TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ኬዝ 769 ደርሷል!

በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተያዙ ሰዎች ቁጥር 769 መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቅርንጫፍ አስታውቋል፡፡ በግብጽ 210 ፣ በደቡብ አፍሪካ 150፣ በአልጄሪያ 82 ፣ በሞሮኮ 61 ፣ በቡርኪና ፋሶ 40፣ በቱኒዚያ 39፣ በሴኔጋል 38 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል፤ ቀሪዎቹ 148 ታማሚዎች በ26 የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ ናቸው፡፡ በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽ ከተከሰተ በኃላ 19 ሰዎች ሲሞቱ ፣ 69 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸው ታውቋል፡፡

#EBC #WHO
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በአፍሪካ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ የተከሰተባቸው አገራት አርባ ሶስት (43) መድረሳቸውን እና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 1 ሺህ 396 መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ በአሁኑ ሰዓት 122 ሰዎች ማገገማቸውን ድርጅቱ ጠቁሟል።

ናይጄሪያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የመጀመሪያውን ሞት ማስመዝገቧን ደግሞ ቢቢሲ የሀገሪቱን የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ጠቅሶ ዘግቧል።

በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈው እንግሊዝ ውስጥ የሕክምና ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ሀገሪቱ የተመለሰ አንድ የ67 ዓመት ግለሰብ መሆኑ ነው የተነገረው።

#BBC #WHO #ETV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
# UPDATE

በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ ሺህ ስምንት መቶ ስምንት መድረሱን የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቅርንጫፍ ይፋ አድርጓል፡፡

ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት በ15 ሀገራት ውስጥ ሁለት መቶ አስራ ስድስት አዲስ ታማሚዎች መመዝገባቸው ተገልጿል፡፡

ኮሮና ቫይረስ ጊኒ ቢሳዎ እና ማሊ ለመጀመሪያ ጊዜ መግባቱ እና እያንዳንዳቸው አንድ ታማሚ ማግኘታቸውም ተገልጿል፡፡

#WHO #AfricaCDC #etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ኮቪድ-19 አየር ወለድ ወረርሽኝ አይደለም!" - WHO

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) አየር ወለድ ወረርሽኝ እንደሆነ ተደርጎ የሚገለፀው የሀሰት መረጃ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት በድጋሚ አስታውቋል።

ኮቪድ-19 ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚስልበት፣ በሚያስነጥስበት አልያም በሚናገርበት ወቅት እንደሆነም ነው ድርጅቱ የገለፀው።

ከወረርሽኙ ራስን መከላከል የሚቻለው በሰዎች መካከል ርቀትን ቢያንስ በአንድ ሜትር በማስፋት፣ በተደጋጋሚ እጅን በሳሙና ቢያንስ ለ20 ሰከንዶች አሽቶ በመታጠብ፣ አልኮል ባላቸው ሳኒታይዘሮች እጅን በማፅዳት እና ፊትን በእጅ ባለመንካት ነው።

#etv #WHO
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom #WHO #DonaldTrump

ትላንት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ለWHO የምትሰጠውን ከፍተኛ ገንዘብ እንደምታቅብ ተናገረዋል። የዓለም የጤና ድርጅት ኮቪድ-19 የዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን በጊዜ አልተናገረም ብለዋል ፕሬዘዳንቱ።

ድርጅቱ ይህን ያደርገው በሽታው ለተጀመረባት #ቻይና ሲል ሊሆን ይችላል ሲሉ ግምት አዘል አነጋገር ተናግረዋል። "በጣም ቻይና ተኮር ይመስላሉ ፣ ይህን ማጤን ይኖርብናል' ሲሉ ተደምጠዋል ዶናልድ ትራምፕ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ ባለበት በዚህ አይነት ሁኔታ ለጤናው ድርጅት /WHO/ የሚዋጣ ገንዘብ መከልከ ተገቢ ነው ወይ? ተብለው ከጋዜጠኛ የተጠየቁት ትራምፕ 'እኔ አንሰጥም አላልኩም፣ እናጤነዋለን ነው ያለኩት' ሲሉ መልሰዋል።

ከፍተኛ ዘመቻ እየተካሄደባቸው የሚገኙት የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ዛሬ በሰጡት ዕለታዊ መግለጫቸው ላይ የግድያ ዛቻ እንደደረሰባቸው ፤ እሳቸው ግን ግድ እንዳልሰጣቸው ተናግረዋል። በማን ይህ ሊደረግ እንደቻለ ግን አልተናገሩም።

ከሁለት (2) እና ከሦስት (3) ወር በላይ #ዘረኛ ጥቃቶች ተሰንዝረውብኛል ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ 'ጥቁር ተብያለሁ። እውነቱን ለመናገር እኔ በጥቁርነቴ እኮራለሁ። የሚባለው ነገርም ግድ አይሰጠኝም' ሲሉም ተደምጠዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ፣ ቪኦኤ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WHO

የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ባለፈው ሳምንት በፍጥነት ከፍ እያለ መምጣቱን ተከትሎ፣ አህጉሪቱ ቀጣይዋ የቫይረሱ ማዕከል(Epicenter) ልትሆን ትችላለች አለ።

እስካሁን ድረስ በአፍሪካ በቫይረሱ ሳቢያ ወደ 1,000 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን እና ከ18,000 በላይ ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ የጠቀሰው ድርጅቱ፣ ቁጥሩ በአውሮፓ አንዳንድ ሀገራትና በአሜሪካ ከታየው እጅግ ያነሰ መሆኑን ጠቅሷል።

ቫይረሱ በደቡብ አፍሪካ፣ በናይጄሪያ፣ በኮትዲቯር በካሜሩን እና በጋና ከዋና ከተሞች ወደ መሃል አገር እየተሰራጨ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት መታዘቡን፣ የድርጅቱ የአፍሪካ ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ሞኤቲ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሯ የአፍሪካ ሀገራት ብዙ የኮሮናቫይረስ ህሙማንን የማከም አቅም ስለሌላቸው፣ ከሕክምናው ይልቅ በመከላከል ላይ ትኩረት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

የድርጅቱ የአፍሪካ ዳይሬክተር አክለውም "በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት በቂ የጽኑ ህሙማን ሕክምና መስጫ መሣሪያዎች እንደሌሉ ስለምናውቅ፣ የጽኑ ህሙማን ክብካቤ ወደ መሻት ደረጃ የሚደርሱ ሰዎችን መጠን አነስተኛ ለማድረግ እንፈልጋለን" ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#WHO

የኮሮና ቫይረስ ከዓለማችን ላይ እስከወዲያኛው ላይወደገድ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ ህክምናዎች ዳይሬክተር ዶክተር ማይክ ረያን በትናንትናው እለት በሰጡት ማብራሪያ፥ ቫይረሱ የሚያበቃበትን ጊዜ መተንበይ ትክክል እይደለም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሁላችንም የኮሮናቫይረስ በዓለም ማህበረሰብ ዘንድ ሌላኛው ወረርሽኝ ሆኖ እስከወዲያኛው ሊቆይ ይችላል የሚለውን ከግምት ማስገባት አለብን ያሉት ዶክተር ረያን፥ ቫይረሱ እስከወዲያኛው አብሮን ሊኖርም ይችላል ብለዋል - #BBC

#AlJazeera
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WHO

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መረጃ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 183 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። ከእነዚህ መካከል ከ 50 ሺህ በላይ የሚሆኑት ከብራዚል የተገኙ ሲሆኑ ቀረዎቹ ከአሜሪካ እና ከሕንድ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#WHO #DrTedrosAdhanom

የአስትራዜኔካ ክትባት የደም መርጋትን ስለማስከተሉ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባለመኖሩ በዚህ ስጋት አገሮች ክትባቱን ከመስጠት መቆጠብ የለባቸውም ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

በትንሹ 5 የአውሮፓ ሀገራት አይስላንድ፣ ቡልጋሪያ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ክትባቱን መስጠት አቁመዋል ፤ ይህ የሆነ አንዲት የዳኒሽ ሴት ከደም መርጋት ጋር በተገናኘ እንደሞተች ከተነገረ በኃላ ነው።

ይህንን በተመለከተ የዓለም ጤና ድርጅት በክትባቱ እና በደም መርጋት መካከል ምንም አይነት ግንኙነት የለም ብሏል።

እስካሁን ወደ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ አውሮፓውያን የአስትራዜኔካ ክትባትን ወስደዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም በበኩላቸው ፥ እስካሁን በመላው ዓለም 335 ሚሊዮን በላይ የኮቪድ-19 ክትባት መሰራጨቱን የገለፁ ሲሆን እስካሁን ከክትባቱ ጋር በተገናኘ ምንም ሞት አለመመዝገቡን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#WHO : "አዲሱ ቫይረስ የኮቪድ-19 ክትባቶችን የመቋቋም አደጋን እያሳየ ነው፤ የበለጠ ለመረዳት ጥናቶች ያስፈልጋሉ"

"ሙ" የተባለ አዲስ ልውጥ የኮሮና ተዋህሲ መከሰቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቀ።

ድርጅቱ «ሙ» በሚል በ12 ኛው የግሪክ ፊደል የሰየመውን የአዲሱን ልውጥ ቫይረስ ሁኔታ እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል።

ድርጅቱ ፥ አዲሱ ልውጥ ቫይረስ በሳይንሳዊ መጠሪያው B.1.621 በመባል የሚታወቅ መሆኑን በትናንቱ የኮቪድ-19 ሳምንታዊ መግለጫ እመልክቷል።

አዲሱ ቫይረስ የኮቪድ-19 ክትባቶችን የመቋቋም አደጋን እያሳዬ መሆኑን የገለፀው ድርጅቱ፤ የበለጠ ለመረዳት ግን ጥናቶች እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥቶበታል።

ቫይረሱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ በደቡብ አሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት ተገኝቷል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም ለልውጥ ቫይረሱ በግሪክ የመጀመሪያው እና የሁለተኛው ፊደል «አልፋ» እና «ቤታ»የሚል መጠሪያ መሰጠቱም ይታወሳል። #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
#UNESCO #WHO

" ... ድርጅቶቹ ያለአድሎ ኃላፊነታቸውን ሊወጡና የህወሃት ቡድን የፈጸመውን ውድመት በይፋ ማውገዝ ይጠበቅባቸው ነበር " - አቶ ዮሴፍ ካሳዬ

ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ካሳዬ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተጠሪ ከሆኑት ዶ/ር ዮሚኮ ዮኮዝኪ እና የዓለም ጤና ድርጅት ተጠሪ ዶ/ር በርማ ኤች. ሳምቦ ጋር ተወያይተዋል።

በወቅቱም አቶ ዮሴፍ ፥ የህወሓት የሽብር ቡድን የትግራይ ክልልን ጨምሮ በአፋር እና አማራ ክልሎች የባህላዊ ቅርሶች እና የጤና መሰረተ ልማቶች ላይ የፈጸመውን ውድመት ለማውገዝ ድርጅቶቹ ቸልተኝነት ማሳየታቸው ገልጸውላቸዋል።

አቶ ዮሴፍ ፥ " ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ንብረቶች ላይ የደረሰው ውድመት እና የንብረት ዘረፋ ከፍተኛ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው " ያሉ ሲሆን " የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉዳዩን በቸልታ ማለፉ ህወሃት በተግባሩ እንዲገፋበት አበረታቶታል " ብለዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ተመድ መስራች አባልነቷ ከሁሉም የተመድ ድርጅቶች ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንዳላት አንስተው፣ ድርጅቶቹም ያለአድሎ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና የህወሃት ቡድን የፈጸመውን ውድመት በይፋ ማውገዝ ይጠበቅባቸው እንደነበረ አጽንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።

የስራ ኃላፊዎቹ በበኩላቸው ከዋና ዳይሬክተሩ ጋር ስላደረጉት ውይይት ምስጋናቸውን ገልፀው፣ ያላቸውን ኃላፊነት ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የኢትዮጵያን ጉዳይ በአንክሮ ለመመልከት ቃል መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Tigray , #Mekelle 📍

የዓለም ጤና ድርጅት ( #WHO_Ethiopia ) 33. 5 ሜትሪክ ቶን የሚገመት አስፈላጊ የሆኑ መድሃኒቶችን እና የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ መጀመሩን አስታውቋል።

ድርጀቱ በቀን 10 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል ይገባል ብሏል።

በዛሬው ዕለትም 10 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁሶችን በአውሮፕን ወደ ትግራይ ክልል መግባቱን አስታውቋል።

ፎቶ፦ WHO Ethiopia

@tikvahethiopia
#WHO

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል በላይ የሰዎች ጤና አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘው በትግራይ ክልል ውስጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ያሉት ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ " "በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል በላይ በትግራይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጤና በአደጋ ላይ ይገኛል" ብለዋል።

"አዎ እኔ ከትግራይ ነኝ። ይህ ቀውስ እኔን፣ ቤተሰቤን እና ጓደኞቼን በግል ይጎዳል። ግን እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር፤ በስጋት ውስጥ ያለን ጤና የመጠበቅ እና የመንከባከብ ኃላፊነት አለብኝ። በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል በላይ በትግራይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ጤና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል" ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ፤ በክልሉ ላለው ሰብዓዊ ቀውስ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት ይፋዊ ያልሆነ እቀባን ተጠያቂ አድርገዋል።

በተጨማሪ በዚሁ መግለጫቸው ላይ ድርጅታቸው 95 ሺ ሜትሪ ቶን መድኃኒት ወደ ትግራይ ለማድረስ ፍቃድ አለማግኘቱን ተናግረዋል። ላለፉት 500 ቀናት የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሥታት በትግራይ ያሉ 6 ሚሊዮን ሰዎችን ይፋዊ ባልሆነ እቀባ ሥር አድርገዋል ብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ላቀረቡት ክስ የኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ የሰጠ ሲሆን ክስ መሰረተ ቢስ ነው ብሎታል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም "መድኃኒቶችን ወደትግራይ ክልል እንዳናስገባ የኢትዮጵያ መንግሥት ፈቃድ አልሰጠንም" በሚል ያቀረበው ክስ መሰረተ ቢስ ነው ሲል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ፤ ማንም የከለከላቸው የለም ፤ ቀድሞ ፈቃድ እንደተሰጣቸው እየታወቀ መዋሸቱ አግባብ አይደለም ብሏል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-03-17

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" በዓለማችን በየ2 ደቂቃ ልዩነቱ  በማህፀን በር ካንሰር ምክንያት ሴቶች ህይወታቸውን ያጣሉ " - የዓለም ጤና ድርጅት

የማህፀን በር ካንሰር (Cervical Cancer) ፦

- የማህፀን በር ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ  ካንሰሮች በገዳይነቱ በዓለም 4ኛ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ 2ኛ ላይ ተቀምጧል::

- ይህ የካንሰር ዓይነት 99.7% መነሻው (Human papilloma virus)  የተባለ ቫይረስ ሲሆን ከሰው ወደ ሰው በጾታዊ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፍ ነው፡፡  ይህ የቫይረስ ዓይነት ከ200 በላይ ዓይነቶች ሲኖሩት የማህፀን በር ካንሰር የሚያመጡት ጥቂቶቹ ሲሆኑ HPV 16 እና HPV 18 የተባሉት ዋነኞቹ ናቸዉ፡፡

- ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ላይ፣ የበሽታ መከላከል አቅማቸው የቀነሰ እንደ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ሰዎች፣ ከአንድ ሰው በላይ ጋር ግንኙነት ሚያደርጉ እና የአባላዘር በሽታ ያለባቸው  ሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው።

-  ለብዙ ጊዜ ምልክት ሳያሳይ በሰውነት ውስጥ ሊቆይ ይችላል፡፡

  ምልክቶቹም-
▪️ከግንኙነት በዃላ በብልት በኩል መድማት
▪️የወር አበባ ካለቀ በዃላ እና በሁለት የወር አበባ ጊዜ መካከል ያለ መድማት
▪️በብልት በኩል ያልተለመደ ጠረን ያለው ፈሳሽ መዉጣት
▪️ከ Menopause (ማረጥ) በኋላ የሚኖር የማህፀን መድማት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

- በዓለማችን በየ 2ደቂቃ ልዩነቱ  በማህፀን በር ካንሰር ምክንያት ሴቶች ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ከ90 በላይ የሚሆኑት ደግሞ እንደኛ በመካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ላይ ነው፡፡

- ይህንን ደግሞ ታዳጊ ሴቶች የማህፀን በር ካንሰር ክትባትን በመከተብ እንዲሁም እድሜያችው 21 እና በላይ የሆኑ ሴቶች ቢያንስ በየ3 ዓመቱ ቅድመ ምርመራ በማድረግ መከላከል ይቻላል፡:

- ይህ በሽታ በአግባቡ በሚደረግ ቅድመ ምርመራ በጊዜ ከተገኘ በህክምና የመዳን አድሉ ከፍተኛ ነው።

▫️ስለዚህ ታዳጊ ሴቶችን  ክትባቱን በማስከተብ እና እድሜያቸው ከ21 አመት በላይ የሆኑ ሴቶች ደግሞ  በየ3 አመት ሚደረገውን ቅድመ ምርመራ በማድረግ በበሽታው ምክንያት የሚከሰት የጤና መጓደልን እና ሞትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይቻላል፡፡

#WHO #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ወባ (Malaria)

" በኢትዮጵያ ተከታታይ በሆኑ ጦርነቶች፣ መፈናቀሎች እንዲሁም ሌሎች ወረርሽኞች ሳቢያ በባለፉት 2 ዓመታት ላይ ተመስርቶ  በወጣ ሪፖርት የወባ በሽታ ቁጥር ከ150%-120% ጭማሪ አሳይቷል " - #WHO Ethiopia

ወባ ተላላፊ በሽታዎች ከሚባሉት መካከል አንዱ ሲሆን የሚተላለፈውም  Plasmodium በሚባል የፕሮተዞአ ዓይነት በሴቷ አኖፊለስ የወባ ትንኝ አማካኝነት ነው።

- የወባ ትንኝ ዉኃ የቋጠረ ረግረጋማ ቦታ ላይ በብዛት ትራባለች።

- የወባ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ብዙ በመሆናቸው የሚያስከትሉት ችግር አንዱ ከአንዱ ይለያያል። ለሞት የሚዳርጉ አሉ፤ቀለል ያለ ህመም የሚያስከትሉም አሉ። በኛ ሀገር ሁለቱም ይገኛሉ። በዋናነት የከፋ ችግር የሚያስከትሉት P.falciparum እና p.vaivax ተብለው የሚጠሩት ናቸው።

▫️P.falciparum የተባለው በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሃገሮች ላይ በስፋትም በገዳይነትም ብዙውን ድርሻ ይወስዳል፡፡

-ለወባ በሽታ ማንኛውም ሊጋለጥ ይችላል::የወባ በሽታ ከተላላፊ በሽታዎች በገዳይነቱ ወደር የሌለው ነው።በተለይ በህፃናት፣ ነብሰ ጡር እናቶችና አረጋዊያን ላይ ሲከሰት የገዳይነት ጉልበት ያገኛል።

ምልክቶቹ ፦
▪️ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት ፣ ማንቀጥቀጥ
▪️ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት
▪️ሆድ ህመም፣ማስታወክ፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ
▪️ራስ ምታት፣ሰውነትን ጥምቅ ሚያደርግ ላብ

- ወባ አብዛኛውን የሰውነት ክፍል ያጠቃል። የከፋ ከሚሆንባቸው አንዱ አንጎልን ሲያጠቃ ነው። በተለምዶ የጭንቅላት ወባ (Cerebral malaria) ተብሎ ይጠራል።

- ሌላው ወባ የኩላሊት መድከምን ሲያስከትል ነው። አንዳንዴ የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው ደረጃም ላይ ይደርሳል።

- የልብና የሳንብ ችግር በማስከተል ለሞት የመዳረግ አቅም አለው። በተጨማሪም የደም ማነስ ያስከትላል።

* መከላከያ መንገዶች

የወባ ትንኝ ንክሻን በመከላከል፤ የመራባት አቅሟን በማስቆም፣ ቅድመ መከላከል መድሐኒት በመውሰድ መከላከል ይቻላል።

- በወባ በሽታ በብዛት ተጠቂ በሆኑ ቦታዎች ላይ የቤት ውስጥ ፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት ማድረግ እንዱሁም ደግሞ በፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል የተነከረ አጎበርን በአግባቡና በትክክል መጠቀም፤ዉኃ የቋጠረ ረግረጋማ ቦታን በማፋሰስ የወባ ትንኝ እንዳትራባ ማድረግ እና ወባ በብዛት ያለበት ቦታ ልንሄድ ከሆነ ሃኪም በማማከር ቀድመን ፀረ-ወባ መድሃኒት መውሰድ ናቸው፡፡

▪️ከላይ የተባሉትን ምልክቶች ብዙ ጊዜ በሽታውን በያዘችው ትንኝ ከተነከስን ከጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት በኋላ ልናይ እንችላለን፤አንዳንድ የወባ በሽታ አይነቶች ግን እስከ አመት ድረስ ምልክት ሳያሳዩ በሰዉነታችን ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ።

▫️ምልክቶቹን ካየን ግን በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ይኖርብናል።

#WHO, #EthioDemographyAndHealth

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች እና የአእምሮ ጤና ፦

- የታዳጊ ልጆች እድሜ (ጉርምስና) ልዩና ወሳኝ ጊዜ ነው:: አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ለውጦቹም ከፍተኛ ናቸው።

- በዚህ ጊዜ ላይ ለድህነት፣ ለጥቃት (አካላዊም ፆታዊ) መጋለጥ እዚህ ዕድሜ ላይ ላሉ ልጆች ለአእምሮ ጤና መታወክ የበለጠ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል::

አጋላጮች ፦
▫️የአቻ ግፊት
▫️አካባቢያዊ ተጽዕኖዎች
▫️አካላዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት
▫️የቤት ውስጥ ሰላም መጓደል
▫️የማንነት ጥያቄ
▫️የሚዲያ ተጽዕኖ
▫️ከፍላጎት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች የተወሰኑት ናቸው።

- በተለይም የአዕምሮ እድገት ውስንነት፣ የተለያዩ የነርቭ ችግሮች፣ የቅርብ ቤተሰብ ድጋፍ የሌላቸው ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች ደግሞ የበለጠ ለአዕምሮ ጤና መታወክ የተጋለጡ ናቸው።

ከስሜት ጋር የተያያዙ ችግሮች ፦
* ከልክ በላይ ጭንቀት
* የስሜት መዋዠቅ
* ድባቴ፣ ራስን ማግለል አልፎም #በህይወት_መቆየት_አለመፈልግ

የባህሪ ችግሮች ፦
° ትኩረት ማጣት፣
° ለነገሮች መቸኮል፣
° የፀባይ ለውጥ መኖር

የአመጋገብ ችግር ፦
ውፍረት እንዳይመጣ ከሚል ከፍተኛ የሆነ የአመጋገብ ችግር ነው።

የስነ-ልቦና ቀውስ ፦
• ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ ያደርጋል።
• ራሳቸውን በተለያዩ ሱሶች ይጎዳሉ።
• ከማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከፍተኛ  ተጽዕኖ ያሳድርበታል።

- ይህ እንዳይሆን ምን እናድርግ ?
▪️ቤተሰብ ልጆቹ በሰውነታቸው ላይ ለውጥ እየተካሄደ እንደሆነ በመረዳት ለልጆቹ ከምን ጊዜውም በላይ ቅርብ መሆን አለበት።
▪️ራሳቸውን በተለያዩ ዓይነት ስራዎቸ(እንደ ስፖርት ያሉ ነገሮች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ)፣ የመፍትሄ ሰዎች እንዲሆኑ፣ በጤነኛ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ  በማድረግ ሁሉም ሰው የድርሻውን ማድረግ አለበት።።

#WHO #የዓለምጤናድርጅት

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

አልኮል ፦

- አልኮል በዓለም ላይ 3 ሚለዮን ለሚሆኑ ሞቶች አስተዋፅኦ ያደርጋል፤ እንዲሁም ደግሞ ከ200 በላይ ላሉ አካላዊ እና አዕምሮአዊ የጤና ችግሮች መንስኤ ነው፡፡

- ምንም እንኳን እንደሚወሰደው መጠንና የጊዜ ብዛት ቢለያይም የትኛውም አልኮል መጠን ጤና ላይ ተፅዕኖ አለው፡፡

ከሚያስከትለው የጤና ችግር በጥቂቱ ፦
አዕምሮን ነገሮችን የሚመለከትበትን መንገድ በመቀየር የባህሪ ችግር እንዲኖርና ነገሮችን በትክክል ማሰብ እንዳይችል ያደርጋል፤ አልፎም ተርፎም ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ በማወክ ለአዕምሮ ቀውስ ይዳርጋል።
የልብ አመታት ችግር
የልብ ጡንቻዎች መድከም
ስትሮክ
የደም ግፊት
የጉበት ህመም ፤ ጉበትን ከጥቅም ውጪ በማድረግ ስራውን እንዲያቆም ብሎም ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡
የተለያዩ ንጥረ ቅመሞችን የሚያመርተው ቆሽት መርዛማ ንጥረ-ነገሮችን እንዲያመርት፤ በዚህም ምክንያት ለራሱም እንዲሁም ሌሎች አካላትን እንዲጎዱ ያደርጋል፤ ይህ ደግሞ ለስኳር እና ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡
በቀን ውስጥ 1 የአልኮል መጠጥ የምትጠጣ ሴት በጡት ካንሰር የመያዝ እድሏ ከ 5-9% ያህል ከማይጠጡት ይልቅ ይጨምራል፡፡
የአንጀት ካንሰርን ጨምሮ አልኮል የብዙ ካንሰር ዓይነቶች መንስኤ ነው፡፡
ብዙ አልኮል መጠቀም የበሽታ መከላከል አቅምን በመቀነስ ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡ 
ትምህርት ላይ ባለው ተፅዕኖ፤ የጤና እክልን በማምጣትና ያለዕድሜ ህይወት እንዲያልፍ በማድረግ ምርታማነትን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡

በየቀኑ ወይም ደግሞ በአንድ ጊዜ ብዙ የአልኮል መጠን መውሰድ በየቀኑ ለምንሰራቸው ስራዎች እንቅፋት ይሆናል፤ በአካልም በስነልቦናም የአልኮሉ ጥገኛ ሆነን ራሳችንን ልናገኘው እንችላለን፤ ይህን ችግር ራሳችን ላይ ካየነው እርዳታ በመፈለግ ህክምና ማግኘት ይኖርብናል፡፡

በቅርብ ያሉ ቤተሰቦቻችን ወይም ጓደኞቻችን ላይ ይህን ችግር ካየን ለአዕምሮቸውም እንዲሁም ለአካላቸው ጤና ስንል ከማግለል ይልቅ ተገቢውን እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

#PAHO #WHO

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#WHO🚨

በግብረ ስጋ ግኝኑነት የሚተላለፉ ሽታዎች ወይም የአባላዘር በሽታዎች በዓለም ዙሪያ እጅግ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየጨመሩ እንደሚገኙ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) አዲስ ሪፖርት አሳይቷል።

ሪፖርቱ ፥ በየዓመቱ በመላው ዓለም 2.5 ሚሊዮን ሰዎች በግብረ ስጋ ግኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ፣ በኤችአይቪ እንዲሁም ሄፓታይተስ እየሞቱ ናቸው ብሏል።

በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉት እና ሊታከሙ የሚችሉ በሽታዎች እጅግ በፍጥነት እየተስፋፉ ሲሆን ሁኔታው አሳሳቢ ስለመሆኑ በሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል።

ሪፖርቱ ፦ https://www.who.int/news/item/21-05-2024-new-report-flags-major-increase-in-sexually-transmitted-infections---amidst-challenges-in-hiv-and-hepatitis

በዓለም ላይ በየዕለቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ የተለያዩ የሽታ አይነቶች ይያዛሉ።

ዲኤንኤ ዊክሊ የተሰኘ የጤና ድረገጽ እንደሚለው ፤ ዛሬም ድረስ በግብረ ስጋ ግንኙነት ስለሚመጡ በሽታዎች መነጋገር ' እንደ ሚያሳፍር እና እንደ ተከለከለ  ' አድርገው የሚቆጥሩ ብዙ ናቸው።

ከጤና ባለሞያዎች ጋር መመካከር ፣ ስለጉዳዩ ማወቅ ፣ ሲታመሙ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ የሚያፍሩ ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም።

ነገር ግን በበሽታዎቹ በየዕለቱ ሚሊዮኖች የሚያዙ ሲሆን በየአመቱም ሚሊዮኖች የሞታሉ።

በመሆኑ ስለ ጉዳዩ አሳስቢነት ሳያፍሩ መነጋገር ፣ የመተላለፊያ የመከላከያ መንገዶች ማወቅ ፣ የጤና ባለሞያዎችን ማማከር ምክራቸውንም መስማት ይገባል።

@tikvahethiopia