TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱን ተናገሩ። ለዚህም የማኅበረሰቡ መዘናጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሐምሌ ወር ላይ ከነበረው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል የመጠቀም 78 በመቶ ምጣኔ አሁን ወደ 52 በመቶ መውረዱን ገልፀዋል።

ዶክተር ሊያ አሁን ላይ በአዲስ አበባ ያለው የጽኑ ህሙማን ክፍል ማከሚያ ማዕከላት መጨናነቃቸውን ተናግረዋል።

በዚህም የፅኑ ህሙማን ክፍል የመጨረሻ የመቀበል አቅም ላይ እየደረሰ ነው ብለዋል።

የፅኑ ህክምና ክትትል ከገቡት 59 በመቶ ህይወታቸው እንዳለፈም አሳውቀዋል።

ዶ/ር ሊያ ፥ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ ትኩረቱን ካላጠናከረ ከባድ የህይወት መስዋትነት ሊያስከፍል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገኙት ክትባቶች በዚህ ዓመት ከሚያዝያ ወር በፊት እንደማይደርሱ ተናግረዋል። ክትባቱን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለማቅረብ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ #AMMA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6_284
• በበሽታው የተያዙ - 544
• ህይወታቸው ያለፈ - 12
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,108

አጠቃላይ 119,025 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,843 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 100,859 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

261 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,313
• በበሽታው የተያዙ - 469
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,294

አጠቃላይ 119,494 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,846 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 102,153 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

258 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ከኮቫክስ የተገኘውና ለ20 በመቶ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሆን የኮሮና ቫይረስ ክትባት በቅርቡ ይመጣል።

ኮቫክስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት ለደሃ አገሮች በዕርዳታ መልክ ለማቅረብ ካቀደው የኮሮና ቫይረስ የመከላከያ ክትባት ውስጥ ፣ ኢትዮጵያ እስከ 20 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን ለመከተብ የሚያስችል የክትባት መጠን በጥቂት ወራት እንደምታገኝ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ
@TIKVAHETHIOPIA
#DrLiaTadesse

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ በሚሰራ አለም አቀፍ የንቅናቄ ቡድን ውስጥ በአስተባባሪነት መመረጣቸውን MoH ገለፀ።

የንቅናቄ ቡድኑ በአለም አቀፉ የጤና ድርጅት እና የክትባት ትብብር የሚመራ ሲሆን የኮሮናቫረስ ክትባት ለሁሉም ሀገራት በፍትሀዊነት ተደራሽ እንዲሆን የሚሰራ ነው፡፡

በቡድኑ አስተባባሪ ሆነው የተመረጡት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የኢንዶኔዢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬትኖ ማርሱዲ እና የካናዳ የአለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ካሪና ጉልድ ናቸው፡፡

ቡድኑ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው 92 የአለማችን ሀገራት ተደራሽ እንደሚሆን ነው ያስታውቀው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#DrLiaTadesse

"9 ሚሊየን የኮቪድ-19 ክትባት ወደ ሃገር ቤት ለማስገባት እየተሰራ ነው" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

በመጋቢት ወር መጨረሻ አልያም ሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ እስከ 9 ሚሊየን የኮቪድ19 ክትባት ወደ ሃገር ቤት እንዲገባ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በክትባቱ እና "እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ" በሚሉት ዘመቻዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ለክትባቱ በዋናነት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዜጎችን የመለየት ስራ እየተሰራ ነውም ብለዋል።

በዚህም የጤና ባለሙያዎች፣ የማህበራዊ ጤና ሰራተኞች፣ የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ማለታቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 7557 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ 1,704 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 19 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 531 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 179,812 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,592 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 145,019 ሰዎች አገግመዋል።

ወረርሽኙ በሀገራችን ከተከሰተ ጀምሮ ከፍተኛው የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 597 ተመዝግቧል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#DrTedrosAdhanom #DrLiaTadesse

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የሀርቫርድ ቲ.ኤች.ቻን ህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት የ2021 ጁሊየስ ቤንጃሚን ሪችመንድ ሽልማትን ተቀብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ የዶክተር ሪችመንድን ምሳሌነት በመከተል የዓለምን ህዝብ ጤና በተለይም አቅመ ደካሞች ጤና ለማሻሻል በቻልኩት ሁሉ ለመስራት ቁርጠኛ ነኝ ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የሀርቫርድ ቲ.ኤች ቻን የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት የ2021 ኔክስት ጄኔሬሽን ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

ዶ/ር ሊያ ለሽልማቱ የበቁት በተለይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በወሰዷቸው ወሳኝ እርምጃዎች መሆኑ ተገልጿል።

ዶክተር ሊያ ታደሰ ፥ የሀርቫርድ ቲ.ኤች ቻን የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ለዚህ የከበረ ሽልማት የመረጣቸው በመሆኑ የተሰማቸውን ክብር ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት እና በቀጣይ በሚሰጠው 2ኛ ዙር ክትባት መርሃ ግብር ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በህንድ ሃገር የተከሰተውን የኮቪድ-19 የወረርሺኝ መስፋፋት ተከትሎ በተለያዩ ሃገራት የክትባት እጥረት ማጋጠሙን በመግለጫቸው ላይ አስታውሰዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሀገራችንም #የክትባት_እጥረት ያጋጣመ ሲሆን ይህን እጥረት ለመፍታት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላቶች ጋር በመሆን ተጨማሪ ክትባቶችን ከለጋሽ አገሮችና እና ክትባትን ከሚያመርቱ ተቋማት ለማግኝት ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

እየተሰራ ባለው ስራ በቅርቡ በተለያየ መጠን ተጨማሪ ክትባት መምጣት እንደሚጀምር ከኮቫክስ የዓለም አቀፍ ጥምረት የተገለጸ መሆኑ ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና የዓለም ጤና ድርጅት ምክረ ሀሳብ መሰረት ሁለተኛው ዙር የኮቪድ-19 ክትባት የመጀመሪያ ዙር ለወሰዱ እና ክትባቱን ከወሰዱ ሶስት ወራት የሞላቸው የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች መስጠት እንደሚጀምር አሳውቀዋል።

2ኛው ዙር የኮቪድ-19 ክትባት እንደ መጀመርያው ዙር የክትባት አሰጣጥ መርሃ ግብር ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ደረጃ በደረጃ ይሰጣል ብለዋል።

መረጃው የጤና ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ሚኒስትሯ በዛሬ መግለጫቸው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተሰጠ ስላለው ስለኮቪድ-19 ክትባት መረጃ ሰጥተዋል።

ዶክተር ሊያ ታደሰ እስካሁን ከ2 ሚሊየን በላይ ዜጎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት እንደወሰዱ ከ42 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ የሁለተኛው ዙር ክትባት እንደወሰዱ አሳውቀዋል።

ክትባቱ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በተከሰተ እጥረት መዘግየቱን ያነሱ ዲሆ በቅርቡ 400 ሺህ የሚጠጋ የአስትራዜኒካ ክትባት ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል ብለዋል።

ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከአርብ ጀምሮ ደግሞ በክልሎች የመጀመሪያውን ክትባት ከወሰዱ 3 ወር የሞላቸው ዜጎች ክትባቱን መውሰድ ይችላሉ ሲሉ ገልፀዋን።

ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ክትባቶችን ለማግኘት የማፈላለጉ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህኛው ዙር ክትባት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዜጎች ዝርዝር ፦

• የትራንስፖርት ዘርፍ ሰራተኞች ( የአውቶብስ እና የሚኒባስ ሹፌሮች)፣
• የመንግስትና የግል ባንኮች ሰራተኞች፣
• የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ቢሮዎች ሰራተኞች፣
• የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የማረሚያ ቤቶችና የፍርድ ቤቶች ሰራተኞች
• የውልና ማስረጃ እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች፣
• መምህራን የህጻናት ማቆያ የመደበኛና የኮሌጅ መምህራን፣
• የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ሰራተኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኞች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።

NB : የመጀመሪያ ዙር ክትባት የሚወስዱ ዜጎች ሁለተኛው ዙር ክትባት ከ3 እስከ 4 ሳምንት ስለሚሰጥ ዜጎች ክትባቱን እንዲወስዱም ዶ/ር ሊያ ታደሰ መልዕክት አስተላልፈዋል። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#DrLiaTadesse #DrMariaVanKerkhove

የዓለም ጤና ድርጅት በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ እየተዘዋወሩ ካሉት አሳሳቢ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች ሁሉ በብዛት እየተዛመተ ያለው #ዴልታ የተባለው በፍጥነት ተላላፊው ዝርያ መሆኑን አስታውቋል።

የዓለም የጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ቴክኒካዊ ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ማሪያ ቫን ኼርኾቭ በሰጡት ቃል አልፋ ፥ ቤታ እና ጋማ የሚባሉት የቫይረሱ ዝርያዎች እያንዳንዳቸው ከአንድ ከመቶ ባነሰ ደረጃ እየተዛመቱ መሆኑን በብዛት እየተስፋፋ ያለው ዴልታው ዝርያ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ መረጃ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፥ በኢትዮጵያ አዲሱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዝርያ (ዴልታ) በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑን ተናግረው በዚህም በዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚያገኝ ተናግረዋል።

የቫይረሱ ስርጭት መስፋፋት በቫይረሱ የሚያዙ ፣ በፅኑ የሚታመሙና ህይወታቸው የሚያጡ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን ገልፀው ፤ ለአዲሱ ቫይረስ መስፋፋት ቫይረሱን ለመከላከል ሚተገበሩ "የጥንቃቄ እርምጃዎች መቀዛቀዝ ምክንያት አንዱ ነው" ብለዋል።

ህዝባዊ ጥንቃቄ የጎደላቸው መሰባሰቦች መብዛታቸውና የህብረተሰቡ በሚፈለገው መጠን ክትባት አለመከተብ ተጨማሪ ምክንያቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።

Credit : MoH/ENA & WHO/VOA

@tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

" ...እየሞቱ ያሉ ሰዎች መሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ክትባት ያልወሰዱ ናቸዉ"- ዶ/ር ሊያ ታደሰ

ዛሬ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅታዊነት እና ክትባት እዲሁም በመጪው ቀናት የሚከፈቱ ት/ቤቶች ማድረግ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ዙርያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ሊያ በመግለጫቸው፦
-አደገኛው የዴልታ ዝርያ መኖሩ
-በየቦታው መሰባሰቦች እና ማስክ አለማድረግ በመበራከቱ
-ደንቦች ተግባራዊነታቸው መቀዛቀዝ ምክንያት በየዕለቱ በቫይረሱ የሚያዙ፣ ወደ ጽኑ ህሙማን መከታታያ ክፍል የሚገቡና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡

በወረርሽኙ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች ቁጥር 6000 እየተጠጋ እንደሆነ ገልፀው፤ ባለፈው ሳምንት ብቻ 308 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው እንዳጡ ይህም ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ትልቅ የሞት አሃዝ ሆኖ እንደተመዘገበ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በየቀኑ በአማካይ ከ1 ሺ ሰዎች በላይ በቫይረሱ ይያዛሉ በዚህ ሳምንትም በየቀኑ በአማካይ 44 ወገኖቻችን እየሞቱ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ ያለተከተቡ ሰዎች ለበሽታው ከፍተኛ ታጋላጭ እንደሆኑ የCDC ጥናትን መነሻ አድረገው የተናገሩ ሲሆን በዚህም በቫይረሱ የመያዝ እድላቸው ከ4.5 እጥፍ በላይ ነው፣ሆስፒታል የመግባት እድላቸው ከ10 እጥፍ በላይ፣ ታመው የመሞት እድላቸው፣ ከ11 እጥፍ በላይ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ዶ/ር ሊያ ታደሰ፥ በአሁን ሰዓት ሀገራችን እየሞቱ ያሉት ሰዎች መሉ በሙሉ ሊባል በሚቻል ደረጃ ክትባቱን ያልወሰዱ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ከሰኔ ወር አጋማሽ እሰከ ነሀሴ ወር አጋማሽ በኮቪድ19 ህይወታቸውን ካጡት ውስጥ አንድ ሰው ብቻ የመጀመርያ ክትባት የወሰደ የሚገኝበት ሲሆን የተቀሩት ግን ያልተከተቡ ናቸው ብለዋል ሚኒስትሯ።

#MoH

@tikvahethiopia