TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የለገሰው 1 ሚሊዮን ብር #ተመላሽ ተደርጓል እየተባለ በማህበራዊ ሚዲየ የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው።

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የለገሰው 1 ሚሊየን ብር ከአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመሆን አስፈላጊ የሆኑ #ግዢዎችን ለማድረግ በጋራ እየተሰራ ይገኛል። ቢሮው እጅግ በጣም አንገብጋቢ ናቸው ያላቸውን የሚገዙ ነገሮች ዝርዝር አውጥቶ ከአለ በጅምላ ለመግዛት ዝግጅት ማለቁንም ከያሬድ ሹመቴ ሰምተናል።

የሚገዙት አስፈላጊ ቁሳቁሶችና የእህል አቅርቦቶች በሙሉ ለተገቢው ጥቅም መዋላቸውን በግልጽ ቁጥጥር በማድረግ ላይ የምንገኝን ሲሆን፤ አላስፈላጊ ግዢዎችና #ብክነቶች እንዳይኖሩ በመመካከር በጋራ እየተሰራ ነው።

#TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በህዝብ ትራንስፖርት የሚጠቀሙ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ፦ * እንዳይቸገሩ ፣ * መንገድ ላይ ሰልፍ ተሰልፈውም ጊዜያቸው እንዳይጠፋ ፣ * ባሰቡበት ሰዓት በህዝብ ትራንስፖርት ያሰቡበት ቦታ እንዲደርሱ በተለየ ሁኔታ ለተወሰነ ሰዓት የግል ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ #ለመገደብ እየተሰራ ይገኛል። ይህ በቅርብ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል። የትራንስፖርት…
የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ፦

- በነዳጅ የሚሰራ #አዲስ ሆነ #አሮጌ የግል አውቶሞቢል መኪና ወደ ሀገር ማስገባት አይቻልም። ሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ ኤሌክትሪክ ብቻ እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል።

- የነዳጅ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ከአምና ጀምሮ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ታግዷል። ግን እስከ ቅርብ ጊዜ በተለያየ መልኩ የሚገቡ ነበሩ። ለምሳሌ ፦ ከውጭ #ተመላሽ ዳይስፖራ ተብሎ እነሱ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም ነበር፤ እነሱ የነዳጅ ሲያስገቡ አይከለከሉም ነበር። ይህ ግን አሁን ላይ አይሰራም። የግል አውቶሞቢል በማንኛውም ምክንያት በዳይስፖራ ሰበብም ይሁን በምንም ሁኔታ እንዲገባ አይፈቀድም።

- የመኪና አስመጪዎች የኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ብቻ ነው ማስገባት የሚችሉት።

- በጣም ያረጁ መኪናዎች ከአገልግሎት እንዲወጡ አዋጅ ወጥቷል። ህግም ወጥቶ መኪናዎች መስጠት የሚችሉት አገልግሎት በእድሜያቸው ልክ እንዲሆንና እድሜያቸው ከአገልግሎት ዘመናቸው ውጭ የሆነ ከገበያ ውና ከአገልግሎት እንዲወጡ የሚሄዱበት ሁኔታ እየተሰራ ነው።

- በተለይ አዲስ አበባ ትንንሽ ሰዎችን ከሚጭኑ ታክሲዎች ይልቅ በአንድ ጊዜ በርካታ ሰዎችን የሚጭኑ ብዝሃ ትራንስፖርት እየተበረታቱ ነው። በሂደት አዲስ አበባ ውስጥ እንደሌሎች ያደጉ ከተሞች 10 እና 12 ሰዎች የሚጭኑ ሚኒባስ ታክሲዎች ከአገልግሎት እየወጡ እንዲሄዱ ይደረጋል። ይህ መጨናነቁንም ፣ ብክለቱን ከከተማ ያስወጣል።

- የብዝሃ ትራንስፖርትን በማሳደግ የተሽከርካሪ ቁጥር ለመቀነስም ታስቧል። የብዝሃ ተሽከርካሪዎች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እንዲሆንም እየተደረገ ነው። አዲስ አበባ በቅርብ የሚገዛቸው ባሶች የኤሌክትሪህ ይሆናሉ።

- ከዚህ በኋላ የመኪና ሰሌዳ ዝም ብሎ አይሰራጭም። አስመጪዎች ሰሌዳ እየወሰዱ / በብዛት እየገዙ ድንበር አካባቢ ሄደው አዲስ / አሮጌ መኪና ላይ በመግጠም እንደነባር ህጋዊ መኪና እያሽከረከሩ የሚገቡበት ሁኔታ አለ። የተራጋ አሰጣቱን ለመቆጣጠር ይሰራል።

- በአዲስ አበባ የፓርኪንግ ቦታ በቅርብ ኖሮ መንገድ ላይ መኪና እንዳይቆም ለማድረግ እየተሰራ ነው። በከተማው በ2 ኪሎ ሜትር አቅራቢያ ፓርኪንግ ካለ ባልተፈቀደ ቦታ ማቆም እንዳይቻል አስገዳጅ ስራ እየተሰራ ነው።

- የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት እንዳይቸጉሩና ባሰቡት ሰዓት ያሰቡበት እንዲደርሱ፣ ሰልፍ ተሰልፈው መንገድ ላይ እንዳይቆሙ ለማድረግና የህዝብ ትራንስፖርት በፍጥነት እንዲመላለስ የግል መኪና ተጠቃሚዎች እንቅስቃሴ እንዲገደቡ ይደረጋል። ይህ የሚሆንበት ሰዓቶችም ተለይተው ተመርጠዋል። በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia