TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥቆማ

" የ2024 ESP ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል " - የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የEducation USA Scholars Program (#ESP) 2024 ማመልከቻ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።

ESP በአካዳሚክ ጠንካራ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወደ አሜሪካ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች #እንዲያመለክቱ የሚረዳ የአራት ሳምንታት የሥልጠና መርሃ ግብር ነው።

ዓላማውም ደግሞ የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሰለጠኑ እና ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን መሪዎችን ማፍራት እንደሆነ ኤምባሲው አመልክቷል።

ከአመልካቾች 20 ከፍተኛ የአካዳሚክ ብቃት ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በኤምባሲው ይለያሉ። ተማሪዎቹ በአካዳሚክ ሪከርዳቸው፣ እንዲሁም በኢንተርቪው እንዲለዩ ይደረጋል።

ከጠቅላላው 20 የመጨረሻ እጩዎች መካከል፣ 15 ከፍተኛ ብቃት ያላቸው፣ በኢኮኖሚ የተቸገሩ ተማሪዎች ከመደበኛ ፈተናዎች፣ ከአሜሪካ ቪዛ ክፍያ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን በሚሸፍነው የOpportunity Program Fund (#OPF) ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይመረጣሉ።

የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ስኬታማ ዕጩዎች ወደ አሜሪካ የራውንድ ትሪፕ ትኬት ያገኛሉ።

ቀሪዎቹ 5 ተማሪዎች በስልጠና ፕሮግራሙ ላይ #በነጻ ይሳተፋሉ ነገር ግን የዝግጅት ወጪን ከራሳቸው ምንጭ ይሸፍናሉ። የሞባይል ዳታ ወጪዎች ለሁለቱም የፕሮግራም ተሳታፊዎች በኤምባሲው ይሸፈናሉ።

ማመልከቻ እስከ ሚያዚያ 10/2024 (5:00 pm EAT) ማስገባት ይችላል ተብሏል።

ለማመልከት አስፈላጊ መስፈርቶች ምንድናቸው ?

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ትምህርታቸውንም እዚሁ ኢትዮጵያ እየተከታተሉ ያሉ።

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ/ች #ኢትዮጵያዊ ተማሪ፣

በዚህ የትምህርት አመት መጨረሻ 11ኛ ክፍልን ያጠናቅቁ እና ከመስከረም 2024 ጀምሮ 12ኛ ክፍል የሚማሩ፣

በጠቅላላ 4 ሳምንታት የESP መርሃግብር ለመሳተፍ ቃል መግባት የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ስታመለክቱ የሚያስፈልጉ ፦
1ኛ. የሁለተኛ ደረጃ ትራንስክሪፕት (9፣ 10፣ 11)
2ኛ. ከትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ
3ኛ. የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውና ለOpportunity Fund Program (OFP) የሚያመለክቱ ከትምህርት ቤት ወይም ከቀበሌ የቤተሰብን #ዝቅተኛ የኢኮኖሚያ ሁኔታ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል።

የማመልከቻ ሊንክ እና ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በዚህ ይመልከቱ ፦ https://sites.google.com/amspaceseth.net/educationusa-esp2024

@tikvahethiopia