TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ: ትናንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ #ቦይንግ 737 #ET302 አውሮፕላን የተከሰከሰበት ቦታ በቁፋሮ የወጡ ነገሮችን ከላይ ባለው ፎቶ መመልከት ይቻላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ET302

ከኢትዮጵያ ወደ ኬኒያ ሲያመራ በተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎችን ማንነት የመለየት ስራ ተጠናቀቀ፡፡ ከስድስት ወር በፊት ከኢትዮጵያ ወደ ኬኒያ ሲያመራ የነበረውና በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ መንገደኞች መሞታቸው ይታወሳል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-09-4
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ በቦሌ አየር መንገድ ካርጎ ተርሚናል እስካሁን የነበረው የቦይንግ 737 ET 302 የመንገደኞች እና የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ቅሪተ-አካል ዛሬ የDNA እና የForensic ማጣሪያውን ጨርሰው ለተጎጂ ቤተሰቦች በመሸኘት ላይ ነው። Via Signorina solomon/TIKVAH ETH FAMILY/ @tsegabwolde @tikvahethiopia
#ET302

ከወራት በፊት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ግለሰቦች አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው። የሟቾቹን አስከሬን ለመለየት የዲኤንኤ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፤ የሰባት ወራት ጊዜም ፈጅቷል። በቦሌ አየር ማረፊያ የቤተሰቦቻቸውን፣ የዘመድ ወዳጆቻቸውን አስከሬን ሊወስዱ የመጡ ግለሰቦች በሃዘን ድባብ ውስጥ ነበሩ። ከአደጋው በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው አስከሬናቸውን ማየት የቻሉት። በዛሬው ዕለትም በኬንያ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ግለሰቦች የሃዘን ሥነ ሥርዓትም ይካሄዳል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለስልጣናት እንደተናገሩት መለየት ያልተቻለ አስከሬን እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶች አደጋው በተከሰተበት አካባቢ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ግለሰቦች በሚሰራው የማስታወሻ ስፍራ የሚቀበር ይሆናል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት
PHOTO: TIKVAH-ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ET302

መጋቢት 1/2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737-800 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች የፊታችን ማክሰኞ እዚሁ ሀገራችን ላይ በሚደረግ የመታሰቢያ መርሐ-ግብር ለመታደም ይሰባሰባሉ ተብሏል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ET302

መጋቢት 1/2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ET302 ማክስ 8 አውሮፕላን የተከሰከበት ቦታ ላይ ዛሬ የሙት አመት መታሰቢያ ስነስርአት ተከናውኗል።

ስነስርአቱ የተዘጋጀው በአካባቢው ነዋሪዎች ሲሆን በሚልኪ የማስታወቂያ ስራዎች አስተባባሪነት የሚከናወን መሆኑን የሚልኪ አድቨርታይዚንግ ስራ አስኪያጅ አቶ ቀልቤሳ መገርሳ ተናግረዋል።

#EPA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia