TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
2021.04.19_MUSE_REPORT.pdf
1.3 MB
#ሪፖርት

በሩዋንዳ በ100 ቀን ውስጥ ብቻ 800 ሺህ ገደማ ቱትሲዎች በተጨፈጨፉበት የ1994ቱ የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ፈረንሳይ የተባባሪነት ሚና እንደነበራት የሚያመለክት የምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆነ፡፡

የምርመራ ሪፖርቱ ይፋ የሆነው በሩዋንዳ መንግስት ቀጣሪነት ምርመራውን ባካሄደው ‘ሌቪ ፋይር ስቶን ሚዩዝ’ በተባለ አሜሪካዊ የምርመራ ተቋም ነው፡፡

ተቋሙ እ.ኤ.አ ከ2017 ጀምሮ ላለፉት 5 ዓመታት ሲያካሂድ የነበረውን ምርመራ የመጨረሻ ውጤት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

ሪፖርቱ ይፋ የሆነው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በመሩት እና ዛሬ በተካሄደ ልዩ የሃገሪቱ ካቢኔ ስብሰባ ነው፡፡

ቦቢ ሚዩዝ የተባሉት የመርማሪው ተቋም ባልደረባም ፥ “A Foreseeable Genocide: The Role of the French Government in Connection with the Genocide against the Tutsi” በሚል ርዕስ የተካሄደውን ምርመራ የመጨረሻ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ከ600 ገጾች በላይ ጥንቅር በሆነ ሪፖርቱ ፈረንሳይ ቱትሲዎች ሰለባ በሆኑበት ጭፍጨፋ የ ‘ተባባሪነት ሚና’ እንደነበራት አስቀምጧል፡፡

“ተገማች የነበረው ጭፍጨፋ እውን እንዲሆን ፈረንሳይ ‘የጎላ ሚና’ ነበራት ነው ሪፖርቱ ያለው፡፡ ይህን ሪፖርት ለማጠናቀር በሚሊዬን የሚቆጠሩ የሰነድ ማስረጃዎች ተመርምረዋል፡፡ የ250 ምስክሮች ቃል ተደምጧል፡፡

#Republic_of_Rwanda #AlAIN

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ሪፖርት

በአማራ ክልል "ሰሜን ሸዋ ዞን" በቅርቡ በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ አካባቢውን መልሶ ለማቋቋም በክልል ደረጃ የተዋቀረው የቴክኒክ ኮሚቴ የምልከታ ሪፖርቱን ለአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ አቅርቦ ነበር።

በሪፖርቱ መሰረት ፦

- በሰሜን ሸዋ 3 ወረዳዎች ብቻ 281 ሰዎች ተገድለዋል።

- 197 ዜጎች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።

- 246 ሺህ 818 ሰዎች እርዳታ ፈላጊ ሆነዋል ፤ 9,661 ዜጎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል።

- በሸዋ ሮቢት፣ ቀወትና ኤፍራታ ግድም 4 ትምህርት ቤቶች ወድመዋል፤ 7 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ንብረታቸው ወድሟል።

- ሶስት የጤና ተቋማት ወድመዋል፤ አንድ ጤና ተቋም ተዘርፏል።

- 7 የእምነት ተቋማት ተቃጥለዋል።

- የውሃ መሰረተ ልማቶች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

- አስራ አንድ ሆቴሎች እና አርባ ዘጠኝ የግል መጋዘኖች ተቃጥለዋል።

- እንስሳት መዘረፋቸውና የግብርና መሰረተ ልማቶች ላይ የከፋ ጉዳት ደርሷል።

- የተጎዱ ዜጎችን ለማቋቋምና አካባቢውን መልሶ ለመገንባት ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል።

በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የደረሰውን ጉዳት የቴክኒክ ኮሚቴው እያጠናው የሚገኝ ሲሆን ባጭር ጊዜ ሪፖርቱን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia
#ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ሕብረት ለምርጫ (CECOE) የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ሕብረት ለምርጫ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አበራ ኃይለማርያም የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን በተመለከተ ቃላቸውን ሰጥተውናል።

በአጠቅላይ ምርጫው ሰላማዊ መሆኑን መታዘብ እንደተቻለ ፣ የተለያየ የፖለቲካ ፓርቲዎች የውድድሩን ህግ በማክበር ፍፁም ነው ባይባልም የተሻለ ውድድር ስሜት የተፈጠረበት እና የህዝብ መነሳሳት የታየበት አበረታች የሚባል ሂደት ነበር ብለዋል።

ነገር ግን ምርጫው እንከን አልባ እና ፍፁም ነበር ማለት እንዳልሆነ ተጠባባቂ ዳይሬክተሩ አሳውቀውናል።

ምርጫው ላይ የተለያዩ ችግሮች የነበሩ እንደሆነም አንስተዋል።

ተጠባባቂ ዳይሬክተሩ ፥ "የትኛውም ምርጫ ፍፁም ሆኖም አያውቅም፣ ሊሆንም አይችልም፤ ምርጫ ሂደት ነው የምንማርበት ነው ከዚህ ምርጫ የተሻለ አፈፃፀም ደግሞ በሚቀጥለው ይታያል ብዬ አስባለሁ" ብለዋል።

* የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
#ሪፖርት

በትግራይ ግጭት ሁሉም አካላት ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፈፅመው መገኘታቸውን የጋራ ሪፖርቱ አመላክቷል።

ተፈፅመዋል የተባሉ ጥሰቶች ፦

• ከሕግ ውጪ ግድያና ርሸና፣
• ማሰቃየት፣
• ወሲባዊና ጾታዊ ጥቃቶች፣
• በስደተኞች ላይ የተፈጸሙ ግፎች እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎችን በኃይል ማፈናቀል ይገኙበታል።

በጋራ የምርመራ ሪፖርቱ ከቀረቡት ክስተቶች መካካል በጥቂቱ ፦

በማይካድራ "ሳምረ" በተባለ ቡድን የተፈጸመ ጥቃት ይገኝበታል ፤ ምንም እንኳን ቁጥሩን እርግጠኛ ለመሆን ባይቻልም ከ200 በላይ ሰዎች በዚህ ጥቃት ተገድለው በጅምላ መቃብሮች መቀበራቸውን ተመላክቷል።

የመከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ልዩ ኃይል ከተማውን በተቆጣጠሩባቸው ቀጣይ ቀናት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ላይ የበቀል ግድያዎች መፈጸማቸውን እና የፋኖ ሚሊሺያዎችም በግድያው መሳተፋቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል።

በአክሱም ከተማ የኤርትራ ሠራዊት አባላት ከ100 በላይ ሲቪሎችን መግደላቸውን፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ግድያዎቹ ሲፈጸሙ ጣልቃ ሳይገቡ መቅረታቸውን ሪፖርቱ ገልጿል።

በቦራ አምደውሃ ፣ በቦራ ጫማላ እና ማኢ ሊሃም ከተሞች ከ70 በላይ ሲቪሎች በመከላከያ ሠራዊት መገደላቸውን የጋራ ሪፖርቱ ገልጿል።

እነዚህን እና ሌሎች የግድያ ማስረጃዎችን በመያዝ የሕግ ትንታኔ የሰጠው የምርመራ ቡድኑ በዚህ ጦርነት ውስጥ "የጦር ወንጀሎች" ተፈጽመው ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።

#EHRC #OHCHR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ድርጊቶቹ ከሞራል ወይም ከሰብዓዊነት ያፈነገጡ ናቸው " - አምነስቲ ኢንተርናሽናል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል የነፋስ መውጫ ከተማ ላይ ጥቃት በፈጸሙበት ጊዜ የአስገድዶ መድፈር፣ ዘረፋ እና አካላዊ ጥቃቶች በነዋሪዎች ላይ መፈጸማቸውን ገለጸ። አምነስቲ ባወጣው ሪፖርት በከተማዋ ነዋሪ የሆኑና ያናገራቸው 16 ሴቶች በህወሓት አማጺያን የአስገድዶ…
#ሪፖርት

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል የነፋስ መውጫ ከተማ ላይ ጥቃት በፈጸሙበት ጊዜ ከአስገድዶ መድፈር ፣ ዘረፋ እና አካላዊ ጥቃቶች በተጨማሪ አዋራጅ ንግግር ሲናገሩ እንደነበር ሪፖርት አድርጓል።

አስገድዶ መደፈረ የተፈፀመባቸው ሁሉም ሴቶች ፈጻሚዎቹን ህወሓቶች መሆናቸውን መለየት የቻሉት በአነጋገር ዘያቸው እና በሚሰነዝሩት ብሔርን መሠረት ባደረገ ስድብ እንዲሁም ደግሞ በግልጽ ህወሓቶች መሆናቸውን በመናገራቸው መሆኑን ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተናግረዋል።

ታጣቂዎች በሴቶቹ ላይ የአስገድዶ መድፈር ከመፈፀማቸው በተጨማሪ ሰብዓዊነትን የሚያጣጥል የብሔር ማንነታቸው ላይ ያነጣጠሩ ስድቦችንና ማዋረድን ይፈጽሙ ነበር ብሏል አምነስቲ።

በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ ደግሞ አስገድደው የሚደፍሩት በፌደራል ኃይሎች በትግራይ ሴቶች ላይ የተፈጸመውን ተመሳሳይ ድርጊት ለመበቀል መሆኑን ይናገሩ ነበር ብለዋል።

ምን ያህል ሴቶች ተደፈሩ ?

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በንፋስ መውጫ ነዋሪ የሆኑና ያናገራቸው 16 ሴቶች በህወሓት አማጺያን የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

ከአስራ ስድስቱ መካከል አስራ አራቱ በቡድን የተደፈሩ ናቸው።

አንድ ለአምነስቲ ሪፖርት ያደረጉ የክልሉ ባለሥልጣን ለአምነስቲ እንደገለጹት ደግሞ አማጺያኑ በንፋስ መውጫ ከተማ ከ70 በላይ ሴቶችን መድፈራቸው ሪፖርት አድርገዋል።

የፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ደግሞ አሃዙ 73 እንደሆነ ያመለክታል።

ሙሉ ሪፖርት : https://www.amnesty.org/en/latest/news/2021/11/ethiopia-survivors-of-tplf-attack-in-amhara-describe-gang-rape-looting-and-physical-assaults/

@tikvahethiopia
#ሪፖርት

ከቀናት በፊት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር /TPLF/ ታጣቂዎች በአማራ ክልል ውስጥ የፈፀሟቸውን ግፎች በሪፖርቱ ያሳወቀው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትላንት ሌላ ኢትዮጵያን የሚመለከት ሪፖርት ይዞ ወጥቷል።

ይኸው ሪፖርት በአዲስ አበባ ከተማ የትግራይ ተወላጆችን ትኩረት ያደረገ እስር እየተካሄደ መሆኑን የሚገልፅ ነው።

አምነስቲ በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያ ጉዳይ ሪፖርት ሲያቀርብ ይህ 2ኛው ነው።

አምነስቲ በትላንት ሪፖርቱ በአ/አ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ እስር እየተካሄደ ነው ፤ እስሩ የተባባሰው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኃላ መሆኑን ገልጿል።

ሰዎች ከቤት ወደ ቤት በሚደረግ አሰሳ በቁጥጥር ስር ይውላሉ ፤ በአዲስ አበባ የሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎች በመሙላታቸው በቁጥጥር ስር የዋሉ የመንግስት ሰራተኞች፣ የኦርቶዶክስ ቄስ እና የህግ ጠበቃን ጨምሮ ሌሎች እስረኞች በወጣቶች ማእከላት እና ሌሎች መደበኛ ባልሆኑ የማቆያ ጣቢያዎች ታስረዋል ብሏል አምነስቲ ኢንተርናሽናል።

ሙሉ ሪፖርቱ : https://www.amnesty.org/en/latest/news/2021/11/ethiopia-tigrayans-targeted-in-fresh-wave-of-ethnically-motivated-detentions-in-addis-ababa/

ከቀናት በፊት #ኢሰመኮ በአ/አ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ጀምሮ ሰዎች ከስራ ቦታቸው፣ ከመኖሪያ ቤታቸው እና ከመንገድ ላይ ጭምር በቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ የከተማዋ ፖሊስ ጣቢያዎች ተይዘው እንደሚገኙ አረጋግጫለሁ ሲል ሪፖርት ማድረጉ አይዘነጋም።

ኢሰመኮ እስሩ ማንነት/ብሄርን መሰረት ባደረገ መልኩ በሚመስል ሁኔታ መከናወኑን ማሳወቁ ይታወሳል ፤ (ምንም እንኳን በግልፅ እስሩ የቱን ብሄር መሰረት እንዳደረገ ባይገልፅም) ።

@tikvahethiopia
Amhara Region Report AMHARIC.pdf
1.8 MB
#ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአማራ ክልል በጦርነት በተጎዱ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶችና የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶች ምርመራ ሪፖርት ይፋ አደረገ።

ኢሰመኮ በደረሱት መረጃዎች መነሻነት በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም በአንዳንድ የትግራይ ክልል ደቡባዊ አካባቢዎች በጦርነት አውድ ውስጥ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶችን በተመለከተ ከነሐሴ 22 እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ምርመራ አካሂዷል።

ከላይ ምርመራው ውጤት ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Amhara Region Report AMHARIC.pdf
#ሪፖርት

ኢሰመኮ ከሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል በሕወሓት ኃይሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብትና የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶችን በተመለከተ ያደረገውን ምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።

ከሰኔ 21 - ነሃሴ 22 /2013 ዓ/ም ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው ይህ ሪፖርት እስከ ነሃሴ 30/ 2013 ድረስ የተካሄደ ምርመራ ውጤት ሲሆን የምርመራ ቡድኑ 128 ቃለመጠይቆችን፣  ከተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች፣ የሲቪልና የፀጥታ አካላት፣ ከሲቪክ ማኅበረሰብ አባላት፣ ከተራድዖ ድርጅቶች ጨምሮ 21 የቡድን ውይይቶችን አድርጓል።  

በሪፖርቱ እንዳመላከተው ምርመራው ባተኮረባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በተደረገው ጦርነት ቢያንስ የ184 ሲቪል ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ እንዲሁም በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት እና የሥነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በተለይ የሕወሓት ታጣቂዎች በቁጥጥራቸው ስር በገቡ ከተሞች እና ገጠራማ አካባቢዎች ሲቪል ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውንና ማቁሰላቸውን፣ ሰፊ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ሆን ብለው መፈፀማቸውን ኢሰመኮ አረጋግጧል። 

እንዲሁም የሕወሓት ኃይሎች ወደ ከተሞች ከባድ መሳሪያዎችን መተኮሳቸውን፤ በሲቪል ሰዎች መኖሪያ ቤቶችና ቅጥር ግቢዎች ውስጥ ምሽግ በመቆፈር እና ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ሲቪል ዜጎችን በአፀፋ ለሚተኮሱ ከባድ መሳሪያዎች ጥቃት ማጋለጣቸውን፤ በዚህ የበርካታ ሲቪል ሰዎች ሞትና አካል ጉዳት እንዲከሰት እንዲሁም ንብረት እንዲወድም ምክንያት መሆናቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። 

በሌላ በኩል የመከላከያ ሰራዊት የሕወሓት ታጣቂዎች ሲቪል ሰዎች የሚኖሩባቸው መንደሮች ውስጥ ሆነው የሚፈፅሙበትን ጥቃት ለመከላከል እና ለማጥቃት ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀሙ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞትና አካል ጉዳት ደርሷል፤ ንብረት እንዲወድም ሆኗል።

@tikvahethiopia
#ሪፖርት

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት (UNOCHA) ወደ 40 የሚጠጉ ሰብአዊ እርዳታ የያዙ የጭነት መኪኖች (ምግብን ጨምሮ) ከሰመራ ተነስተው ወደትግራይ ማቅናታቸውን አሳውቋል።

ይህ እኤአ ከጥቅምት 18 በኋላ ወደ ትግራይ ክልል ያቀና የመጀመሪያው ኮንቮይ ነው።

ነዳጅ እና የህክምና ቁሳቁሶችን የያዙ የጭነት መኪናዎች ከባለስልጣናት ፈቃድ እስኪያገኙ ድረስ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ተመላክቷል።

UNOCHA በትግራይ ያለው የሰብአዊነት ሁኔታ ​​እየተባባሰ መምጣቱን ጠቁሞ፣ ወደ ክልሉ የሚደርሰው ሰብዓዊ ዕርዳታ መደበኛ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝቧል።

እኤአ ከጥቅምት 22 ጀምሮ የተቋረጠው ወደ መቐለ ከተማ የሚደረገው በረራ ከትናንትና በስቲያ መጀመሩን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ አየር አገልግሎት (UNHAS) አስታውቋል።

በአማራ ክልል ደግሞ ከ500 የሚበልጡ የጤና ተቋማት በግጭቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል በዚህም በርካታ ሰዎች የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ማድረጉን UNOCHA አሳውቋል።

በአፋር እና በአማራ ክልሎች ለሚቀጥሉት 2 ወራት የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸውን ህጻናት ለማከም በቂ የስነ-ምግብ እና የመመገቢያ ቁሳቁሶች ወደ ሁለቱም ክልሎች መላካቸውን አመልክቷል።

UNOCHA የምግብ አጋሮች በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በደሴና በኮምቦልቻ ከ450,000 በላይ ሰዎችን ለመርዳት የምግብ ድጋፍ ማድረግ መጀመራቸውን ሪፖርት አድርጓል።

ሙሉ ሪፖርት : https://reports.unocha.org/en/country/ethiopia/

@tikvahethiopia
#ሪፖርት

Afar Region | Conflict Situation

የአፋር ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ህወሓት በክልሉ ላይ በፈፀመው ወረራ በ4 ዞኖች (21 ወረዳዎች) 377,000 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና በአሁን ሰዓት በክልሉ 1.3 ሚሊዮን ህዝብ ለችግር ተጋልጧል ሲል አሳውቋል።

- በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከ376,502 በላይ ተፈናቃዮች አሉ።

- ከ205,178 በላይ ሰዎች ከአውሲራሱ፣ ከብላቲራሱ፣ ከፋንቲራሱ እና ከሃሪራሱ ዞኖች አዲስ ተፈናቃዮች ናቸው።

- ከፍተኛ ቁጥር ያለው አዲስ ተፈናቃይ የተመዘገበው ከጭፍራ (42156)፣ አዳአር (33,696)፣ ዳዌ (30,000)፣ ሃዳሌላ (21,000)፣ ሳማሮቢ (18,000) እና ተላሌክ (23,288) ነው። (እኤአ በህዳር 2021)

- መፈናቀሉ አሁንም በአውሲራሱ፣ ቀብላቲራሱ፣ ፋንቲ ራሱ እና ሃሪራሱ ዞኖች እንደቀጠለ ነው።

- በአጠቃላይ በግጭት ምክንያት የተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ በአፋር ክልል 21 ወረዳዎች ውስጥ ወደ 1.3 ሚሊዮን ሰዎችን ለችግር አጋልጧል።

(የአፋር የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል)

@tikvahethiopia
#ሪፖርት : Human Rights Watch !

ሂዩማን ራይትስ ዋች የህወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል #ጭና እና #ቆቦ በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን በጅምላ መግደላቸውን ይፋ አደረገ።

በሁለቱ ስፍራዎች ግድያው የተፈጸፀመው ከነሐሴ 25 - ጳጉሜ 04/2013 ዓ.ም. በነበሩት 10 ቀናት ውስጥ ነው።

መጀመሪያ የህወሓት ኃይሎች ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም ጭና ወደተባለችው መንደር በመግባት ከፌደራል ሠራዊትና ከአማራ ኃይሎች ጋር ውጊያ ካካሄዱ በኋላ ቦታውን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት በነበሩ 5 ቀናት በ15 የተለያዩ ስፈራዎች 26 ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል።

በተመሳሳይ በቆቦ ከተማ ጳጉሜ 04/2013 ዓ.ም በ4 የተለያዩ ስፍራዎች ላይ 23 ሰዎችን እንደገደሉ የዓይን ምስክሮች ለሂዩማን ራይትስ ዋች ገልፀዋል።

ድርጅቱ 36 ሰዎች ቃለመጠይቅ ያደረገ ሲሆን 19ኙ ጭና እና ቆቦ ውስጥ የህወሓት ኃይሎች በአጠቃላይ 49 ሰለማዊ ሰዎችን ሲገድሉ ማየታቸውንና ከሟቾቹ የ44ቱን ሰዎች ስም ገልፀዋል፤ በተጨማሪም የሟቾቹን ቁጥር ከፍ የሚያደርግ የስም ዝርዝር ማግኘቱን አመልክቷል።

የሂማን ራይትስ ዋች የቀውስና የግጭት ጉዳዮች ዳይሬክተር ላማ ፋኪህ ስለግድያዎቹ ሲናገሩ " የትግራይ ኃይሎች በጥበቃቸው ስር ያሉ ሰዎችን በመግደል ለሰው ህይወትና ለጦርነት ሕግጋት ጭካኔ የተሞላበት ግድየለሽነት አሳይተዋል" ብለዋል።

አክለው " እነዚህ በኢትዮጵያ የትግራይ እና የአማራ ክልሎች ውስጥ በተካሄዱ ግጭቶች በሁሉም ወገኖች የተፈጸሙ ግድያዎችና ጭፍጨፋዎች ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ምርመራ እንደሚያስፍልግ ያመለክታሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

ሙሉ ሪፖርት : www.hrw.org/news/2021/12/09/ethiopia-tigray-forces-summarily-execute-civilians

@tikvahethiopia
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት.pdf
1.4 MB
#ሪፖርት

የህወሓት /TPLF/ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል ገብተው በቆዩባቸው ጊዜያት ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ በሲቪሎች ላይ ግድያ እና የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶችን መፈጸማቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ከሐምሌ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ተቆጣጥረዋቸው በነበሩ አካባቢዎች፤ ከጦር እና በሰብዓዊነት ላይ ከሚፈጸም ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ ወንጀሎችን ስለመፈጸማቸው የሚያመለክቱ ማስረጃዎች መኖራቸውን አምነስቲ ገልጿል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል " የትግራይ ኃይሎች በአማራ ክልል ከተሞች የሚገኙ በርካታ ንጹሃን ሰዎችን ሆነ ብለው ገድለዋል ፣ ሴቶች እና ታዳጊዎችን አስገድደው በቡድን ደፍረዋል፤ እንዲሁም የግል እና የሕዝብ ንብረት አውድመዋል " ብሏል።

የህወሓት ታጣቂዎች በጭና እና ቆቦ ከተሞች እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙ ስፍራዎች ላይ ጥቃት ያደረሱት ከነሐሴ 2013 ዓ.ም. አጋማሽ እስከ መስከረም 2014 ዓ.ም. መጀመሪያ ባሉት ጊዜያት ነው።

ታጣቂዎቹ በአካል ላይ ከሚደርሱት ጥቃቶች በተጨማሪ የግድያ ማስፈራሪያዎች፣ ብሔር ተኮር ስድቦች እና ማንቋሸሾች በተጠቂዎች ላይ ሲደርሱ ነበር።

ቆቦ ላይ ከታጣቂ ነዋሪዎች እና ከሚሊሻዎች የገጠማቸውን መገዳደር ለመበቀለ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የበቀል እርምጃ ሲወስዱ እንደነበር አምነስቲ ሪፖርት አድርጓል።

የህወሓት/TPLF/ታጣቂዎች ተቆጣጥረዋቸው በነበሩ በእንዚህ የአማራ ክልል አካባቢዎች ዓለም አቀፍ መሠረታዊ የሆኑ የሰብዓዊ ሕጎችን አለማክበራቸውን ገልጿል።

(ሙሉ ሪፖርት በPDF ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት.pdf
#ሪፖርት

ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል (የፆታዊ ጥቃት) ፦

(ቢቢሲ)

ከሐምሌ ወር 2013 ዓ/ም ጀምሮ በጭና እና በዙሪያዋ እድሜያቸው 14 የሚሆኑ ሴት ታዳጊዎችን ጨምሮ የህወሓት ታጣቂዎች በርካታ ሴቶችን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ መድፈራቸውንና አስገድደው ምግብ እንዲያበስሉላቸው አድርገዋል።

ቃላቸውን የሰጡት 14 የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎች በቡድን፤ አንዳንዶቹ ልጆቻቸው ፊት መደፈራቸውን ተናግረዋል።

አንዲት የ7ኛ ክፍል ተማሪ እና 14 ዓመት ታዳጊ ከእናቷ ጋር በመኖሪያቸው ድር-ባሕር በህወሓት ታጣቂዎች መደፈሯን ተናግራለች።

ይህች ታዳጊ ፥ "ረፋድ 5 ሰዓት አካባቢ መሳሪያ የያዙ ሁለት ወጣቶች ወደ ቤታችን ሲመጡ ከእናቴ እና ከአያቴ ጋር ነበርኩ። አንደኛው የወታደር ልብስ ነው የለበሰው ሌላኛው ደግሞ የሲቪል ልብስ። ትግርኛ እና አማርኛ እየቀላቀሉ ነው የሚያወሩት። 'ቤተሰቦቻችን ተደፍረዋል አሁን እናንተን የምንደፍርበት ተራ ነው' አሉን። አንደኛው ከቤት ውጪ እኔን ደፈረኝ። ሌላኛው ደግሞ ቤት ውስጥ እናቴን ደፈረ። እናቴ አሁን ታማለች። . . . ምን እንደተፈጠረ አናወራም" ስትል ተናግራለች።

የ29 ዓመቷ ሰላም ለ15 ሰዓታት በዘለቀ ቆይታ እንዴት 4 የህወሓት ታጣቂዎች እየተፈራረቁ አስገድደው እንደደፈሯት ተናግራለች።

@tikvahethiopia