TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
* Tigray

የትግራይ ክልል ጦርነት ወደ አንድ አመት እየተጠጋ ይገኛል ፤ ጦርነቱ የከፋ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ እንዳደረሰ ይታመናል።

ጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ንፁሃን ዜጎች አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እንዳያገኙ ሆነዋል፤ በተለያዩ ቦታዎች ምግብ ለማግኘት በመቸገራቸው በርካቶች ችግር ላይ መውደቃቸው በተደጋጋሚ ሲገለፅ ነበር።

ጦርነቱ ወደአፋርና አማራ ክልሎችም ሰፍቶ ሚሊዮኖችን ችግር ላይ ከጣለ ወራት አልፈዋል።

ዛሬ ድረስ በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል የቀጠለው ጦርነት ሰብዓዊ ድጋፍ ወደህዝብ እንዳይደረስ ከፍተኛ እንቅፋት ሆኗል፤ በዚህም በርካቶች እየተጎዱ ነው።

ዓለም አቀፍ ተቋማት በፀጥታ ችግር እርዳታ ማቅረብ እንደቸገራቸው ሲገልፁ ታይተዋል።

አሁን ላይ ከትግራይ ክልል በተለያዩ አካላት የሚወጡ ሪፖርቶች የምግብ እጦት የሚገድላቸው ሰዎች መኖራቸውን የሚጠቁሙ ናቸው።

ለአብነት ኤፒ ዛሬ ከናይሮቢ ከተማ ባወጣው ዘገባ በአንዳንድ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ርሃብ መግባቱን ጠቁሟል፤ በአንዳንድ ቦታዎች የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሰዎች ለቀናት አረንጓዴ ሳር ለመመገብ እንደተገደዱ ፅፏል።

በአንድ ጤና ጣቢያ አንዲት ወላድ እና ጨቅላ ልጇ በርሃብ እንደሞቱም ገልጿል።

በአይደር ሆስፒታል ጽኑ ታማሚዎች ክፍል ሕክምና ላይ ያሉና በምግብ እጥረት ክፉኛ የተጎዱ 50 ሕጻናትን ፎቶ ከሆስፒታሉ እንደደረሰው ጠቁሟል : https://t.co/4YfTYa3pJ9

በትግራይ በተለያዩ ተቋማት ከሚገለፀው የምግብ ችግር በተጨማሪ የኑሮ ውድነት፣ የምርቶች ዋጋ መናር፣ የኤሌክትሪክ እጦት፣ የኔትዎርክ፣ ባንክ፣ ትራንስፖርት አለመኖር...መላው ህዝቡን ለከፋ ችግር የዳረገ እንደሆነ ይታመናል።

@tikvahethiopia
* Amhara

"በወሎ ሕዝብ ላይ ያንዣበበው አደጋ ታሪክ ራሱን እንዳይደግም ያስፈራል " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ በወሎ ጉዳይ መግለጫ አውጥቷል።

ፓርቲው በላከልን መግለጫ ፥ በወሎ አካባቢ ያንዣበበው አደጋ እጅጉን እንደሚያሳስበው ገልፆ አፋጣኝ መፍትሔ ያሻዋል ብሏል።

እናት ፓርቲ የወሎ ህዝብ ላለፉት ዓመታት በማንነቱ ምክንያት ግፍ ተፈፅሞበታል ያለ ሲሆን ያለፈው መከራና ሰቆቃ አልበቃ ብሎ ሽብረተኛ ተብሎ በተፈረጀው ሕወሓት በተቀሰቀሰው ጦርነት ዛሬም ለከፋ ችግር፣ ለመራር ስቃይ ተዳርጓል ብሏል።

አሁን ላይ በተቀሰቀሰው ጦርነት ህዝቡ የሕወሓት የክፋትና የበቀል በትር እያረፈበት ይገኛል ሲል ፓርቲው በመገለጫው አስፍሯል።

በዚሁ ሳቢያ በመቶ ሺዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፣ በግፍ ተጨፍጭፈዋል፣ ንብረታቸውም በእነጭሬ ላፍሰው ሜዳ ላይ በከንቱ ፈሷል ብሏል።

ፓርቲው በየአካባቢው ካሉ የዐይን እማኞች አረጋግጫለሁ እንዳለው በጦርነቱ ውስጥ እጃቸው የሌለበት ንጹሓን ፦
- ከነፍስ ወከፍ መሳሪያ እስከ ከባድ መሳሪያ ተጨፍጭፈዋል፣
- ሴቶች በተለይ ከዋና ዋና መሥመሮች ወጣ ባሉ አካባቢዎች ተደፍረዋል፣
- በመድኃኒት እጦት ብዙዎች ይሰቃያሉ አለፍ ሲልም ይሞታሉ፣
- ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከግለሰብ ኪስ እስከ ጓዳ በመግባት የትኛውም ይጠቅማል የተባለ ንብረት ይዘረፋል፣
- ተጎጂዎች ሌላው ቀርቶ ውሐ እንኳን ጠጥተን እንሙት እያሉ የዋይታ ድምጽ ያሰማሉ፣
- ውሐ ለመቅዳት ወደ ወንዝ የወረዱ እናቶች ለምን ውሐ ትቀዳላችሁ ተበለው ሊቀዱ የያዙትን እንስራ እንደተሸከሙ በጥይት ይገደላሉ ሲል አስረድቷል።

ፓርቲው ፥ "ይህ ሁሉ ግፍ ሳያንስ በቁም ያሉት ወገኖቻችን የረሃብ አለንጋ እየገረፋቸው፣ የጣር ድምጽ እያሰሙ ይገኛሉ" ብሏል።

* ተጨማሪ ከላይ በተያያዘው መግለጫ ያንብቡ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* Amhara "በወሎ ሕዝብ ላይ ያንዣበበው አደጋ ታሪክ ራሱን እንዳይደግም ያስፈራል " - እናት ፓርቲ እናት ፓርቲ በወሎ ጉዳይ መግለጫ አውጥቷል። ፓርቲው በላከልን መግለጫ ፥ በወሎ አካባቢ ያንዣበበው አደጋ እጅጉን እንደሚያሳስበው ገልፆ አፋጣኝ መፍትሔ ያሻዋል ብሏል። እናት ፓርቲ የወሎ ህዝብ ላለፉት ዓመታት በማንነቱ ምክንያት ግፍ ተፈፅሞበታል ያለ ሲሆን ያለፈው መከራና ሰቆቃ አልበቃ ብሎ ሽብረተኛ…
#Wollo / #ወሎ : እናት ፓርቲ በመግለጫው ፦

1. መንግስትን ፦

የትኛውም ዋጋ ተከፍሎ የወሎ እና የአካባቢውን ማኅበረሰብ ከህወሓት ቡድን ነጻ እንዲያወጣ ጠይቋል።

2. መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶችን ፡-

በአካባቢው ያለውን ሰቆቃ በሚመጥን መልኩ እጃቸውን ዘርግተው ቢያንስ የነዋሪውን ረሃብ እንድታስታግሱለት፣ በእቅፉ ያሉና የጣር ድምጽ የሚያሰሙ ሕጻናት ልጆቹ ድምጽ ተሰምቷቸው በአፋጣኝ እንዲደርሱላቸው ተማጽኗል።

3. ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፡-

በሩቅ የሰማነው የረሃብ እልቂት በወሎ ሕዝብ ላይ አንዣቧልና ለነገ ሳይ ከጉርሱ እየቀነስክ ወሎን እንዲታደግ ፤ ችግሩን አርቆ መመልከት ከተቻለ እንደሀገር የሚገባበት ቀውስ ከባድ ስለሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደየአቅሙ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርቧል።

4. ለፖለቲካ ፓርቲዎች ፡-

እስከአሁን ሲደረግ እንደቆየነው ሁሉ " በትብብር የወሎ ሕዝብ ድምጽ እንሁን ብሎም የአቅማችንን እንድናደርግ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

5. መገናኛ ብዙኃንን ፡-

የረሃብ አደጋ ላንዣበበበት የ #ወሎ_ሕዝብ_ድምጽ እንዲሆኑ ጠይቋል። አሁን ያለው ሁኔታ ቢሸፋፈንም እንዲህ ያለው ሽል ገፍቶ መውጣቱ ስለማይቀር ያኔ በታሪክ ፊት አንገትን ከመድፋት አሁን ረሃብ ላንዣበበት የወሎ ህዝብ ድምፅ እንዲያሰሙ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
* Germany

የጀርመን መንግስት በሁሉም ጉዳት ባጋጠማቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማዳረስ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ ነኝ አለ።

ይህ የተሰማው በዛሬው ዕለት የጀርመን መራሂተ - መንግስት በአፍሪካ የግል ተወካይ እንዲሁም በጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስቴር የአፍሪካ ኮሚሽነር በሆኑት ሚ/ር ጉንተር ኑክ የተመራ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ ሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

የሰላም ሚኒስቴር ውይይቱን ተከትሎ ለህዝብ መረጃ አሰራጭቷል።

የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በህወሃት የጥፋት ምክንያት የተፈጠረው የሰብዓዊ ቀውስ ያለበት ደረጃና ወደፊት በአፋጣኝ ስለሚያስፈልገው ፈጣን ምላሽ ለልዑካን ቡድኑ ማብራራታቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በተለይም በወረራው ምክንያት በአማራ እና አፋር ክልሎች ከ540,000 በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውንና ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ህብረተሰብ ተጎጂ መሆኑን ሚኒስትሯ መግለፃቸው ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ለማቀላጠፍ በርካታ ማሻሻያዎችን በማድረግ ዝግጁነቱን ያረጋገጠ ቢሆንም በአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች እየተሰጠ ያለው ምላሽ ግን ካለው ፍላጎት አንጻር እጅጉን አናሳ መሆኑንም በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ሚ/ር ኑክ የጀርመን መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ በሁሉም ጉዳት ባጋጠማቸው አካባቢዎች ለማዳረስ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የጀርመን መንግስት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia
የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በጎረቤት ሱዳን !

የሱዳን መንግስት መገናኛ ብዙሃን በሀገሪቱ "ያልተሳካ" የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉን አሳውቁ።

የአገሪቱ ገዥ ምክር ቤት አባል ሁኔታው ​​በቁጥጥር ስር መዋሉን ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ሰኞ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራው ተሳትፈዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ ሊጀመር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የሀገሪቱ ጦር በአጭር ጊዜ ውስጥ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ምንጭ ደግሞ ለሮይተርስ፥ መፈንቅለ መንግስቱ ከዋና ከተማዋ ካርቱም በናይል ወንዝ ማዶ በኦምዱርማን ግዛት የመንግሥት ሬዲዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር ሙከራ መደረጉን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
* Update

የሱዳን መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው በሜ/ጄ አብደል ባቂ በክራዊ የተመራ እንደነበር ገለፀ።

በሜጀር ጄነራል አብደል ባቂ በክራዊ የሚመሩትና የግልበጣ ሙከራው አካል የሆኑ ወታደሮች በምስራቃዊ ሱዳን የሚገኘውን የሃገሪቱን ጦር ተቆጣጥረው እንደበር ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

ወታደሮቹ ድልድዮችን እና የመተላለፊያ መንገዶችን ይዘው እንደነበር የተገለጸም ሲሆን የሃገሪቱን ብሔራዊ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያን ለመቆጣጠር በሙከራ ላይ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

ጣቢያው መደበኛ ስርጭቱን አቋርጦ የተለያዩ ሃገራዊ ይዘት ያላቸውን ሙዚቃዎች ይለቅም ነበር ተብሏል፡፡

ኦምዱርማንን ከሃገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱም የሚያገናኘው ድልድይም በአሁኑ ወቅትም ተዘግቶ ይገኛል፡፡

ሆኖም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው በቁጥጥር ስር መዋሉን የሚያመለክቱ መረጃዎችም እየወጡ ነው፡፡

የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ቃል አቀባይ “ነገሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ አብዮቱም ባለድል” ሆኗል ብለዋል፡፡

ሆኖም ሙከራው አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን እና በወታደሮቹ ይዞታ ስር የሚገኙ ነገሮችም እንዳሉ የሚያመለክቱ ዘገባዎች እየወጡ ነው።

ከሰሞኑ በምስራቃዊ ሃገሪቱ አካባቢዎች አመጽ ተቀስቅሶ ነበር፡፡ አመጹ በቤጃ ጎሳ አባላት የተቀሰቀሰ ነበር፡፡

የጎሳ አባላቱ በምስራቅ ሱዳን ያሉ ወደቦችን ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍል ጋር የሚያገኘውን መንገድ ጭምር ዘግተው ነበር፡፡

ለተቃውሞ መነሻ የሆነው የቤጃ ጎሳ አባላት የሚኖሩበት ግዛት ኋላ ቀር ነው የሚል መሆኑን የተለያዩ ሚዲያዎች እየዘገቡት ይገኛሉ፡፡

የቤጃ ጠቅላይ ም/ቤት ተብሎ የሚጠራው የቤጃ ጎሳ አባላት ተቆርቋሪ ያሰማውን ጥሪ ተከትሎ ዋናው መንገድ 5 ቦታዎች በላይ መዘጋቱ ተዘግቧል፡፡

Credit : አል ዓይን

@tikvahethiopia
#Yemen : የሞት ፍርድ !

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት እና የሳውዲው ልዑል በሌሉበት የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው።

በየመን የሑቲ ታጣቂዎች ፍርድ ቤት የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕንና የሳኡዲውን ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማንን በሌሉበት ሞት ፈረደውባቸዋል።

ፍርድ ቤቱ በነዶናልድ ትራምፕ መዝገብ ተከሰው የነበሩ ዘጠኝ ሰዎች ከትናንት በስቲያ በአደባባይ በሞት ቀጥቷቸዋል፡፡

በሞት ከተቀጡት ዘጠኝ ሰዎች መሀል በሚያዝበት ወቅት አዳጊ የነበረ አንድ ልጅ ይገኝበታል፡፡

በሰንዓ አደባባይ ላይ በመቺ ኃይል ከጀርባ እየተተኮሰባቸው እንዲገደሉ የተደረጉት ዘጠኝ የመናዊያን በ2018 አንድ ከፍተኛ የሑቲ አመራርን በሳኡዲ መራሹ ኃይል የአየር ጥቃት እንዲገደል መረጃ አቀብላችኋል በሚል ጥፋተኛ ተብለው የተፈረደባቸው ናቸው፡፡

7ኛው ተከሳሽ የሳኡዲው ልኡል መሐመድ ቢን ሰልማን እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሌሉበት ሞት ተፈርዶባቸዋል፡፡

9ኙ ሰዎች የተገደሉት በሰንአ ታህሪር አደባባይ ሕዝብ በተሰበሰበበት ነበር፡፡

ተመድ ይህን የአደባባይ ግድያ በጥብቅ ያወገዘ ሲሆን አሜሪካ ፣ ዩኬ ፣ እንዲሁም የአውሮጳ ኅብረት ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡

ተመድ የፍርድ ሂደቱ ዓለም አቀፍ ደረጃን የማያሟላ ነበር ሲል ፤ አሜሪካ ደግሞ የተፈፀመድን ድርጊት አሳፋሪ ብላዋለች፤ የአውሮጳ ኅብረት በበኩሉ ቅጣቱ ኢሰብአዊና ነውረኛ ብሎታል፡፡

Credit : BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ ተጠያቂ ባደረጓቸው ፦ - የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት - የአማራ ክልል ባለስልጣናት - የህወሓት አመራሮች - የኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ በፈረሙት የስራ አስፈጻሚ አካል ትዕዛዝ (executive order) የትግራይ…
የኤርትራ መንግስት ምላሽ ለጆ ባይደንን ትዕዛዝ ፦

" ...በአሜሪካ እና አውሮፓ ሀገራት የሚተላለፉ ውሳኔዎችንና የሚወሰዱ እርምጃዎችን ዋነኛ የሀገራዊ ህጎችን እንዲሁም የሀገራትን ነፃነት እና ሉኣላዊነትን የሚጥሱ፣ በማጠልሸት እና በማሰይጠን ዲፕሎማሲያዊ ማስፈራራት የሚያምኑ እና የሚመረኮዙ በመሆናቸው በርትህ እና በህግ ተቀባይነት የላቸውም " - የኤርትራ መንግስት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ ተጠያቂ ባደረጓቸው ፦ - የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት - የአማራ ክልል ባለስልጣናት - የህወሓት አመራሮች - የኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ በፈረሙት የስራ አስፈጻሚ አካል ትዕዛዝ (executive order) የትግራይ…
የኤርትራ መንግስት የጆ ባይደንን ትዕዛዝ ተቃወመ።

ባለፈው ሳምንት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲራዘም ባደረጉ ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ እጃቸው አለበት ባሏቸው ፣ ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይቀርብ ያስተጓጎሉና የቶክስ አቁም ስምምነት እንዳይደረስ እንቅፋት ሆነዋል ባሏቸው ፦
- የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት አካላት
- የአማራ ክልል ባለስልጣናት
- የህወሓት /TPLF/ አመራሮች
- የኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል ማዘዛቸው ይታወሳል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ የኤርትራ መንግስት ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን "በህግ ተቀባይነት የሌለው" ሲል ተቃውሞታል።

የኤርትራ መንግስት በመግለጫው ፥ የህወሓት / TPLF መሪዎች በሰሜን ዕዝ ላይ ወረራ እንደጀመሩ በግልፅ በአደባባይ መናገራቸውን በማስታወስ ወረራው አስቀድሞ በድርጅቱ ማዕከላዊ ስብሰባ ላይ በውይይት የፀደቀ እቅድ እንደነበር በጦርነት ወቅት የተገኘው የህወሓት/TPLF ሚስጥራዊ ሰነድ አጋልጧል ብሏል።

ባለፉት ወራት ይሄን አቻ የሌለው ወንጀል ለመሸፈንና ህወሓትን ከተጠያቂነት ለማዳን ከዛም ባለፈ ሃጥያቱን ወደሌላ ወገን ለማሳበቅ በሰብዓዊ መብት እና የሰብአዊ እርዳታ ስም ሲካሄድ የቆየው ጆሮ የሚያደነቁር የተደራጀ ፕሮፖጋንዳ ዘመቻ እጅግ አስደማሚ ነው ሲል የኤርትራ መንግስት ገልጿል።

መግለጫው አክሎ ፥ ህወሓት እኤአ በ1998 ኤርትራ ላይ ጦርነት አውጆ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሰፊ የጦር ወንጀል በመፈፀም እራሳቸው አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ምስክር /ዋስ ሆነው የፈረሙበትን የመጨረሻውና አሳሪ ብይን ባለመቀበል ለ20 ዓመታት በቀጠናው የፈጠረው ውጥረት ፣ ሱማሊያ ላይ የፈፀመው ወረራ እና ውድመት፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈፀመው ግፍ፣ በደልና ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዋናነት በአሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት ሀገራት ተባርኮ ሲፈፅመው የነበረው ወንጀል እንደሆነ በማስረጃነት አቅርቧል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ የተከሰተውን እና የአፍሪካ ቀንድን ሰላም እየጎዳ ያለው የፀጥታ ችግርና ሰብዓዊ ቀውስ ህወሓት ባለፉት 27 ዓመታት የስልጣን ዘመኑ በምዕራባውያን ሀገራት ትልቅ ባጀትና አይዞህ ባይነት እየታገዘ ሲፈፅመው የነበረው ወንጀል እና ውጤት ቀጣይ ተግባር ነው ብሎታል።

በአሁን ወቅት ህወሓት በተጨነቀ መንፈስ ውስጥ ሆኖ ወዲያ እና ወዲህ እያለ ባለበት የቀቢፀ ተስፋ ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን መከላከል እና ደህንነቱን ማስጠበቅ ባህሪያዊና ህጋዊ መብቱ መሆኑን የኤርትራ መንግስት መግለጫ ጠቁሟል።

ህወሓት እራሱን ከተጠያቂነት ለማሸሽ የትግራይን ህዝብ እንደማያዣነት ይዞ ለከፍተኛ ችግር ለመዳረግ እየፈፀመ እና እየቀጠለ ያለበት አውዳሚ ተግባር የዓለም ማህበረሰብ ሊያወግዘና ሊኮንነው ይገባል ብሏል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ህወሓት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት እና ሴቶችን ጨለማ ውስጥ የከተተበትን ኢሰብዓዊ ድርጊት ከመኮነን ይልቅ የተወሰኑ ወንጀለኞችን ለማዳን የተለያዩ ጫናዎችን በሌሎች ላይ መፍጠር ታሪክ ይቅር የማይለው ኢ-ፍትሃዊ ተግባር ነው ሲል በምዕራባውያን ሀገራት እየተደረገ ያለውን ተግባር ኮንኖታል።

በእንዲህ ያለው ሁኔታ በአሜሪካና አውሮፓ ሀገራት የሚተላለፉ ውሳኔዎችንና የሚወሰዱ እርምጃዎችን ዋነኛ የሀገራዊ ህጎችን እንዲሁም የሀገራትን ነፃነት እና ሉኣላዊነትን የሚጥሱ፣ በማጠልሸት እና በማሰይጠን ዲፕሎማሲያዊ ማስፈራራት የሚያምኑና የሚመረኮዙ በመሆናቸው በርትህ እና በህግ ተቀባይነት የላቸውም ሲል የኤርትራ መንግስት የባይደንን ውሳኔ አጥብቆ ተቃውሞታል።

Credit : ጋዜጠኛ ብርሃነ በርኸ (ኣስመራ-ቪኦኤ)

@tikvahethiopia
* Update

ለመስከረም ሃያው ምርጫ ለድምፅ መስጫ እና ለኦፕሬሽን ሥራዎች የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ከማዕከል ወደ ምርጫ ክልሎች አሰራጭቶ ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

መስከረም 20 ፦
- በሐረሪ ክልል፣
- በሶማሌ ክልል
- በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል ለሚያካሂደው ምርጫና ሕዝበ ውሣኔ፤ ለድምፅ መስጫና ለኦፕሬሽን ሥራዎች የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ከማዕከል ወደ ምርጫ ክልሎች ተሰራጭተዋል።

ሥርጭቱ ዐርብ መስከረም 07 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን ሐረሪ ክልል፣ ሶማሌ ክልል እና ደ/ብ/ብ/ሕ ክልል ላይ የሚሠራጩትን ቁሳቁሶች የጫኑ መኪኖች አዲስ አበባ ከሚገኘው የቦርዱ ጊዜያዊ መጋዘን መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደየጫኑበት ምርጫ ክልል ተንቀሳቅሰው ጨርሰዋል።

በአዲስ አበባና ቅርብ አካባቢዎች ለሐረሪ ተወላጆች ለተከፈቱት ምርጫ ጣቢያዎች የሚሠራጩትን ቁሳቁሶች ደግሞ የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች መድረስ ያለበትን የጊዜ እርዝማኔ ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ እንደሚጠናቀው ቦርዱ ዛሬ ከሰዓት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
* መስቀል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ፤ መጪውን የመስቀል በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቋል።

የቤተክህነቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በበዓሉ አከባበር ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ መግለጫ ስጥተዋል።

ባለፈው ዓመት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ በጥቂት ሰዎች በዓሉ መከበሩን ያወሱት ምክትል ስራ አስኪያጁ ዘንድሮ ተገቢውን የጥንቃቄ ተግባራት በመከወን በድምቀት ለማክበር ታስቧል ብለዋል።

በታሰበለት ጊዜና ድንቅ የግንባታ ስራ በተጠናቀቀው መስቀል አደባባይ ላይ የሚከበረው በዓሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የመስቀል በዓል በድምቀት እንዲከበር በርካታ የቤተክርስቲያኗ ኮሚቴዎች እየተንቀሳቀሱ ነው ያሉት ምክትል ስራ አስኪያጁ የበዓሉ ስነ ስርዓቶች እስከ ቀኑ 12 ሰዓት ድረስ ብቻ ይከወናሉ ብለዋል።

Credit : AMN

@tikvahethiopia
* Addis Ababa

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 5 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ክላስተር 04 በተለምዶ ጃክሮስ አደባባይ አካባቢ የሚገኘውና ቤላ ፒዛ (BELLA PIZZA) እየተባለ የሚጠራው ሬስቶራንት ድንገት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል።

የእሳት አደጋው ከምግብ መስሪያው ማድቤት ውስጥ በሚገኝ የጋዝ ሲሊንደር ድንገተኛ መፈንዳት የተነሳ መሆኑ ተጠቁሟል።

በአደጋው አምስት የድርጅቱ ሰራተኞች ከባድ ጉዳት አጋጥሟቸዋል።

አደጋው ከዚህ የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር በሰራው ስራ የአደጋውን መጠን መቀነስ መቻሉን ተገልጿል።

ጉዳት የደረሰባቸውን 5ቱ ግለሰቦች ለህክምና ወደ ካዲስኮ ሆስፒታል መላካቸውንና በድርጅቱ የወደመው ንብረት ግምት እየተጣራ ነው።

መረጃው የቦሌ ወረዳ 7 ፕሬስ ነው።

@tikvahethmagazine