#AddisAbaba
ትናንት ምሽት 5 ሰዓት ተኩል ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ ከተማ ወረዳ 7 ኢንዱስትሪ መንደር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አንድ ግለሰብ በማሽን ተይዞ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል።
እንደ አዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መረጃ ፤ ከሜድሮክ ድርጅቶች በአንዱ ውስጥ ሰራተኛ የሆነው ሟቹ ትናንት ምሽት አሸዋ በሚፈጭ ማሽን ላይ ስራውን እያከወነ በነበረበት ወቅት በማሽኑ ተይዞ ወዲያው ህይወቱ አልፏል።
አስከሬኑን ከማሽኑ ለማላቀቅ አልተቻለም ነበር፡፡
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስከሬኑን ከማሽኑ አላቀው ማውጣት የቻሉት ለ2 ሰዓት ከፈጀ ጥረት በኋላ ነው።
የትናንቱ በማሽን ላይ የደረሰው አደጋ ጉዳይ በህግ ተይዟል ተብሏል።
በሌላ በኩል ፤ ትላንት በሸገር ከተማ አሸዋ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተወና ወሀ ባቆረ ጉድጓድ ውስጥ ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው አልፏል።
ሟቾቹ ዕድሜያቸዉ 19 እና 23 ነው።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አንደኛውን ወጣት አስክሬን አውጥተዉ ለፖሊስ ያስረከቡ ሲሆን እድሜው 19 ዓመት የሆነው ወጣት አስክሬን የአካባቢው ህብረተሰብ አስቀድሞ አውጥተውታል።
ክፍት የተተወው ጉድጓድ ውሃ ያለበት በመሆኑ አንደኛው ግለሰብ ለመታጠብ ብሎ ገብቶ ተንሸራትቶ ወደ ውሃው ውስጥ ይገባል ፤ የዚህን ሰው መግባት የተመለከተው ሌላው ግለሰብ ደግሞ እርሱን ለማውጣት ሲል ወደ ጉድጓዱ በመግባቱ የሁለቱም ህይወት ወዲያው አልፏል፡፡
#ShegerFM102.1
@tikvahethiopia