥራ ጉዳይም ላይገኙ ይችላሉ'' ብለዋል ወ/ሮ ፈትለወርቅ።

ለመጨረሻ ጊዜ አቶ ጌታቸውን መቼ እንዳይዋቸው ከቢቢሲ የተጠየቁት ወይዘሮ ፈትለወርቅ በቅርቡ ከሁለት ሳምንት በፊት ገደማ #መቀሌ እንዳገኟቸው አረጋግጠዋል።

📌በሌላ በኩል የፌዴራል አቃቢ ሕግ በአቶ ጌታቸው አሰፋ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ልዑካን ቡድኑ በመቐለ የሚኖረው ቆይታ ምን ይመስላል ? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክሳዊት ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ልኡክ ዛሬ ጥዋት መቐለ ገብቷል። ቆይታው ለሁለት ቀን ይሆናል።  ለልዑኩ በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ አቀባበል ተደርጓል። ቀጥሎ በመቐለ ቅዱስ ሚካኤል…
#Update

ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ መቐለ ትግራይ ሲደርሱ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካብኔ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ልዑኩ በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ በትግራይ ጊዚያዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ በተለያዩ ማህበራትን የማህበረሰብ ወኪሎች እና ወጣት ዘማርያን ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል ተብሎ በመርኃግብሩ ቢገለጽም በስፍራው የትግራይ ክልል የሃይማኖት አባቶች ፣ ዘማርያን #እንዳልተገኙ ለማወቅ ተችሏል።

በመቀጠል ልዑኩ በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች እገዛ የሚውል 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በፕላኔት ሆቴል በተደረገ መርኃግብር ላይ ያስረከበ ሲሆን በትግራይ ያሉ የሃይማኖት አባቶች ግን በሥፍራው አልታደሙም።

ደጋፉን የተቀበሉት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከቅድስት ቤተከርስትያንዋ የተበረከተውን ድጋፍ የዘገየ ቢሆንም የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በቅዱስ ሲኖዶሱና በትግራይ አብያተ ክርስትያናት አባቶች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ከተካሄደው ጦርነት ተያይዞ አንዳንድ ጳጳሳት ባደረጉዋቸው ከሃይማኖት ያፈነገጡ ንግግሮች ግንኙነቱ እንዲሻከር ምክንያት መሆኑና፤ ይህን ቅሬታ የፈጠረው አለመግባባት በመመካከር በውይይት ለመፍታት የሚደረገው ጥረት የረፈደ ቢሆንም የሚደገፍ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ፥ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቤተከርስትያንዋ በጀመረችው ጥረት የወደሙ ቤተእምነቶችን ከመገንባትና የተጎዱ የሃይማኖት አባቶች ከመደገፍ በዘለለ የተፈጠረው መቃቃር እንዲሻር በልዩ ጥንቃቄና ፅናት በመስራት ግንኙቱ ተሻሽሎ ትክክለኛ መንፈሳዊ ሂወት እንዲቀጥል ለማድረግ በሚሰራው ስራ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባሰሙት ቃል በትግራይ የተካሄደው ጦርነት ለማቆም ቅዱስ ሲኖዶሱ በግዜው ድምፁ ባለማሰማቱ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል ፣ ይቅርታው የበለጠ እንዲጠናከር ውይይት እጅግ አሰፈላጊ መሆኑ በመገንዘብ የትግራይ የሃይማኖት አባቶች ተባባሪ እንዲሆኑ አባታዊ ምክር አስተላልፈዋል።

ያለፈው ዘግናኝና አሳፋሪ ጦርነት ለማቆም የትግራይና የፌደራል መንግስት ሃላፊዎች በፕሪቶሪያ የፈረሙት ስምምነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የሃይማኖት አባቶች ይህንን ፈለግ ተከትለው  በመወያየት መግባባት እና አንድነት መፍጠር ይገባቸዋል ብለዋል።

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ በተመራው የሰላም ልዑክ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ አትሌት ደራርቱ ቱሉና ሌሎች ተገኝተዋል።

መረጃው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ አባል ነው።

@tikvahethiopia