TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የድሬዳዋ_ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት አሊ መሐመድ ቢራ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበረከተ! #ድሬዳዋ_ዩኒስቨርሲቲ #DireDawaUniversity

🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት ምን ይመስላል ?

#BahirDarUniversity

- የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበል የዝግጅት ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል።

- በተለይ የዶርምተሪ ጥገናዎች ተደርገዋል፤ ተማሪዎች በዶርም ውስጥ የሚኖራቸው ቁጥር በመመሪያው መሰረት ከዛም በተሻለ መልኩ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

- የተለያዩ የግብዓት አቅርቦቶችም እየተሟሉ ይገኛል።

- ዩኒቨርሲቲው ካሉት ካምፓሶች ሁለቱ (2) ብቻ በኳራንቲን ማዕከልነት አገልግለዋል ፤ በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች የጽዳት ሥራም ይሰራል።

#DireDawaUniversity

- ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ በኳራንቲን ማዕከልነት እያገለገለ ሲሆን በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ወደ ቀድሞ ተግባሩ ለመመለስ እየተሰራ ነው።

- በዶርም ውስጥ የሚገኙ ፍራሾች በአዲስ የሚተኩ ሲሆን የእድሳት ሥራዎችንም በአጭር ግዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል፡፡

- ትምህርትን በሚመለከት ተመራቂ ተማሪዎች እና የአራተኛ አመት ኢንጂነሪንግ ተማሪዎች በተለይ (አፓረንት) የሚወጡ ተማሪዎች ቀድመው ይጠራሉ።

- ተማሪዎች የአንደኛ (1) ሴሚስተር ፋይናል ፈተና ሳይወስዱ ከግቢ በመውጣታቸው ምክንያት ሲመለሱ የማጠናቀቂያ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

- ሆለስቲክ ፈተናም ይሰጣል።

- በተጨማሪም የተግባር ልምምድ (አፓረንት) በተመለከተ ከፈተናው በኃላ የሚወጡ ይሆናል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ቅድመ ዝግጅት በየጊዜው እየጠየቀ እና እየተከታተለ ለተማሪዎች እንዲሁም ለተማሪ ወላጆች ያሳውቃል)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት የተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል ፦

#DireDawaUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ12ኛ ጊዜ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸው 2 ሺህ 93 ተማሪዎችን አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል ከ700 በላይ ሴቶች መሆናቸ ተገልጿል።

#Yekatit12_Hospital_Medical_College

የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ4ኛ እና በ5ኛ ዙር በተለያዩ የህክምና ዘርፍ ያስተማራቸውን 127 ዶክተሮች አስመርቋል።

#AddisAbabaUniversity

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 484 የሕክምና ባለሙያዎችን አስመርቋል። ከምሩቃኑ 209 በስፔሻሊስት፣ ሁለት በዶክትሬት እና 273 በ2ተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ የሕክምና ባለሙያዎች ናቸው።

#MetuUniversity

የመቱ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ ትምህርት ዘርፎ ያሰለጠናቸው 252 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል።

ከሰለጠኑባቸው የትምህርት መስኮች ውስጥ ነርሲንግ፣ ፋርማሲ፣ ህብረተሰብ ጤና እና አዋላጅ ነርሲንግ ይገኙበታል።

ከመካከላቸው 93 ሴቶች ናቸው።

#CateringandTourismTrainingCenter

የሆቴልና ቱሪዝም ስራ ማሰልጠኛ ማዕከል (CTTC) በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 425 ተማሪዎችን አስመርቋል።

በዘንድሮ መርሀ ግብር በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ በድግሪ 16 ተመራቂዎች ፣ በደረጃ 3 በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ 202 ተመራቂዎች ፣ በደረጃ 4 በሆቴል እና ቱሪዝም 157 ተመራቂዎች እንዲሁም በደረጃ 5 በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ 53 ተማሪዎች ነው የተመረቁት።

@tikvahethiopia
#DireDawaUniversity

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት የሕክምና ሳይንስ ተማሪ የነበረው ታሪኩ ሶሪ ሐሙስ ጥር 19/2014 ዓ.ም እኩለ ቀን አካባቢ ራሱን ማጥፉቱን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የተማሪውን ህልፈት ምክንያት ለማጣራት ከጸጥታ አካላት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የተማሪው አስክሬን ወደ አዲስ አበባ ጳውሎስ ሆስፒታል ተልኮ ምርመራ እንደተደረገበት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ዐቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ደቻሳ ጋንፉሬ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው የምርመራው ውጤቱ እንደደረሰው ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ እንደሚያደርግ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

" ተማሪ ታሪኩ ታንቆ ራሱን እንዳጠፋ ነው የምናቀው " ያሉት ዳይሬክተሩ፤ "ከህልፈቱ ጋር እየተነሱ ያሉ ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው" ብለዋል።

የተማሪው አስክሬን ትላንት ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት ወለጋ ዞን ሆሩ ጉዱሩ መላኩን ዳይሬክተሩ ለቲክቫህ ገልጸዋል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
#DireDawaUniversity

በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በጊዚያዊነት ተመድበው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ነባር ተማሪዎች " ግቢው ውጡ አለን " ሲሉ ቅሬታቸውን አድርሰውናል።

ተማሪዎቹ "ግቢውን ለቀን እንድንወጣ ተነግሮናል"፣ "የምግብ አገልግሎትም ተቋርጦብናል" ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀርባሉ።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት መገርሳ ቃሲም (ዶ/ር) ተከታዩን ምላሽ ሰጠውናል።

"መደበኛ ነባር ተማሪዎች በግቢው መቆየት የሚችሉት እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ብቻ ነው። ከሰኔ 30 በኋላ ዩኒቨርሲቲው የክረምት ተማሪዎችን ይቀበላል። በመሆኑም መደበኛ ነባር ተማሪዎችን የምናቆይበት አሰራር የለም።"

"በኮቪድ-19 ምክንያት የተደራረቡና የምንቀበላቸው 5 ሺህ የሚሆኑ የክረምት ተማሪዎች አሉብን። በቅርቡ የተቀበልናቸው የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ነው የሚገኙት። ከዚህ በተጨማሪ ከፍተኛ የበጀት እጥረት ገጥሞናል።"

በመሆኑም ሁሉም መደበኛ ነባር ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ተቋሙ በአካዳሚክ ካላንደሩ መሰረት ነው የሚሰራው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ተማሪዎቹ የዩኒቨርሲቲውን ውሳኔ ሊያከብሩ ይገባል ብለዋል።

More : @tikvahuniversity