TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ብሔራዊ_ባንክ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከጥር 10 ጀምሮ ለብሔራዊ ባንክ ገዥ ሹመት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ባንክ ገዥ በሆኑት ዶ/ር ይናገር ደሴ ምትክ አቶ ማሞ ምህረቱን በቦታው ላይ ሹመዋል።

አቶ ማሞ ምህረቱ ፤ የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ #ከፍተኛ_የኢኮኖሚ አማካሪና ዋና የንግድ ተደራዳሪ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ሰርተዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይነገር ደሴ በፈቃዳቸው ቦታቸውን ይልቀቁ ፣ ከባንኩ ገዢነት በመንግሥት ይነሱ ወይም ደግሞ ለሌላ ኃላፊነት/ስልጣን ታጭተው እንደሆነ እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም።

ዶ/ር ይናገር ደሴ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው ተሾሙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ከወራት በኋላ በ2011 ዓ.ም ነበር።

@tikvahethiopia
የብድር ስርዓት . . . #ብሔራዊ_ባንክ

ባንኮች ብድር ለመስጠት መያዣ የሚጠይቁበት አሰራር እንዳለ ይታወቃል።

ከዚህ ቀደም ዜጎች ቋሚ የሆነ ማስያዣ ሳያቀርቡ ከባንክ እንዲበደሩ ለማስቻል ስራዎች ተጀምረው እንደነበር መነገሩ ይታወሳል።

አሁን ላይ ይህ ስራ ከምን ደረሰ ?

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ #ለሸገር_ኤፍ_ኤም 102.1 ሬድዮ የሰጡት ቃል ፦

" ተንቀሳቃሽ ዋስትና ሲስተም ዘርግተናል።

ብዙ ነገሮች ከዚህ በፊት ተቀባይነት የሌላቸው ፦
- የቁም እንስሳት
- እህል
- በግምጃ ቤት ውስጥ እህል እናስቀምጥና ርሲት እንይዛለን
- የመሬት አጠቃቀም የምንለው አለ
- ሶፋ
- ፍሪጅ
- ቴሌቪዥን . . . ሌሎችም አሉ፤ አስይዘን የምንበደርበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

ከዚህም ባለፈ IP (Intellectual Property) ጭምር ሃሳብ (Idea) ፋይናንስ የሚደረግበት ስርዓት ነው ይሄ፤ ስለዚህ ሃሳቡን Patent ወይም የሆነ certified ነገር ይዞ ከመጣ ያንን ያሳያል እንደ Collateral ከዚያ በኃላ ብድር ይሰጡታል (ባንኮች) ማለት ነው። ያን ሂደት አሁን ተጀምሮ ወደ 70 ሺህ በMovable Collateral Registry ላይ ተመዝግቧል። ተንቀሳቃሽ ዋስትና አስይዘው ወደ 70 ተበዳሪ ተበድሯል።

ከእውቀት ጋር ፣ ከConsumer protection ጋር ተያይዞ የሚሰራ ስራ አለ፣ ለግብርና ... ወዘተ ከ5 % ያላነሰ ብድር እንዲሰጥ መመሪያ አውጥተን እሱንም ተግባራዊ እያደረግን እንገኛለን። አሁን ባለን መረጃ ከ5 % በላይ ሄዷል። "

@tikvahethiopia