TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የፌዴራል ፖሊስ ለልጆቻችሁ #ሙሉ_ኃላፊነት ይወስዳል ፤ አስተማማኝ ጥበቃም ያደርግላቸዋል " - የጋምቤላ ትምህርት ቢሮ ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል የፀጥታ ችግር መከሰቱና የሰዎች ህይወት ማለፉ ፣ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም በክልሉ የሰዓት እላፊ ገደብ ታውጆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ…
#NewsAlert

በጋምቤላ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ቦታዎች እንዲሰጥ ተወሰነ።

በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ እና በጋምቤላ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደሚሰጥ የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት ፤ " በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ብቻ ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ያለውን ጫና ለመቀነስ ታስቦ ፈተናው በኮሌጅም ጭምር እንዲሰጥ ተወስኗል " ብሏል።

የክልሉ መንግስት ውሳኔውን ያሳወቀው ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ መግባት ጀምረዋል።

በተለይም በ #ኑዌር_ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ መግባት መጀመራቸው ተገልጿል።

#አኙዋ_ዞን፣ በከፊል ከ #ኢታንግ ልዩ ወረዳና ከ #ጋምቤላ_ከተማ ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ በጋምቤላ ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በነገው ዕለት እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት ወደተመደቡበት የመፈተኛ ጣቢያ በመሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የክልሉ መንግስት አሳስቧል።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርና ሀገር አቀፍ የፈተናዎች አገልግሎት ከክልሉ መንግስት ጋር በመነጋገር ነው በሁለት ቦታ ፈተናው እንዲሰጥ የተወሰነው።

መረጃው ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia