TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MustafaMohammed

የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝን በሚመለከት ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው መግለጫ ሰጥተዋል።

ዋና ዋና ነጥቦች፦

• የክልሉ ህዝብ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት፣ በዜጎች ህይወት ልያስከትል የምችለውን አደጋና የክልሉ ህዝብ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው ጥንቃቄዎች አይመጣጠንም ብለዋል።

• የሶማሌ ክልል ህዝብ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ከፌዴራል እና ከክልሉ መንግሥት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መተግበሪያዎችና መመሪያዎችን በአግባቡ ተግባራዊ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

• የሶማሌ ክልል በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠረጠሩ እና የተገኘባቸው ሰዎችን የለይቶ ማቆያና የህክምና ድጋፍ የሚሰጡ ማዕከላትን ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።

• የክልሉ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሸኝ ለመግታት የተለያዩ ኮሚቴዎች ማቋቋሙን ተናግረዋል።

• የህክምና ባለሙያዎች ቀን ተሌሊት በወትሮ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

• ፀጥታ አካላቱ ከአጎራባች ሀገራትና ክልሎች ምንም አይነት የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት እንዳይገቡ ተሰማርተዋል።

#SRTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

በትላንትናው ዕለት በሶማሌ ክልል የአይሻ ወረዳ ፣ ደወንሌ ኮሪደር በሚገኝ ኬላ ከጅቡቲ ለሚገቡ አሽከርካሪዎች ኮቪድ-19 ለመመርመር የሚያስችል ናሙና መውሰድ ተጀምሯል።

ናሙናውን ለመውሰድ የሚያስችል እና ለማቆያ የሚያገለግል የድንኳን አልጋ በማዘጋጀት ነው ስራው መጀመሩን #SRTV የዘገበው።

የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ናሙና ምርመራው ኮንቴኔር በሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ ነው የተጀመረው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለ22 ዓመት ጅቡቲን የመሩት ፕሬዜዳንት ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን እየተወዳደሩ ነው !

የጂቡቲ ህዝብ ለፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ዛሬ ድምፅ በመስጠት ላይ ይገኛል።

የጅቡቲው ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ለፕሬዜዳንትነት እየተወዳደሩ ይገኛሉ።

ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድምፃቸውን ሰተዋል።

ከ200 ሺህ በላይ ድምፅ ሰጪዎች የተሳተፉበት ምርጫ ምሽት ላይ ይዘጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የ73 አመቱ ፕሬዝዳንት ጌሌ ለ22 አመታት የጂቡቲን መርተዋል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ በር ላይ የምትገኘው ጂቡቲ አንድ ሚሊየን ገደማ ህዝብ ያላት ሲሆን የተለያዩ ሀገራት ወታደሮች የጦር ሰፈር ይገኙባታል።

#SRTV
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Somali

በሶማሌ ክልል መዲና ጅግጅጋ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመው የበደር የትራንስፖርት ማህበር በዛሬው እለት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሄደ፡፡

ማህበሩ በከተማ ትራንስፖርትና በመካከለኛ ሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰማራ ሲሆን በቅድሚያም አገልግሎቶቹን በጅግጅጋ ፤ ቱጉጫሌ ፤ ደገሀቡርና ድሬዳዋ ከተሞች እንደሚጀምርም ነው የተገለፀው፡፡

#SRTV

@tikvahethiopia
የሶማሊ ክልል ሰላምና ደህንነት እንዲጠናከር ማሳሰቢያ ተሰጠ።

የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የክልሉ ሰላምና ደህንነት እንዲጠናከር ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

የክልሉ ፕሬዝዳንት ማሳሰቢያውን የሰጡት ትላንት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር መስከረም 20 በክልሉ የሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እና በሰላምና ደህንነት ዙሪያ ሲወያዩ ነው።

የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ሙሁመድ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ዜጎች በሰላም ድምፃቸውን ሰጥተው እንዲገቡና በክልሉ ያለው አስተማማኝ ሰላም የበለጠ እንዲጠናከር የፀጥታ አካላት እና ህዝቡ በጋራ መስራት አለባቸው ብለዋል።

በውይይቱ የክልሉን ሰላም እና ደህንነት የበለጠ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል።

መስከረም 20 2014 ዓ.ም በክልሉ ለሚካሄደው ምርጫ እጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው። #SRTV

@tikvahethiopia
#ShabelleBank

የሸቤሌ ባንክ ምስረታ ስነ- ስርአት ተካሔደ።

የሸቤሌ ባንክ መመስረቻ ስነ ስርአት ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተካሒዷል።

በ2011 የሶማሊ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም " ሄሎው ካሽ " በሚል የገንዘብ ግብይትና ዝውውር አገልግሎት መስጠት የጀመረው ተቋሙ ለመቶ ሺህ ለሚሆኑ የአካባቢው ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሮ እያገለገለ ይገኛል።

በማይክሮ ፋይናንስነት አገልግሎቱ እስከ አሁን 1 ሚሊየን 3 መቶ ሺህ በላይ የሚደርሱ ደንበኞችን እንዳሉት ይገለፃል።

ተቋሙ በእስከ አሁን ሒደቱ በ43 የተለያዩ የአገልግሎት ማዕከላት ሲኖረው 500 ቋሚ ሰራተኞችን ይዞ በ 3.7 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር ጠቅላላ የሐብት መጠን በማስመዝገብ በ2013 አመተ ምህረት ከብሔራዊ ባንክ ባገኘው እውቅና ወደ እስላሚክ ሸቤሌ ባንክነት ማደግ ችሏል።

በዛሬው የባንክ በምስረታ የሐገር ሽማግሌዎች ፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፣ አምባሳደር ዶ/ር መሐሙድ ድሪር ፣ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሐሰን መሐመድ፣ የተለያዪ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#SRTV

@tikvahethiopia