TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ዛላምበሳ⬆️

የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች አዲስ ዓመትን በጋራ #በዛላምበሳ እያከበሩ ይገኛሉ፡፡

በክብረበዓሉ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካዔል ተገኝተዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

እንዲሁም ለሁለቱ ሀገራት ዘላቂ #ሰላም መስፈን በሀገራቱ ህዝቦች ተሳትፎ ይረጋገጣል ብለዋል፡፡

📌ዛሬ ማለዳ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ቡሬ #ድንበር ላይ ተገኝተው ከሁለቱ ሀገራት ወታደሮች ጋር አዲስ ዓመትን በማክበር ላይ ይገኛሉ፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሱዳን ካርቱም ግጭቱ አሁንም መቀጠሉ ታውቋል። በተለይ በማዕከላዊ ካርቱም ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ የተመላከተ ሲሆን ግጭት የተባባሰው በሪፐብሊኩ ቤተ መንግስት እና በአል-ማክ ኒምር ድልድይ አካባቢ ነው ተብሏል። ኤርፖርቶችን ለመቆጣጠር አሁንም ድረስ ውጊያ እየተደረገ ነው ተብሏል። በሌላ በኩል የሱዳን ጦር አየር ኃይል ፤ " የፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎችን ዋና ዋና ቦታዎችን በአየር ላይ ማጥቃት…
#Update

የRSF መሪ የሆኑት ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሱዳን ጦር አዛዥ የሆኑትን አብዱል ፈታህ አል ቡርሃንን " ወንጀለኛ " ናቸው ብለዋቸዋል።

የመሩትን ጦርም በመፈንቅለ መንግስት ተጠያቂ አድርገዋቸዋል።

ሄሜቲ ወታደሮቻቸው ወደ ግጭት ተገደው መግባታቸውን አመልክተዋል።

የሱዳን ጦር አዛዥ ሀገሪቱን እንዳወደመ የገለፁት ዳጋሎ ጦራቸውን እያሸነፈ መሆኑንና ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍኑ ፤ ያለው ሁኔታም በቅርቡ እንደሚቋጭ ተናግረዋል።

የጦር ሃይሉ ዋና አዛዥ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን ለአልጀዚራ እንደተናገሩት RSF በጦር ኃይሉ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከጠዋቱ 9 ሰዓት ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። የአልጀዚራ ሂባ ሞርጋን "እና በሁለቱ ወገኖች መካከል ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ የሆኑት ያኔ ነበር" ስትል ተናግራለች።

በሌላ በኩል ፤ የጦር ሃይሉ ዋና አዛዥ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን ለአልጀዚራ በሰጡት ቃል፤ RSF በጦር ኃይሉ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ዛሬ ጥዋት ጥቃት መሰንዘራቸውን ተናግረዋል።

በሁለቱ ወገኖች መካከል ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ የሆኑት ያኔ እንደነበር ተነግሯራ።

በሱዳን ግጭቶች አሁንም መቀጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል። ይህን ተከትሎ ጎረቤቷ ቻድ #ድንበር_ዘግታለች

@tikvahethiopia